tgoop.com/fker12/1786
Last Update:
🕑የቤተሰብ ሰዓት
🌊 አንድ ነገር ልንሞክር ነው ። አይምሯችሁ ላይ የሚፈጠረውን ተዓምር በማየት ፣ እናንተ እራሳችሁ ምን እንደጠቀማችሁ ትነግሩኛላችሁ! The power of Now - approach ነው የምንጠቀመው!
📮ብቻችሁን ብትሆኑ አሪፍ ነው ፣ በመጀመሪያ ዘና ብላችሁ ለመቀመጥ ወይ ደግሞ ጋደም ለማለት ሞክሩ!አይናችሁን ክደኑት ፣ አንደኛው እጃችሁን ልባችሁ ላይ አርጉት! ከዛን በጥልቀት መተንፈስ ጀምሩ ፣ በጆሯችሁ የሚመጡ ነገሮችን በሙሉ ስሙ! ስለምትሰሙት ነገር አታስቡ!ዝም ብላችሁ ስሙት! በጆሯችሁ ከሚመጣው ድምፅ ጋር እንዲሁ ትንፋሽ ወደ አፍንጫችሁ ሲገባ Feel አርጉት ፣ በ አፋችሁ ሲወጣም እንዲሁ የወላፈኑ ግርፋት ይሰማችሁ! በእጃችሁ የልባችሁን ትረታ አዳምጡ! ስለ ፍቅረኛችሁ አታስቡ ፣ ስለ ኑሮ አታስቡ ፣ ምንም አታስቡ ፤ ለዛ ቅፅበት ብቻ ስሜት ይኑራችሁ! በጆሯችሁ ድምፆች ሲገቡ የሰማችሁ ፤ በገላችሁ ላይ አየሩ ሲዳብሳችሁ ይሰማችሁ ፣ የልባችሁ ትርታ በእጃችሁ ይሰማችሁ ፣ ትንፋሻችሁ ሲገባ ሲወጣ ይሰማችሁ! ሌላ ምንም አታስቡ ፣ የነገርኳችሁን ስሜቶች ብቻ አዳምጡ! ይሄን ማረጋችሁ ሞኝነት አደለም ፣ የሚፈጠረውን ተዓምር ታያላችሁ ፣ የሩቅ ምስራቅ መነኩሴም ላረጋችሁ አደለም ፣በሳይንስ የተረጋገጠ Mindfulness State ነው! ለ 5 ደቂቃ ብቻ አድርጉት! ከዛን የተሰማችሁን መታችሁ ከስር Comment ላይ ትነግሩኛላችሁ! ከመጀመራችሁ በፊት ለ5 Minute የሚሆን Alarm ሙሉ ፣ ከዛ ጀምሩ! አሁኑኑ ሞክሩት ✅
#Share
┄┄┉┉✽»🌺✿»🌺✽┉┉┄┄
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fker12 @fker12
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
BY #ስለ_ፍቅር (sele fkr)❤️

Share with your friend now:
tgoop.com/fker12/1786