tgoop.com/fker12/1779
Last Update:
ዛንዛኒንን ነው የምጠራልህ ፡ ሲባል የማይፈራ ህጻን የለም ።
......
የዚህ ልጅ እናት ፡ ይህንን ህጻን የገኘችው ፡ ከአመታት የልጅ ናፍቆት በኋላ ነው ። ከሱ በፊት አምስት ልጅ ወልዳ በሞት አጥታቸዋለች ። እና በመጨረሻ ግን አንድ ልጅ ወለደች ።
ዛንዛኒ ስልት ስም አወጣችለት ። ሆኖም የወለደችው ልጅ ፡ ከሌላው ሰውነቱ አንጻር ሲታይ የጭንቅላቱ መጠን አነስተኛ ነበር ።
ይህም ገፅታው የተለየ አይነት መልክ ይሰጠው ጀመር ።
......
ይህም ገፅታው በመንደሩ ሰወች እንዲያገሉት ምክንያት ሆነበት ። በመንደሩ ውስጥ ህጻናት ሲጫወቱ አይቶ አብሮ ለመጫወት ሲጠጋ ፡ የያዙትን መጫወቻ ጥለው ይሮጣሉ ። ወላጆች ልጆቻቸው ሲያጠፉ ፡ ዛንዛኒን ነው የምጠራልህ በማለት ልጆቻቸውን ያስፈራሩበት ጀመር ።
ይህ የማግለል ነገር በዚህ አላበቃም ። የመንደሩ ሰወች ሲያዩት ጦጣው እያሉ ይሰድቡት ፡ ጀመር ።
ብቸኛ ፍቅር የምትሰጠው ፡ እናቱ ነበረች ። ዛንዛሚ ኤሊ ፡ በእድሜ እያደገ መጥቶ ፡ ትምህርት ቤት የሚገባበት ጊዜ ደረሰ ።
እናቱ ይዛው በአካባቢው ወደሚገኘው ት/ቤት ይዛው ሄደች ።
ሆኖም የመገለሉ ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ነበርና ፡ ወደትምህርት ቤት ለመሄድ ሲሞክር ፡ ተማሪዎች ከጦጣ ጋርማ አንማርም እያሉ ሰላም ነሱት ።
....
ይህ የማግለልና የጥላቻ ሁኔታ ፡ እየባሰ ሲነጣም ፡ ሁሉን ነገር ተወላቸውና ፡ ጫካ ገባና ፡ ውሎው እዛ ሆነ ። ዛፍ ለዛፍ እየተንጠላጠለ ዱር ውሎ ይገባል ።
.......
እናትና ልጅ ፡ በዚህ ሁኔታ ፡ የመንደሩ ሰው አግልሏቸው ፡ ለአመታት ኖሩ ። ሆኖም ግን ታሪክ ሊለወጥ ግድ ሆነና ፡ ይህንን የዛንዛኒን ሁኔታ የሰማ አንድ የአፍሪማክስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወደ መንደራቸው መጥቶ ፡ የደረሰባቸውን መገለልና ፡ የድህነት ህይወታቸውን በተመለከተ ፡ አንድ ሰፊ ዶክመንተሪ ተሰርቶ በቴሌቪዥን ተላለፈ ።
ይህ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሚሊዮኖች ተመለከቱት ። ከቀናት በኋላም ዛንዛኒ ኤሊንና እናቱን ለመርዳት የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፈተ ።
.......
በአውሮፓ አሜሪካና አፍሪካ የሚገኙ ፡ ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሁሉ ፡ ለዚህ ቤተሰብ ደግነታቸውን አሳይተው ብዙ ገንዘብ ተሰበሰበ ።
........
ህይወታቸው ተቀየረ ። ዘመናዊ ቤት ተገነባላቸው ። ለእናትየው የስራ እድል ተከፈተላት ።
ያ ፡ ጦጣው እየተባለ ጫካ የሚውለው ዛንዛኒ ኤሊ ፡ ለአመታት አብራው ያረጀችውን አሮጌ ልብስ ጣለ ። በደርዘን የሚቆጠሩ ዘመናዊ ልብሶችና ጫማዎች እየቀያየረ የሚለብስ ፡ ዘናጭ ሰው ሆነ ።
ትምህርት ቤት ገባ ። አስጠኚ ተቀጠረለት ። ትምህርት ቤት የሚሄደው በሹፌር ነው ። አሁን ያ የድሮው ማግለል የለም ።
የመንደሩ ልጆች ፡ ብስክሌት እንዲያስነዳቸው የሚከቡት ። ከሱ ጋር ለመጫወት በልጆች የሚከበብ ሰው ሆኗል .
ይህን በተመለከተ እናትየው ስትናገር ፡ ፈጣሪ አንድ ቀን ታሪካችንን እንደሚለውጠው አምን ነበር ብላለች ።
.......
ደጋግና ፡ መልካም አሳቢ ሰወች እስካሉ ድረስ ተባብረው የማይቀይሩት ነገር የለም ።
©በዋሲሁን ተስፋዬ
BY #ስለ_ፍቅር (sele fkr)❤️

Share with your friend now:
tgoop.com/fker12/1779