FNOTEAEMRO Telegram 261
ከላይ የቀጠለ .....
.....ርኩስ መንፈሶች የሰውን ልጅ ትውልድ ሕይወት ወደ ረከሰውና በኃጢአት ወደተጨማለቀው ለመለወጥ በተለያዩ መንገዶች በሥጋዊ ድክመቱ በመዝለቅ መንፈሳዊ ሕልውናውን ለዘመናት ተፈታትነውታል፡፡ ለአዳምና ለሔዋን የተሰጣቸው የበረከትና የጸጋ ማኅተም ውስጥ የተሰጠንን ታላቅ ረድኤተ-ቡራኬ ስጦታን ቀልብሰው ሥጋን በማርከስ እግዚአብሔር የተቀደሰበትና ስሙ የተጠራበት ሰማያዊ አኗኗር ከሰውነት እና ቤታችን አርቀው ዘባተሎ ኑሮን እንድንኖር የጽልመት መልአክት ይፋለሙናል፡፡ በመሆኑም አመንዝራነትና ሴሰኝነት ብዙዎቻችን ከማይታዩ ተጽዕኖዋቸው ግን ከሚታይ ርኩሳን መናፍስት የኃጢአት ግብር አስፈጻሚነት ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ሰዎች በሞራላዊ የሥነ-ምግባር መዛነፍና መበላሸት ወይም በዘመኑ አመጣጥ የሚላከክ የአጉል ዘመናዊነት ጊዜ የመዝቀጥ ውጤት ብቻ አድርገነው ፈዘን ተቀምጠናል፡፡

+++
በተሰወሩ የመናፍስት ወጥመድ ሥር የመግባት አንደኛው ገጽታ፤ በወሲብ ፊልሞችና ምስሎች የመለከፍ እድል ውስጥ ለመገኘት፤ በአንዳንዶች ላይ ልክ እንደተፈጥሮ አጋጣሚ የተለመደ ሁነት አስመስሎ በሕሊና ውስጥ አሊያ በሌሎች ሰዎች ግፊት እያሳመነ እንዲመለከቱት በማለማመድ እንደ ሱስ እንዲቆራኛቸው የአእምሮ ወሳኝነትን ይቆጣጠራል፡፡ አንዴ እንዲመለከቱት አጋጣሚና ሁኔታው ከተመቻቸ፤ መናፍስቱ ከውስጥም ከውጪም ሆነው በመዋረስ፤ የሰው ልጆች ከተፈጥሮና ከእምነትም ምግባር የወጣ የጋጠወጥነትና የእንስሳት ጠባይ የሚንጸባረቅበት አረማዊ ምግባር እንደሆነ በልቦና ቢረዱም፤ በፍትወት እያቃጠለ በስሜት እንዲነዱ ሕሊናን እየተጫነ እንዲለከፉበት ያስገድዳል፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥም ሦስት ደረጃዎችን ያሳልፋሉ፦
  ➊• በምናብ ውስጥ የሚያውቁትን ወይም የማያውቁትን ሰው ምስል እየሳለ የወሲብ ስሜትን ይቀሰቅስባቸዋል፡፡ ወይም ከዚህ በፊት ያዩትን የወሲብ ፊልም ደግሞ ከውስጥ ያሳያቸዋል፡፡
  ➋• ከሕሊና ውስጥ ሆኖ እንደግል አሳብ እያስመሰለ ልብ ላይ የሱሰኝነቱን አዚማዊ ኃይል ስለሚጽፈው፤ ውስጣዊ ውጊያውን በተፈጥሮ ስሜት ወስዋሽነት በኩል ገፋፍቶ ገፋፍቶ በመጨረሻም እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል፡፡
  ➌• ተመልክተው ራሳቸውን በማርካትም ሲጨርሱ ወደ ልቦናቸው በመመለስ 'ምን ነካኝ' እያሉ በራሳቸው እንዲበሳጩና እንዲሸማቀቁ እያደረገ ከውስጥ ኃጢአተኛ እንደሆኑ እየደሰኮረ ከእግዚአብሔር እንዲርቁ መንገዶችን ያመቻቻል፡፡
+++

