tgoop.com/fnoteAemro/239
Last Update:
፨፨፨፨የወራት ስያሜ፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዲ/ን ሕሊና በለጠ
ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለውን ይመልከቱ፡፡
1
የወሩ ስም - መስከረም
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሴ እና ከረም
ትርጉም - መሴ-አለፈ ፣ መሸ ፤ ከረም-ክረምት፤ ክረምት አለፈ ፣ ክረምቱ መሸ
2
የወሩ ስም - ጥቅምት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ጠቀመ
ትርጉም - ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ
3
የወሩ ስም - ኅዳር
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ
ትርጉም - አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል
4
የወሩ ስም - ታኅሳስ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀሠሠ
ትርጉም - መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን ያመለክታል ፤ ሰብዐ ሰገል በታኅሳስ ወር የተወለደውን ጌታችንን ማሰሳቸውን ፣ መፈለጋቸውንም ያመለክታል።
5
የወሩ ስም - ጥር
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ነጠረ ፣ አጥረየ
ትርጉም - ነጠረ - ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል ፤ አጥረየ - ገዛ (ከብቱም ምርቱም የሚሸጥበት የሚገዛበት ወቅት)
6
የወሩ ስም - የካቲት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ከተተ ፣ ከቲት
ትርጉም - መክተቻ (እኅልን ወደ ጎተራ)
7
የወሩ ስም - መጋቢት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መገበ
ትርጉም - በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት)
8
የወሩ ስም - ሚያዝያ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሐዘ
ትርጉም - ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ)
9
የወሩ ስም - ግንቦት
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ገነበ
ትርጉም - ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል)
10
የወሩ ስም - ሰኔ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሰነየ
ትርጉም - አማረ (አዝርዕቱ)
11
የወሩ ስም - ሐምሌ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሐመለ
ትርጉም - ለመለመ ፣ ሐመልማል ሆነ ፣ ለቀመ (ለጎመን)
12
የወሩ ስም - ነሐሴ
የግእዝ ሥርወ ቃሉ - አናሕስየ
ትርጉም - አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለል ያሳያል)
13
የወሩ ስም - ጳጉሜ
ሥርወ ቃሉ - ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ)
ትርጉም - ተጨማሪ ማለት ነው፡፡
(1.ኅብረ አትዮጵያ፤ ከቴዎድሮስ በየነ፤ አዲስ አበባ፤ 1999ዓ.ም.፤ ገጽ 16-17
2. ከሊቃውንት አስተምህሮ)
ጳጉሜ 2006 ዓ.ም.
BY ኰኲሐ ሃይማኖት
Share with your friend now:
tgoop.com/fnoteAemro/239