tgoop.com/ewuntegna/14269
Create:
Last Update:
Last Update:
በነበር ጊዜን መጨረስ ጽድቅ አይደለም።
ብየ ነበር፣አስቤ ነበር፣ቢሆን ጥሩ ነበር፣እንዲህ መሆኑን አውቄ ቢሆንማ እንዲህ አደርግ ነበር፣ነበር..በነበር ትችት ጊዜያችን አለቀ። በነበር ጊዜን መጨረስ ጥቅሙ ምንድን ነው? ምንም።ወቃሽ ህሊናን ለማስተኛት ብቻ ይጠቅም ይሆናል።
ለነፍስም ለሥጋም የሚጠቅም ተግባርን ካልሠራንበት የነበር እድሜ ዕዳ ነው።
ነበር እያሉ መውቀስ እና ማማረር ስንፍናን እና ውሳኔ አልባነትን በራስ ላይ ማጽደቅ ነው።
ተግባር በሌለው ንግግር ነበር እያሉ ብቻ መናዘዝ የጽድቅ ትሩፋት ሊሆን አይችልም።
የአባታችን የቅዱስ ጳውሎስ ምክሩ ግን ይች ናት፦"ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።"፪.ቆሮ.፲፩፥፲፪ ብሎ ምክንያተኞች እንዳያመካኙ ከተግባረ ወንጌል አለመለየቱን ነግሮናል።
ሌሊት በድንኳን ስፌት ቀን በትምህርት የተጋ ሁኖ ኑሯልና።
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
BY ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት
Share with your friend now:
tgoop.com/ewuntegna/14269