Telegram Web
በዚህ ሙቅ ከተማ
በዚህ ደማቅ መንገድ
ሺ አምፖል በበራበት
ፀሐይ ቀንና ሌት ፥ በማትጠልቅበት
ለሰው የማይታይ
አለ ብቸኝነት ።

አለ ብቸኝነት
በስንት እግሮች መሐል
ያደፈ ኮት ለብሶ
አይኑ ማዶ ፈዞ
የታክሲ ጥሩንባ የሚያደነቁረው
ሰው ገፍትሮት እንኳን
"ይቅርታ" የማይለው
ስሙ ፥ ማይነሳ
መኖሩ ፥ የተረሳ
ቢሞት ፥ ልብ የማይባል
አለ ብቸኝነት
እዚሁ ፥ እኛው መሐል ።

አለ ብቸኝነት
አንድ ጊዜ ተራምዶ
ብዙ ጊዜ የሚቆም
በፋሲካ በአል ፥ ብቻውን የሚጾም ።

አለ ብቸኝነት
ቢያውቀው ወይ ባያውቀው
የሚገላምጠው
(ወይ በመተያየት)
ፈገግታ 'ሚሰጠው
አንድ አይን የናፈቀው ።

አለ ብቸኝነት
ዕንባውን የዋጠ
ሳቁን የመጠጠ
ስሜቱን ያፈናት ፥ ልውጣ ባለች ቁጥር
ልቡ እንደ ድመት ሆድ ፥ ትር ትር የምትል ።

አለ ብቸኝነት
ወዴትም የማይሄድ ፥ ዝም ብሎ የሚራመድ
እንኳንስ ሰውና ፥ ልቡ ያልሆነው ዘመድ
ጭር ያለ ባይተዋር
በሰው ጎርፍ መሐል
ትንፋሹ የሚታየው
እርምጃ የሚመትር
ጠብታ የሚቆጥር
ወዴትም ሳንርቅ ፥ እዚሁ አፍንጫችን
እዚሁ ልባችን ስር
አለ ብቸኝነት ።

By HAB HD

@getem
@getem
@paappii
[የሌሊት ራዕይ....]

🌟
አሮጊት ኮከቦች....
እንደ ፍም አብርተው....
ከሌሊቱ ሰማይ— ረከቦት ሰርተው ፤
(ነጭ ጉም — ስኒ ዘርግተው ፤)
በጨለማ በራድ — በድቅድቅ ጀበና
(ከሩቅ ተጠራርተው ይሰበሰቡና....)
ያፈላሉ — ቡና ።
🌟
በስብሰባው መሀል....
አቦል እየጠጡ — ጨረቃን ያሟታል ፤
(እንደዚህ ይሏታል....)
“አብራን እየኖረች እኛን ያልመሰለች
ከህብረት ከቡድን የተገነጠለች
ይቺ ' ቅርፀ ጥፉ ' የተድቦለቦለች....!”

🌒
እሷም ትሰማለች...
(ጎረቤት አይደለች?!)
መልኳ ያስጠላታል ፤
እንደ`ነሱ ሆና...
(ያፈሉትን ቡና...)
መጠጣት ይምራታል ።

(ቀረብ ትላለች....)
“አምራለሁ ብላ ነው ከእኛ መለየቷ?!
እኛን ለመብለጥ ነው ገዝፋ መታየቷ?!”
(ሲሉ ትሰማለች...)
አንገት ትደፋለች ....
(ብቻዋን አይደለች!?)
ሀሜት ይሰብራታል
አንሳ ትጠፋለች ።
🌒
[በራስ መንገድ መቆም ...
የሚያኖር አይደለም ፥
መንጋ መልቀቅ የለም!
'መለየት'-- 'ማፈንገጥ' ...
በሆነበት ዓለም...
በልዩነት መኖር — መቼ ይወደዳል!?
የህላዌ ህጉ — መምሰል ያስገድዳል ።]
🌒
(እኒህ አሮጊቶች....)
ሽሙጥ ሀሜታቸው በርዶ ካላበቃ ፤
ተፈጥሮ ስሪቷን
(ልዩ ማንነቷን)
ገላዋን አውልቃ ፤
ኮከብ ትሆናለች — አንድቀን ጨረቃ ።
_
ህዳር ፳፮—፪፼፲፮ ዓ.ም
By
@Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
ለማታዉቀኝ 2 ✍️በዔደን
<unknown>
ለማታዉቀኝ 2
ገጣሚ እና አንባቢዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
ያልታደለች እናት 💔

