FNOTEAEMRO Telegram 355
‹‹ምሁራን ምርጥ ዘር ላይ መመራመር ሲያቅታቸው ሰውን በዘር ያባላሉ››

🎤መጋቢ ሀዲስ እሽቱ አለማየሁ

በቀደዱልን መፍሰስ የለብንም። እኛ ውሃ አይደለንም። እኛ ሰዎች ነን፤ ልባዊነት (አዋቂነት)
በውስጣችን መኖር አለበት። አዋቂነት ማለት ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ ባዮሎጂ ወይም አቋቋም፣
ድጓ፣ ቁርዓን መማር ማለት አይደለም። ይሄ ይሄ ከላይ የሚጨመር ነው። ምክንያቱም
አንዳንድ ጊዜ ማንበብ ያቋረጡ ሰዎች ንግግር የሚያልቅባቸው የተቀባው ድንጋይ ቀለሙ
ስለሚለቅ ነው።
አንዳንድ ሕንፃ ዝናብ በጣም ሲበዛበት ቀለሙ ይገፋል፤ ቀለሙ ሲለቅ ድንጋዩ ይወጣል።
ማንበብ ስናቆም ወደቀደመ ነገራችን ነው የምንመለሰው፤ ምክንያቱም ርሃብ እንጂ
ባህሪያችን ዕውቀት ባህሪያችን አይደለም። ከውስጥ የተቀባ ቀለም ማንበብ ስናቆም ቀለሙ
ይለቃል። ለምሳሌ ኮምፒውተር ሳይንስ ላይ የተመራመረ ሰው 15 ዓመት ጎጃም ወይም
ወለጋ ከርሞ ቢመጣ ‹‹ኮምፒውተር ምንድነው›› ሊል ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ እኮ የሚገጥመን ነገር ዲግሪው ቤቱ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ዕውቀቱ ግን
ጭንቅላቱ ውስጥ የለም። ዲግሪያቸውን ‹‹እዚህ ስመረቅ ነው፤ ከዚህ ቦታ ያገኘሁት ነው››
ይላሉ፤ ዕውቀቱ ግን ከውስጣቸው የለም። ዲግሪው ግድግዳ ላይ ቢሰቀልም ጭንቅላቱ
ውስጥ ያለው ዕውቀት ግን በየጊዜው ማሞቅ ያስፈልገዋል።
አባቶቻችን ዓድዋ ላይ እንደዚያ ተግባብተው፣ አርቀው አስበው፣ ጥቁር አፍሪካውያን
የሚኮሩበትን የጀግንነት መልስ የሰጡ በልብም በጉልበትም ሲመልሱ የ21ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን እንዴት ምን ነካው? ‹‹ምን አገባህ!›› ማለት እንዴት አይችልም?
አባ መላ(ፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ) አንድ ፈረንጅ መጥቶ ሰገሌ(ሰሜን ሸዋ
ውስጥ ያለ) የወሎና የሸዋ ነገሥታት ተዋግተው ነበር። ነገር ካለፈ በኋላ አንድ ጣሊያን
መጥቶ ‹‹እናንተ የሸዋ ሰዎች እኮ እነዚህን ወሎዎችን ጉድ ሠራችኋቸው!›› አላቸው፤ እሱ
ጠብ ለመጫር ብሎ እንጂ አስቦበት አይደለም። ‹‹የወንድማማቾችን ስትል ለምን
የዓድዋውን አልነግርህም›› አሉት አባ መላ።
እሱ የነገራቸው የሸዋውንና የወሎውን ነው፤ መጋጨት ደግሞ ያኔም የነበረ ነው። አሁን
ሰሞኑን እየሰማሁ ነው፤ እገሌ የሚባለው ክልል ልሁን አለ የሚባል ነው። እነዚህ ዛሬ ክልል
እንሁን ክልል እንሁን እያሉ የሚጠይቁ የዛሬ ሰባት ዓመት ዕድሜ ሰጥቶት ያየ መከለያ
ይቸግራቸዋል። እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ መከለያ ይቸግራቸዋል። ሀገር እንደሹራብ
በዘዴ የተሠራ ነው። አንዱ ክር ሲመዘዝ ሁሉም ይመዘዛል። እዚህ አገር የወሰን ጥያቄ
የሌለበት የለም።
በአማራውና በትግራይ አለ፣ በኦሮሞና በሶማሌ አለ፤ እንደገና ደግሞ ተለጥጦ በአማራና
በአማራ መካከል አለ። እሱ ነው እኔ የሚገርመኝ! በኦሮሞና በኦሮሞ፣ በወለጋና በወለጋ
መካከል ይቀጥላል ገና! በሶማሌና በሶማሌ መካከል ይደረጋል። ጠብ የሆነ ቦታ ላይ
ካልተገደባችሁት ሰውነታችሁን ያበሰብሰዋል።
ይሄን ጥላቻ አሁን መገደብ ካልቻልን በጣም እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ አትራፊ የለም።
ልዩነቱ አየለ ሰኞ ይጎዳል፣ ከበደ ማክሰኞ፣ ሥዩም ረቡዕ፣ ተሾመ ሐሙስ፣ እስከ ዕሁድ ድረስ
