tgoop.com/fnoteAemro/295
Last Update:
አንዲት በትዳሯ በባሏ ሐይለኛነት ሞገደኛነት ትእግስት አልባነት የተጨነቀችና የተማረረች
ሴት ወደ ንስሐ አባቷ ሔዳ እያለቀሰች "አባቴ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ባላውቅም አሁንስ
በቃኝ ከዚህ ሰውጋር መኖር አልችልም "ስትል ትናገራቸዋለች።
ንስሐ አባቷም እንዲህ ሲሉ ይመክሯታል ። "ልጄ በአንድ አፍ ውስጥ የሚኖሩትን ጥርስንና
ምላስን አስታውሺ። እነዚህ አካላት ተፈጥሮአቸው የተለያየ ነው። ጥርስ ነጭ ነው ምላስ
ቀይ ናት። ጥርስ ጠንካራ ስለታም ነው ምላስ በጣም ለስላሳ ናት። አፍ ሲከፈትላት ምላስ
ትወጣለች። ሲከደን በገዛ ጎረቤቷ ላለመጎዳት ትሸሻለች። ጥርስ ያደማውን እጅ ምላስ
ትልስለታለች። ጥርስ ሲያኝክ ምላስ ታርስለታለች። የፊት ጥርስ ማኘክ ሲከብደው ወደ መንጋጋው እህሉን በመውሰድ ትረዳዋለች።
ግን አንድ ቤት ይኖራሉ። እናንተም መልካችሁ
አቅማችሁ ጸባያችሁ የተለያየ አንዳችሁ ስለታም አንዳችሁ ለስላሳ ብትሆኑም አብራችሁ
እንደ ምላስና ጥርስ ተረዳድታችሁ ተቻችላችሁ መኖር ይገባችኋል። ሐይለኛና ትሁት ሰው
አንድ ቤት አይኖርም ያለው ማነው? ሥጋችንና ነፍሳችን እኮ ጦርነት ላይ ናቸው ሥጋ ልብላ
ልጠጣ ልጨፍር ሲል ነፍስ ደግሞ ልጹም ልስገድ ልዘምር ይላል። እንደውም ሐዋሪያው
ቅዱስ ጳውሎስ ነፍሴ በሥጋዬ ላይ ሥጋዬም በነፍሴ ላይ ይቀዋወማሉ። ይላል
በዚህ ምድር ላይ አንዳቸው አንዳቸውን እየተቀዋወሙ አንዳቸው ያለ አንዳቸው መኖር
አይችሉምና አብረው ይዘልቃሉ። ባልና ሚስትም አንድ አምሳል አንድ አካል ናቸው እስከተባሉ ድረስ ስጋ ያለ ነፍስ ነፍስ ያለ ስጋ እንደማይኖሩና እንደማይለያዪ ሊለያዪ አይገባቸውም።
ሞት የሚባለውም የነፍስ ከስጋ መለየት ነው።ባልና ሚስትም አንዳቸው ካንዳቸው የተለያዩ እለት ሁለቱም እንደ ሞቱ ነው የሚቆጠሩት
ልቦና ግዥ ልጄ ስጋችንና ነፍሳችን ሁልጊዜ ጦርነት ላይ ቢሆኑም እስከ እለተ ሞታችን
እንደማይለያዩት ሁሉ እኛም መቀዋወማችንን ለመለያየት አናድርገው።
መለያየት ጥል ክርክር የሰይጣን ነው። ገላትያ 5:7 ባይሆን መልካም የሆነው እንዲያሸንፍ እድል
እንስጠው።" በማለት መክረው ሸኟት።
ያስተማረን የገሰጸን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። እናንተስ ምን ተማራችሁ?
BY ኰኲሐ ሃይማኖት
Share with your friend now:
tgoop.com/fnoteAemro/295