tgoop.com/ewuntegna/13489
Last Update:
👉 መቅደሲቱ ወደ መቅደስ
''ኪሩቤል የሚጋርዷት መቅደስ አንቺ ነሽ " እንዲል ቅ.ኤፍሬም አንድም ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ እንዲል መዝ 131፥8
እንደሚታወቀው በዓመት በዓመት በሚሰጠው ስብከት ትምህርት እና በገድላት በታሪክ መጻሕፍት እንደተረዳን ቅድስት ንጽሕት እመቤታችን የስእለት ልጅ መሆኗን ሁሉም ይረዳል ሐናም ቃሏ ሳይታበል ልቧ በልጅ ፍቅር ሳይታለል የመለኮትን እናት አማናዊት መቅደስ እመቤታችንን ለቤተ መቅደስ ሰጥታለች
ሐና ሆይ በብዙ ገዓር በብዙ ልመና በብዙ ውጣ ውረድ ያገኜሻትን ምትክ የለሽ አንዲት ቅንጣት ታናሽ ብላቴና ድንግልን መስጠት እንዴት ቆረጥሽ ? ! ለልጅ ያለሸ የእናትነት ፍቅርሽስ መቸ ተፈጸመ ? ልብሽስ እንዴት ሳይለወስ ቀረ ?
የልጅ ፍቅርም አልጠገብሽም ጠግበሻል እንዳንልማ ታናሿ ብላቴና ድንግል አፏ እህል ሳይለምድ ሆዷ ዘመድ ሳይወድ ገና በሦስት ዓመቷ ከእቅፍሽ መለየቷ ትልቅ ማረጋገጫ ነው
እኛ የምናውቀው የእናት አንጀት እንዲህ አይደለምና
ሐና ሆይ እኔ ግን ላንቺ አንክሮ አለኝ
ማን ይሆን ?
የልጁን ፍቅር ትቶ
ልጁን ከእቅፉ ለይቶ
በገባው ቃል ኪዳን ተገኝቶ
የመጀመሪያውን እሽት
ገና በሦስት ዓመቷ
መስጠት የሚቻለው ?
ኦ ወዮ እንደምን ያለ መጥዎተ ርእስ (ራስን መስጥት ነው)
ለዚህ አንክሮ ይገባል
ሐና ሆይ መቅደሲቱን ወደ መቅደስ መውሰድሽ ትክክል ይሆን ? በእርግጥም ትክክል ነው ምክንያቱም ስእለት ብጽዐት ነውና "የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ " የሚለው የአበው ብሂልም ላንቺ ይመስላል እኔ ግን ሳስበው ሰው ወደ መቅደስ የሚሔደው ለመቀደስ ነው( ቀ ይጠብቃል) የድንግል መሔድ ግን ለምን ይሆን ? እርሷ እንደሆነች ከዕለተ ልደት እስከ ዕለተ ዕረፍት እንከን አልባ ንጽሕት ቅድስት ናት
ታዲያ ወደመቅደስ የወሰድሻት ለምን ይሆን ?
ነገሩ እንዲህ ነው እኛ ወደመቅደሱ መቅረብ ቢሳነን በመዓዛ ቅድስናዋ በመዓዛ ንጽሕናዋ አማንዊት መቅደስ እመቤታችን አማናዊ መቅደስ ክርስቶስን ወደእኛ ማቅረብ ፈልጋ ነው
ታላቁ የድኅነት ምሥጢርም ይህ ነው እኛም በመቅደሰ ርእሱ እንቀደስ ዘንድ ነው ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ወደመቅደስ ገባች ስንልም
በመቅደሰ ርእሱ እንቀደስ ዘንድ አማናዊ መቅደስ ክርስቶስ በእመቤታችን ማኅጸን ለተዋሕዶ አደረ ማለት ነው ክርስቶስ በማኅጸነ ድንግል አደረ ማለትም በልጅነት በሀብታት በምሥጢራት ከብረናል ማለት ነው
መቅደሲቱ ወደ መቅደስ ገባች የስእለት ልጅ ናትና አንድም መቅደሲቱ ወደመቅደስ ገባች በፍጹም ተዋሕዶ እንኖር ዘንድ
" መቅደሲቱ በመቅደሰ ርእሱ እንደኖረች በመቅደሰ ርእሱ ያኑረን " ።
በመ/ር አብርሃም ፈቃዴ
@Ewuntegna
@Eeuntegna
@Ewuntegna
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/13489