ሁሉም ተጎድተው ጨርሰው ለቅሶ ደራሽም አይገኝም። ይሄንን እርግጠኛ ሆኜ ነው ምናገረው፣
ነብይ መሆን አያስፈልግም።
ወጣቶች በተለይ፤ አዲስ ሃሳብ ምታመነጩ ወጣቶች፤ ይሄን የተከበረ ጭንቅላት፣
እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ጭንቅላት፣ ማፍረስም መገንባትም የሚችለውን
ጭንቅላት እስኪ ለበጎ እናውለው!
107 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመስርተዋል እዚህ አገር፤ አሁንም ግን ፈረንጆቹ በበሬ
እንደሚታረስ ለማየት ሙዚየም ገብተው ነው የሚያገኙት፤ እኛ አገር ግን ዛሬም በበሬ
ይታረሳል። ከአንድ ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቀ ምሁር ገበሬን ወክያለሁ ብሎ ገበሬውን
ሲያፈናቅል ከገበሬው ያነሰ ሰው መሆኑን ያሳያል። እንዲያውም እዚህ አገር ገበሬ ውሎ
ይግባ! ምሁራኑ ምን አመጡ?
ምሁራኑ ምርጥ ዘር ላይ መመራመር ሲያቅታውቸው ሰውን በዘር ማባላት ተያያዙት! ገበሬው
እንዲያውም ምርጥ ዘር እየዘራ ሠርቶ እያበላ ነው። በትግራይ ብትሄዱ፣ በአማራ ብትሄዱ
መሬቱ የተበላ ነው፤ ከዚያ ከድንጋዩ ላይ ዘርቶ ግን፣ 24 ሰዓት እየሠራ ከጀንበሯ ጋር
ሽቅድምድም ነው። ማታ ሲተኛ አመስግኖ ነው። ‹‹ጌታዬ ያለ እኔ ማንን ፈጥረሃል?›› ብሎ
ነው። ሰው ጨረቃ ላይ እንደወጣ አልሰማም፤ ኧረ እንኳን ያልሰማ! እኛም ሰምተን ምንም
አልተጠቀምን፤ እብደት ነው ያተረፍንነው!
በዚህ ዘመን የማን አድናቂ ነህ ብትሉኝ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች
አድናቂ ነኝ፤ ፖለቲከኞቹን ንቁባቸው! በጣም ነው የገረመኝ። እኔ በ1998 ዓ.ም ጥቅምት ወር
ላይ ቅንጂት የሚባል ፓርቲ አሸንፎ ኢህአዴግ ያልተዘጋጀበት ሽንፈት፤ ቅንጂትም
ያልተዘጋጀበት ድል አጋጥሟቸው ሁለቱም ሰክረው ነበር። የቅንጅት የዚያን ጊዜ ችግር ዱብ
ዕዳ ድል ወረደበት! ለድልም ለሽንፈትም መዘጋጀት ያስፈልጋል።

tgoop.com/fnoteAemro/355
Create:
Last Update:

BY ኰኲሐ ሃይማኖት

Share with your friend now:
tgoop.com/fnoteAemro/355

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

How to create a business channel on Telegram? (Tutorial) While some crypto traders move toward screaming as a coping mechanism, many mental health experts have argued that “scream therapy” is pseudoscience. Scientific research or no, it obviously feels good. While the character limit is 255, try to fit into 200 characters. This way, users will be able to take in your text fast and efficiently. Reveal the essence of your channel and provide contact information. For example, you can add a bot name, link to your pricing plans, etc. “Hey degen, are you stressed? Just let it all out,” he wrote, along with a link to join the group. You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether.
from us

Telegram ኰኲሐ ሃይማኖት
FROM American