tgoop.com/fekr_bicha/1132
Create:
Last Update:
Last Update:
🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟
#ፍለጋ_ላይ .....
ከልብ የገባን ሰው እንዴት ነው 'ሚወጣው?
የእውነተኛ አፍቃሪ ምን ነበረ ዕጣው?
ተፈቃሪ የለም ደግሜ ገበየኹ
ዓለም ውሸታም ናት ብዙውን ሰው አየኹ!
አገኘኹ ይልና ልቤ የልቤን ሰው
ግና...
እምነቴን ጨለማ ወረሰው
አጣኹ የልኬን ሰው
ሚዛኔ ላይ ቆሞ እንባዬን 'ሚያብሰው
የለም ለእኔ ያ ሰው!
ክፉ ነኝ እንዳልል...
እውነተኛ ፍቅር ከልቤ ይፈልቃል
ታድያ?
ፍቅርማ ከክፋት ይልቃል!
ከሽንገላ ያርቃል
ግን የሆዴን ማን ያውቃል?
ሞኛ ሞኝ አጫውቶኝ፥ ሕጻን አዋቂውን በእኔ ይሳለቃል
ይዝናናል ይስቃል
መንስኤው በእኔ ያሳብቃል
ሕጻኑም ይስቃል!
ይኸውልሽ ሔዋኔ...
ካለሽበት መንደር በጊዜ ካልመጣሽ
ቆሞ ቀርነት ነው የወደፊት ዕጣሽ
ይሄም ካላሳጣሽ!
ነይ ነይ እያልኩሽ ነው፤ ነይ ቶሎ ድረሺ
ጊዜ ከወርቅ በላይ፤ መሆኑን አትርሺ!
አትሽሺ በይ "እሺ"
አንቺ የእኔ ሴት...
እኔ ላይ ምታደርጊ ሐሴት
ደርሶሽ ካነበብሺው በዪኝ "መጥቻለው!"
ከእንግዲህ አልጠይቅሽ ዕርሜን ጨርሻለው!
አቅሜን አጥቻለው!
ነይ 'ፈልጌሻለው!
ላውቅሽ አውቄያለው!
አንቺ የእኔ ሚስት አትመጪም? 😂
ወይስ ጭራሽ ከቤትሽ አትወጪም 😜
ከኔ አታመልጪም! 🆗
🔵
Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
BY ስለ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/fekr_bicha/1132