tgoop.com/fekr_bicha/1134
Last Update:
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
👱♀👫አንቺን እያፈቀሩኩ…💝👫
ቃል
👨👩👱♀👱👴👵👳♀👳👮♀👮
አንቺን እያፈቀርኩ ከማህፀን ወጣሁ፡
አንቺን እያፈቀርኩ ብዙ ነገር አጣሁ
አንቺን እያፈቀርኩ እየመሸ ይንጋ
አንቺን እያፈቀርኩ ይለፍ ክረምት ና በጋ
አንቺን እያፈቀርኩይለፍም እድሜዬ
አንቺን እያፈቀርኩ ልቅርም ብቻዬን
💚💛❤️💙💜🖤💝💖💞💝
ለአንቺ እየኖርኩ እኔን ይክፋኝ
አንቺን ደስ ብሎሽ እኔን ይጭነቀኝ
ልሁን እማይጠቅም ልሁን እርካሽ
አንቺን እያፈቀርኩ ለ አፍታ ሳረሳሽ
ልኑር በድር በድር ልኑር በጨለማ፡
ምን ንብረት አለኝ ለአንቺ እማይሆንማ
ዉሰጂው ልቤን ውሰጂው ደሜን
ይምቱኝ ይቀጥቅጡኝ ስለ አንቺ እኔን
አንቺን ከቶ አይክፋሽ እኔ እያለሁኝ
አንቺን እያፈቀርኩ አለም ተለፈኝ
አንቺ ላይ እሚሆነው ይሁን እኔ ላይ
ምድርም ከፍ ዝቅ ትበል እኔን ታሰቃይ
ባዶም ቢሆን ይህ ዐለም ያለአንቺ
መውደዴን አትወቂው አትረጂው አንቺ
💚💛❤️💙💜🖤💝💖💜💙
አንቺን እያፈቀርኩ ልክሳም ልጥቆር
አንቺን እያፈቀርኩ ልምሰልም አፈር
አንቺን እያፈቀርኩ አልሳቅ አልጫወት
አንቺን እያፈቀርኩ ትለፍም የኔ ህይወት
አንቺን እያፈቀርኩ አልብላ አልጠጣ
አንቺን እያፈቀርኩ ከቤቴም አልውጣ
ከወደኩበት ቦታ አንድ ቀን ብቅ ብለሽ
አፃናነተሺኝ ሂጂ አለሁልህ ብለሽ
አግቢ ውለጂ ከብደሽም ኑሪ
ይክፋኝ ግድ የለሽም እኔ የአንቺ አፍቃሪ
💝💘💖💚💛❤️💝❤️💛💚
አደራ ግን ነይ በህልሜ ማታ
አንቺን አይቼ ላንባ መንታ መንታ
እመጣለው የሰርግሽ ለታ
እንቺን እያፉቀርኩ ሉኑር በትዛታ
ፅልይልኝ እንዳልሞትብሽ
አልቻልኩም አቃተኝ እኔ አፍቃሪሽ…
.
@fekr_bicha
BY ስለ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/fekr_bicha/1134