tgoop.com/fekr_bicha/1123
Create:
Last Update:
Last Update:
➖➖➖➖➖➖ ♥ ➖➖➖➖➖➖
❤️ እናቴ ❤️
ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።
እማ ዛሬ ፍቅርሽ ገባኝ!!!
━━━━━━━━✦❤️✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 👍
Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
BY ስለ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/fekr_bicha/1123