tgoop.com/ewuntegna/12087
Last Update:
የኦርየንታል ኦርቶዶክስ እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የነገረ መለኮት ውይይት ከ34 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካይሮ መካሄድ ጀመረ !
ጉባኤው “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14) በሚል መሪ ቃል በእምነት እና እና በአገልግሎት እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂደዋል፤ ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ በግብጽ ቅዱስ ቢሾይ ገዳም “ሎጎስ” የስብሰባ ማዕከል መካሄድ የጀመረ ሲሆን በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት እና በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ይፋዊ የነገረ መለኮት ውይይት በዚህ ስብሰባ ተካሂዷል። ዓላማው ከ30 ዓመታት በላይ የተቋረጠውን ይፋዊ የሥነ-መለኮት ንግግር እንደገና ለመቀጠል እና እንደገና ለመገምገም መሆኑን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አስታውቃለች።
ጉባኤው የተከፈተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና በፓትርያርክ አቡነ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ መልእክት ነው።
በስብሰባው ላይ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያናት ቤተሰቦች ላይ የሚነሱ ልዩ ልዩ የአስተምህሮ ጉዳዮች ወደ አንድ ወጥ አቋም ለመድረስ በማለም በዚሁ ልክ ውይይት መደረጉ ነው የተገለጸው።
የምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት ልዑካንን ጨምሮ በጉባኤው የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (አስተናጋጅ ቤተ ክርስቲያን)፣ የአንጾኪያ እና የመላው ምሥራቅ ፓትርያርክ (ሶርያ )፣ የአርመን ኦርቶዶክስ፣ የኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ የኤርትራ አቢያተ ክርስቲያናት መወከላቸውን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ገልጻለች ።
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/12087