tgoop.com/ewuntegna/12097
Last Update:
ራስን ድል መንሳት
የስጋ ምኞትንና ፍላጎትን አስመልክቶ ጾምና ድንግልናን ራስን ድል የመንሳት መንገዶች
ናቸው። ነፍስን አስመልክቶ የሚጠቀስም ሌላ መንገድ አለ።ራሱን የሚገዛና እርሱነቱን ወደ
ዓለማዊ ደስታ ከማዘንበል የሚያግድ ሰው ብጹዕ ነው።
ማንነት ልታይ ልታይ ሲል፡ ጉራውን ሊገልጥ ሊተብት ይችላል።በዚህ ሁሉ ግን ልንቃወመው
ይገባናል። ለእኛ #ከእግዚአብሔር ጋር መደሰትና መልካም የሆነው ነገር ለመጪው ህይወት
ብናቆይ የሚሻለን መሆኑን ራሳችንን ልናሳምነው ይገባናል፡፡ በዚህ ዓለም ድስታን ለማግኘት
በሚፈልጉ ሰዎች ላይ #የመድኋኒ_ዓለም ቃል ይመሰክርባቸዋል፡- " . . . እውነት
እላችኋለው፡- ዋጋቸውን ተቀብለዋል።"ማቴ6፡5፡፡
ስለዚህ በምድር ላይ ያሉ መብቶችህን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እግዚአብሔር እያንዳንዱ
ዕንባህን ከዓይኖችህ ላይ የሚጠርግበት በወድያኛው ዓለም ቢሆንልህ ይሻልሃልና።
ማንነትህ ወይም ስጋህ አሁን ላለህበት ዓለም ደስታ የሚያዘም ከሆነ በርትተህ ተከላከላቸው።
በራስህ ወይም በስጋህ ላይ የምይወስደው ይህ እርምጃ ጭካኔ አደለም፡ለእነርሱ ዘላለማዊ
ሕይወትን ማረጋገጫ እንጂ!
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚንከባከባት ያጠፋታል። ራሱን በጥብቅ ከመቆጣጠር ችላ የሚል
ሰው በእርሱ ላይ ኋይል እንዲኖረው ያደርጋል።ሰለሆነም ራሱን ለጽድቅ ከሚያለማምደውና
#የእግዚአብሔር መንገድ ከሚተገብረው ሰው በተለየ ሁኔታ በመንፈሳዊ ጠባዩ ላይ
እንዲያምጽ ያደርገዋል።
ራስን ድል መንሳት የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ከስጋ ደስታ ጋር እንደማይነጻጸር እርግጠኛ
ሁን። ከሁሉ በጣም የሚያስደንቀው የራስ ጉራ ሙሉ ለሙሉ መጥፋት በሚገባው በመንፈሳዊ
አገልግሎት ውስጥ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው።
#ቅድስነታቸው_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
(መንፈሳዊ ውግያዎች ከሚል መጽሓፋቸው የተወሰደ ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።)
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/12097