 ✞ መናፍስት እንዴት በወሲብ ፊልም በኩል ይዋረሳሉ? ✞
1) ቡዳ በመሆን
ከላይ ለመግለጽ እንደምከርኩት የወሲብ ፊልሞች የጀርባ አጥንት የሆኑት መናፍስታዊ ድርጅቶች የጥፋት መናፍስቱን ለራሳቸው የተንኮል ሥራና የአመፃ ስልት ስለሚጠቀሙባቸው፤ ከኖህ ዘመን አንስቶ የነበሩት ልቡሳነ ሥጋ መናፍስት-የኔፍሊም ሠራዊት ዳግም ከጥፋት ውኃ በኋላ በድጋሚ ወደ ሰው ልጆች ትውልድ ዘልቀው የሚገቡበትን ዕድል ስላገኙ እነዚህንና የዝሙት መናፍስት እንደ ሩሃንያ አባድ የሚባሉ የጽልመት መልአክትን በግብርና በተለያየ ጭዳ በመሳብ፤ በጥንቃቄ እንደ መደበኛ ፊልም ድርሰት አዘጋጅተው በሚለቁት የወሲብ ፊልምና ምስሎች ውስጥ መናፍስቱን አዚማዊ ቡዳ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል፡፡ በዓይን በመመልከት ብቻ በቀጥታ ውስጣዊ ሕይወትን እንዲቆጣጠሩም ተደርገው ስለሚላኩ፤ መናፍስቱ ቡዳ በመሆን የወሲብ ፊልሙን የሚያየውን ሰው ከውጪ ወደ ውስጡ ይመለከቱታል፡፡ እነዚህ ርኩሳን መናፍስት የሰው ልጆችን ሕይወት ለመያዝና በዝግታ ለመቆጣጠር የሚፈልጉት አንድ ፊልም አሊያም ምስል ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች በመጀመሪያ የወሲብ ምስሎችን ያዩበት ቀንን እስከተገኙበት ዕለተ ቀናቸው እየረገሙና እየተበሳጩ መፍትሔ ባጣ አኗኗር እየዋተቱ ታስረው ታስረው ተቀምጠዋል፡፡

2) ቀድሞ ውስጥ ባለ መንፈስ አዚም በመሆን

ከውስጥ ያደፈጠ ማንኛውም አይነት ርኩስ ኃይል ሲገኝ፤ ከውጪ በምናስገባው መረጃ መሠረት ላይ እየተመረኮዘ፤ የማጥፋትና ወደ መሰነካኪያው ጎዳና የሚመራ ዘዴንና ስልትን በጥንቃቄ እየቀየሰ፤ ግዜያቸው፣ ኑሮአቸው፣ ሕሊናቸው፣ እፎይታቸው የሚያለቅስ ሰዎችን እየጨመረ፤ ወደ ተስፋ ማጣትና የብስጭት አኗኗር ከማማረር ሕይወት ጋር እያንደረደረ ለስቃይና ለመከራ የተፈጠርን እስክንመስል ድረስ ይፈትነናል፡፡፡

አንደኛው ከውጪ ወደ ውስጥ የምናስገባው መረጃ ታዲያ፥ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ጽሑፍ፣ ንግግርና የመሳሰሉትን ነው፡፡ እነዚህ መረጃዎች ለኃጢአት ግብር መንስኤ መሆን የሚችሉ ከሆነ ያደፈጠው ጠላት ይጠቀምባቸዋል፡፡ ግለ ሩካቤ ሥጋንም እንድንወድቅበት የሚያደርጉት መንሸራተቻዎች እነዚሁ የወሲብ ፊልሞች፣ ሙዚቃዎች፣ ጽሑፎችና መሰል መረጃዎች ናቸው፡፡
ከሠለጠኑ አገራት በከፍተኛ ግፊትና ፍጥነት እየተንሰራፋ የመጣው የወሲብ ፊልሞችና መልእክቶች ዛሬ በአብዛኛው ወጣቶች ሥልክ ውስጥ ተስግስገው፤ እንደ አንድ የእውቀትና የመዝናኛ ክፍል በመታየት የስሜት ማብረጃ እየሆኑ ውስጣዊ ማንነታችንን እየበሉት፤ በውጪ ግን እየሳቅንና እየተጫወትን የምናስመስል ፍጥረቶች ሲያደርጉን ማስተዋል ተሳነን፡፡ የሚገርመው፥ ባለትዳሮች፣ አዛውንታንና በዕድሜ ያልደረሱ ትንንሽ ልጆችንም የሚለክፈው የወሲብ ፊልም ቁራኝነት፤ እነርሱም የእነዚህ የፈረንጅ አተላ የወሲብ ግብአቶችን እንደ ሕይወታቸው አንድ የተለመደ ክፍል ይዘውት በድብቅ ይጠቀሙበታል፡፡

