tgoop.com/ewuntegna/11951
Last Update:
🌼+‹‹ ዘመኑን ዋጁ ››+🌼
ዘመናት ያረጃሉ በየዘመን ውስጥ ያለ ሰው እንደሚመላለስበት ጊዜ አርጅቶ በሌላ መተካት መገለጫው ነው እንደ ዓዲስነቱ የሚኖር ጌታችን አምላካችን ወደ እርሱ ከኃጥያት ዘመናችን በንስኅ ተለውጠን እንመለስበት ዘንድ ዘመን ይጨምርልናል ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን በላከው መልእክቱ እንዴት በዘመን መመላለስ እንደሚገባን ይነግረናል ፦ "እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደ ሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንደ ምትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖቹ ክፍዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ"። (ኤፌ 5፥15-16) መዋጀት ማለት ፦ መፈተሽ ፣ መመርመር ፥ ማወቅ ማለት ነው ። ጥበበኞችስ ስጋውያን ያልሆኑት እንዴት በማን እንደ ሚመላለሱ ፈትሸው የሚያውቁ ናቸው ። በሥነ ምግባር የሚኖሩ እርሱን በህግ "የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔር መፍራት ነው " መዝ 110፥) እንደሚል የሚለወጠን ሰውን ሳይሆን የማይለወጠውን እርሱን እያዩ እንደሚኖሩት ጥበበኞች በተሰጠን ዘመን እንድንመለስ ይጠራናል ።
" የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትን ወደ ጻድቃን ጥበብ " የሚመልስ " ሉቃ (1፥17) አባቶች አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ልጆች የተባሉትም ሐዋርያት ጥበብ ወደተባለው ክርስቶስ የሚመለስ ነው እንደተባለለት ምድራዊው መልአክ ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ወደ ሚነግረን እንመለስ እኛን ወደ ጥበብ ክርስቶሰ ክፍ ቀን ከተባለበት እኛና እግዚአብሔር ከተለያየንበት እንደሞኝ ዘመንን በኃጥያት ካሳለፍንበት ተመለሱ ተውት ይብቃቹሁ ጽድቅን የምትሰሩበት ዘመን ይሁን እያለ የተሰጠን ዘመን ወደ እርሱ መመላሻ መሆኑን የሚያስተምረን ነውና። ሐዋርያት "እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን" 1ኛ ቆሮ 1 ፥16 ይሉ ነበር ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ሐሳብ ስለነበራቸው ዘመናችንን ሰማያዊ ሐሳብ ምናስብበት ወደ ቅዱሳን የሕይወት መንገድ ምንመለስበት ያድርግልን ።
እንኳን አደረሳቹሁ ለአዲሱ ዓመት 2017 ዓ.ም ። 🙏🌼
ዲያቆን ፍፁም ከበደ
መስከረም 1 2016 ዓ.ም
ዲላ ኢትዮጵያ
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/11951