tgoop.com/fekr_bicha/1140
Last Update:
🍃🍂✟በፍቅሩ አሸንፏል ✟🍂
ምን አይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መውደድ
ንጉሱን ከሰማይ ከዙፋን የሚያወርድ
እስኪ የትኛው ነው የትኛው ስራችን
እስከሞት ውለታ የሚከፈልልን
ፍፁም ይገርመኛል ከአይምሮ በላይ ነው
ስለአንዱ በግ ብሎ መንጋውን የተወው
ፍፁም ፍቅር አየን ፍፁም ትህትና
አምላክ ስለ ሰው ልጅ ከላይ ወርዷልና
እንዲ ለዋለልን ለታላቁ ጌታ ለፍቅር ባለቤት
ሞትን ደገስንለት በአይሁዶች እጅ ተሰቃይቶ እንዲሞት
አምላክና ወንበዴ አንድላይ አቁመን
ወንበዴውን ፈታን ከአምላክ አስበለጠን
ይህን ክፋት አይቶ ከቶ መች እራቀን
እሱ አቀርቅሮ እኛን ቀና አረገን
ድንጋዩ ልባችንን መች ፍቅሩ ሰበረው
ገንዘብ አስበልጠን በ 30 ዲናር ለጠላት ሰጠነው
ንፁህ ሆኖ ሳለ ሀጥያት የሌለበት
በሀሰት ተከሶ ሞት ተፈረደበት
አኛ እየሸጥነው ወዳጄ ይለናል
የፍቅር አምላክ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል
መስቀል አሸክመን ቀራኒዮ ሰደድነው
እራሱ ፍቅር በሀሰት ልንሰቅለው
እሁንም ፍቅር ነው አሁንም ዝምታ
ለጠላቶቹ ነው የሚያዝነው ጌታ
እንዲህ እየወደደን እኛ መች ወደድነው
ቀትር 6 ሰዓት ከመስቀል አኖርነው
አሁንስ ይገርማ በእውነት ድንቅ ነው
መስቀል ላይም ሆኖ ማራቸው ነው ሚለው
ቁስላችንን ሊያድን ስለኛ ቆሰለ
ከሞት ሊያነሳን ሞቶ ተቀበረ
እጅግ ቢበረታም የኛ በደላችን
በፍቅሩ አሸንፏል ኢየሱስ ጌታችን
✍ ዮዳሄ
አዘጋጅ : ስለ ፍቅር
┄┄┉┉✽»✿»🌺✽┉┉┄┄
❣@fekr_bicha ❣
BY ስለ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/fekr_bicha/1140