አሁን እነዚህን ፊልሞችና መሰል መረጃዎች የምታይ ከሆነ፤ ከውስጥም ያለው ጠላት በምታየው ነገር ልክ የምትጠፋበትንና ቁራኛ የምትሆንበትን ችግር ይቀርጽለሃል፡፡ ኦሪት ዘዳግም 28፥
34 ላይ " ዓይኖችህም ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ።" ይላል፡፡ ምን ከምትለው የተነሣ? ዓይኖችህ ከሚያዩት የተነሣ፡፡ በእውነትም ታዲያ ከምታየው የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች የተነሣ፤ ከራስህ ጋር እየተጣላህ በግለኝነት ጸብ የምትማስን የውስጥ ዕብድ ሆነህ ትገኛለህ፡፡

3) የሚዘዋወሩ መናፍስት አጋጣሚውን ይጠቀማሉ

መጽሐፍ ቅዱስ በጴጥሮስ መልእክት በኩል << ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል >> በማለት ከባቢያችን ላይ የሚያንዣብቡ ጠላቶች እንዳሉ ቁልጭ ባለ ቃል አስቀምጦልናል፡፡ ከሩቅ ያያችኋል አይደለም የሚለው፡፡ በዙሪያችሁ ይዞራል ነው የሚለው፡፡ እነዚህ የሚያንዣብቡ መናፍስት የወሲብ ፊልሞችንና ምስሎችን በምንመለከትበት ጊዜ ወደኛ ለመምጣት በር ያገኛሉ፡፡ ምን ማለት ነው ለምሳሌ አበባ ንብን እንደሚጠራ ሁሉ ዝንብ ቆሻሻ ይስባታል፤ እንዲሁ የኃጢአት ልምምዶችና የአመፃ ድርጊቶች በአየር የሚዘዋወሩትን መናፍሰት እይታ ስለሚስብ፤ ክፉውንና የረከሰውን ምግባር በምናደርግበት ቅጽበት ውስጥ መናፍስቱ ወደ ሕይወታችን ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ያገኛሉ፡፡ ወደ ባሕሪያችን ሲቀላቀሉም መጀመሪያ ሲገቡ የተጠቀሙበትን የርኩሰት ምግባር ግብር አድርገው ስለሚቆጥሩት፤ በርኩሰት ልምምድ ውስጥ እንድንቀር ግብራቸውን ከውስጥ ሆነው በግፊትና በከፍተኛ ጫና በየጊዜው በተደጋጋሚ በመጠየቅ ከእስራታቸው እንዳንወጣ በተጽዕኖ ኃይል እጅጉን ይታገላሉ፡፡
+++
በጥልቀትና ከእግዚአብሔር አምላክ የእውነት ቃል ጋር በማያያዝ በቀጣይ በሚኖሩኝ ተከታታይ ስድስት ክፍሎች የምዳስሰውን የሚከተሉት ርዕሶች ይዤ እመለሳለሁ፡፡
➊• የወሲብ ፊልምና የስነልቦና ጉዳቱ
➋• የወሲብ ፊልም የቱን ያህል በዘመኑ ፋሽን ዘልቆ ሄደ?
➌• የወሲብ ፊልምና የመዝናኛው ኢንደስትሪ ተያያዥነት
➍• የወሲብ ፊልምና ከእምነት መሸሽ
➎• የወሲብ ፊልም ለአስገድዶ መድፈር ያለው ተጽዕኖ
➏• ከወሲብ ፊልም ጥገኝነት

tgoop.com/fnoteAemro/261
Create:
Last Update:

BY ኰኲሐ ሃይማኖት

Share with your friend now:
tgoop.com/fnoteAemro/261

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Members can post their voice notes of themselves screaming. Interestingly, the group doesn’t allow to post anything else which might lead to an instant ban. As of now, there are more than 330 members in the group. “Hey degen, are you stressed? Just let it all out,” he wrote, along with a link to join the group. More>> In 2018, Telegram’s audience reached 200 million people, with 500,000 new users joining the messenger every day. It was launched for iOS on 14 August 2013 and Android on 20 October 2013. Image: Telegram.
from us

Telegram ኰኲሐ ሃይማኖት
FROM American