tgoop.com/fnoteAemro/369
Create:
Last Update:
Last Update:
በሰማይ ሰልፍ ሆነ ውጊያው ተጀመረ
በሚከኤል ነገድ ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በአይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
ዳቢሎስ አልቻለም ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳለም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው አይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን አይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ
ቅዱስ ሚካኤል ከሚመጣብን ክፉ ነገር ይጠብቀን🙏
BY ኰኲሐ ሃይማኖት

Share with your friend now:
tgoop.com/fnoteAemro/369