tgoop.com/fekr_bicha/1130
Create:
Last Update:
Last Update:
➖➖➖➖➖➖❤️➖➖➖➖➖➖
ጨረቃ 🌕
ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ
እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ
ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ
አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ
ቀና ብዬ አይቻት
ስላንቺ ነገርኳት
ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት
አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት
ለብዙ ደቂቃ ስናወራ ቆየን
እኔ ጨረቃ በጣም ተወያየን
ለካ አሷም አፍቅራለች
ፀሀይን ለማግኘት በጣም ናፍቃዋለች
ነገርኳት ብታዝንም አንደማታገኘው
ፀሀይ ቀን ቀን እንጂ ለሊት ምን ስራ አለው
አዘነች ትዘና ተከፋች ትከፋ
አኔን አታይም ወይ ስጠብቅ በተስፍ
የኔም ፍቅር ሆኖ ልክ እንደጨረቃ
ላገኝሽ አልቻልኩም አቅቶኛል በቃ
ጨረቃዬን ቃኘሁ ብድግ አልኩኝ ቀና
አይዞሽ አትከፊ ለኛም ቀን አለና
ምን አልባት ፈጣሪ ፀሀይን በለሊት
ወይ አንቺን ቀንአርጎ ለቀናችን ድምቀት
ያሳካው ይሆናል ያንቺን ፍቅር አውነት
ብዬ ነገርኳት ዋሸኋት
ፈገግ አለች ጨረቃዬ ሳቀች ጥርሷ ፈካ
ደና ዋል አለቺኝ ሊነጋ ነው ላካ
አይ ጨረቃ አምናኛለች መሰል
ክፋቱን ሳታውቀው በፀሀይ መቃጠል
ደስ ብሏት ሄደች
ክብ ሆና እየበራች
አኔ ግን ተከፋሁ
የሚያፅናናኝ ፍጡር መካሪ ስላጣሁ
🌕🌖 ❤️
Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
BY ስለ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/fekr_bicha/1130