tgoop.com/fker12/1784
Last Update:
[አንድ ግጥም ፃፊ]
ዓይን ያልመረመረው፣
ጆሮ ያልቆጠረው፣
ምላስ ያልነካካው፣
እጅ አልፎ ያልለካው፣
ከቆዳ ዝላይ ሂያጅ፣
አንድ ግጥም ፃፊ፤
ገሎ ማዳን ልመጅ፣
ከእይታ ግዘፊ፣
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።
ሰጠሁሽ ዋርካውን፣ ለቀለም ውቀጭው
ጥላው አይምሽበት፣ ማልደሽ አስቆርጭው
እጄን በሴት አንገት፣ የቆየ እንዳያየው
ልቤን እንደ በካር፣ ቀይ ደም እለቢው።
ሁለት ቀለም አለሽ፣
የዋርካ ለነጩ፣ የልቤ ቀይ ደማቅ
ሁለት ጀብዱ ሰራሽ፣
ጎንደር እጅ ሰጠሽ፣ ጃንተከል እስኪደርቅ
በቃ አሁን እረፊ፣
እስኪ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።
አሁን አየ አሞራ፣ ሟቿን ገዳይ አለ
አሁን ዞረ ንስር፣ ግዳይ ተቀበለ
"ዋ ጀግና ዋ ገዳይ
እስኪ አዝልቋት ትታይ
ሽኝቷ እስከነፍሱ፣ ባሩዷ የቀለም"
ይሸለል ይፎከር፣ ይንገሩልሽ 'ላለም።
በቃ አሁን እረፊ፣
አንድ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ
ቃላት ያከንፋሉ፣ ቃላት ይሰብራሉ
ሆሄያት ያናግራሉ፣ሆሄያት ይቀብራሉ
ህመምን አስታመው፣ ፍቅርን እስኪያበቃ
ታምሚያለሁ መሰል፣ ወደቅኩኝ እንደ እቃ
እጄን ትራስ ውሰጅ፣ ወንድነቴ አበቃ።
©ክፍሌ
#Share
┄┄┉┉✽»🌺✿»🌺✽┉┉┄┄
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fker12 @fker12
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
BY #ስለ_ፍቅር (sele fkr)❤️

Share with your friend now:
tgoop.com/fker12/1784