tgoop.com/ewuntegna/12661
Last Update:
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።
የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።
የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።
የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።
ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።
ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/12661