tgoop.com/eyorkis/1271
Last Update:
(ከመጽሐፉ የጀርባ ገጽ የተወሰደ -ከውስጥ)
የደስታ ቀናት እንደ ሰማይ ሲርቁ... ክፋ ቀናት እንደ አጀብ ሲከቡን... የተጠበቀው ቀርቶ የልተጠበቀው ሲሆን... ሞት አንድ አማራጭ ሆኖ ሲቀርብ... ውስጣዊ ሰላማችን ሲረበሽ... አርጋታ ፈጽሞ ሲጠፋ....
...ያን ጊዜ “ጌታ ሆይ እስከመቼ?” እንላለን፡፡ ደግሞም በልጅነት ሰቆቃ በአባቶቻችን አንደበት “እስከማዕዜኑ?” እንላለን፡፡ አንባችን አንደ መጠጥ፣ ሀዘናችንም እንደ መበል ይሆንበናል፡፡ የቀናት ጠንሳሽ የሆነው አባታችን እግዚአብሔር ግን “ታገስ፣ የመጠበቅን ፍሬ ትበላለህ” ማስቱን ይቀጥላል፤ እኛም “አምላኬ ሆይ፣ እንዴት ልታገስ? እሰከመቼስ ልጠብቅ?” አንላለን፡፡ ከዚያም ቃሉን ያስታውሰናል፣ የቀደሙ ቅዱሳኑን አብነት ይዘክርልናል፡፡
“እንደ ልጄ እንደ ዳዊት ቀና ሁን፣ እንደ ታላቁ ታጋሽ እንደ ኢዮብ ሁንልኝ፣ የቀጠርኩልህ ቀን ሲደርስ የመከራህን ቀናት አስረሳሃለሁ! እንደ ተወዳጁ ልጄ እንደ ወልድ ትንሳኤህ እስኪገለጥ እርጋታን ገንዘብህ አድርግ!'' ይለናል፡፡ በቅዱስ ቃሉ ያባብለናል፡፡
የህማማት ቀናቶቻችን እንደ ግዮን ወንዝ የረዘሙ ሲመስሉ፣ የህዝባችን እፎይታ፣ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደ ጌታችን መምጫ ቀን ሲርቁብን፣ ህይወት ከንቱ፣ መኖርም ምናምንቴ መስሎ ሲታይ... የምድረ በዳው መንከራተት ከንዓናችንን ሊያስረሳን ሲደርስ፣ መራርነት ተስፋችንን ሊያስጥስን ሲተጋ፣ የስጋ ድካም ከዘለዓለማዊው እጣ ፈንታችን ሊያናጥበን ሲል... ያን ጊዜ የታላላቅ አባቶች ምክር፣ የቅዱሳን ጥበብ፣ የታጋሾች ምስክርነት ያስፈልገናል፡፡
"እስከማዕዜኑ"
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ምንጭ፦እስከመንገድ የቴሌግራም ቻናል
@eyorkis
BY ኢዮርቅስ
Share with your friend now:
tgoop.com/eyorkis/1271