tgoop.com/ethiopianarchitectureandurbanism/14471
Last Update:
ጥንታዊ ቤት መፍረስ።
ፊትአውራሪ አጥናፍሰገድ ይልማ ቤት።
የፊታውራሪ አጥናፍ ሰገድ ይልማ ቤት ከግራዝማች ሳህሌ ቤት በጣም ቅርብ ሆኖ ይገኛል ። ይህ ከግራዝማቸወ ሳህሌ ቤት በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 200 ሜትሮች ርቀት ላይ በዘውዲቱ ጎዳና በቀኝ በኩል ይገኝ ነበር። የፊትአውራሪ አጥናፍሰገድ መኖሪያ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የልቤ ፋና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሆኖ ያገለግል ነበር። የሚያምር ባለ ሁለት ፎቅ የነበረው ህንፃ በዕቅዱ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ነበር። በመሬት ወለል ዙሪያውን የሚሄድ ክፍትና ዝግ በረንዳ ያለው ሲሆን በመጀመሪያው ፎቅ ላይ ደግሞ የተዘጋ በረንዳ ነበረው።
በሮች እና መስኮቶቹ ከፊት ለፊቱ ላይ ወጣ ብሎ የተሰራው ውብ ግንብ ላይ ያሉትን ትናንሽ መስኮቶችን ጨምሮ ጨምሮ ቅስት (arched openings) ነበሩ። ይህ የግማሽ ባለ ስድስት ጎን ግንብ በተለዩ ማዕዘኖች (quoined corners) ያጌጠ እና በ ፒራሚዳዊ ጉልላት የተሸፈነ ነው። ግድግዳዎቹ ከድንጋይ የተሠሩ ሲሆኑ እንጨት ግን በረንዳዎቹ ግን በእንጨት ተገንብተዋል።
ፊትአውራሪ አጥናፍ ሰገድ በአካባቢው የሚገኘውን መሬት በዘውዲቱ ዘመነ መንግስት ተቀብለው መኖሪያ ቤቱን በነዚያ አመታት ውስጥ የገነቡት ይመስላል።
የአካባቢው መረጃ ሰጭዎች እንዳስረዱት ቤቱ ህንዳዊ መልክ ሊይዝ የቻለበት ምክንያት በአቅራቢያው የሚገኘውን የገብርኤል ቤተክርስቲያንን እና ሌሎችን ጨምሮ የነደፈው ህንዳዊው ህንጻ ነዳፊ ወሊ መሀመድ ህንጻውን የነደፈው በመሆኑ ነው።
መኖርያ ቤቱ ሰፊ መሬት የነበረው ሲሆን ፣ በኋላም የገብርኤል እና የኡራኤል አብያተ ክርስትያናት ቀሳውስት የሰፈራ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ቦታው ሊቀንስ ችሏል።
ይህ ጥንታዊ ቤት በትናንትናው እለት ፈርሷል።
ዋቢ። Natty Nigussie, BCAA, Daniel Demere 90's ልጆች፣, Theodora Berhanu, Ehsan Saied, Old Tracks In The New Flower A Historical Guide to Addis Ababa page 168, Milena Batistoni, Gian Paolo Chiari
@ethiopianarchitectureandurbanism
BY Ethiopian Architecture Construction and Urbanism
Share with your friend now:
tgoop.com/ethiopianarchitectureandurbanism/14471