ሳቋን ለገሰችው
መልኳን አተመችው
ሳጠግብ አጉርሳ ከዚህ አደረሰችው
አደገልኝ አለች ጦሮ ሊያሳርፈኝ
የልፋቴን ዋጋ ፈጣሪ ሊክሰኝ
.
ግና መቼ ሊሆን ከልቧ ያለመችው
በእርሱ ስትሰቃይ ዕድሜዋን ፈጀችው
ዕድሜዋን ፈጀችው!
ውጥኗን ቀጨችው!
መኖር እንዳልጓጓች ሞቷን ናፈቀችው


በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
ስንኩልኩል ተራማጅ በኃጥያት ቦይ ፈሳሽ
ቀና ብዬ ማላይ የህይወቴን ቀያሽ፤
እንደነገሩ ሂያጅ
እንዳሻኝ ወራጅ
ነጥዬ ማላውቅ ጠላት እና ወዳጅ፡
ስንፏቀቅ የምኖር ውድቀት ተንተርሼ
ዘመኔን የበላሁ
ራሴን የጎዳሁ አዳኜን ነክሼ።

የእውር ድንብር ተጓዥ ስንኩልኩል ወልካፋ
እየሄድኩ አልነበር ራሴን ላስጠፋ
ታዲያ እንዴት ተረፍኩ?
እስትንፋስን ታቀፍኩ?
መውደቂያዬን ሚያቆም መጥፊያዬን ሚያድን
ምን ነበር እኔጋ ፈዋሽ የቁም በድን?
ምንም!
ማንም!

እንዴ...
ወይ ጉዴ
ረስቼህ አልነበር ... እንዴት አስታወስከኝ
ንቀት ግፌን ትተህ እንደምን ታደግከኝ
ጥል ምርኩዝ ሲጥለኝ እንደምን ደገፍከኝ።
እንዴት ታዘዘልህ ክንፍህ እኔን ሊጋርድ
ገፍትሬህ አይደለ እንዲህ ምንገዳገድ።

ሚካኤል አባቴ
ጉዞዬ ወደ ምሬት መንገዴ ወደ ሞት
የት አግኝተህ ቀየርክ የኔን ስብር ህይወት

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
#ህመም_አሞኝ_ያውቃል!

የሚያስጨንቅ የሚከፋ
አለ ሲሉት የሚጠፋ
የለም ሲሉት አለው የሚል
ስቃይ ሲሉት ደስ ደስ የሚል
የሚያደቀኝ በስልብ ቃል
ህመም ሚሉት አሞኝ ያውቃል።

#በድኔንም_ልክ_እንደዛው!

ያወሩኝ 'ለት አልነበርኩም
ሲጠላልፉኝ አልወደኩም
አታለሉኝ በመሃል ላይ በድን በድን በሚለው ቃል
አዎን ልክ እንደዛው...በድኔንም አሞኝ ያውቃል።

#እራሴንም_ምታት_መታው!

ስንለያይ ስትጨክን በጌታ ቃል ተማምላ
ከቆምኩበት ጥላኝ ስትሄድ ስትመልሰኝ ወደኋላ
ጭንቀት ቢጤ ሲጫርብኝ አስጨፍነው ለሚቀብሩት
ራሴንም ምታት ነገር ጠጋ ብለው አወራሩት።

#ማመኔንም_እምነት_ነሳው!

"አፈቀርኩህ" ስትል "አፈቀርኩሽ" ያልኳት
"ትበልጣለህ" ስትል በጭፍን ያመንኳት
ሳወራላት ስኖር የሚቆጨኝን ቃል
ማመኔንም አሞኝ ያውቃል።

#ህይወቴንም_አሞኝ_ነበር!

አጨብጭቤ ያስጨበትኳት
ስጦታ ነው ብዬ የላኳት
የሚሰማኝ እየጫረ
ከጓድ በላይ እኔን ለኔ የመከረ
ህይወቴንም ታምሜ ነበረ።

#ህሊናዬን_ጎድቻለሁ!

ወሰንኩና ውሳኔዎች ተናገርኳት እስኪበቃት
የተጠጋት ቆሌ መንፈስ ካጠገቧ እስኪርቃት
ተናደድኩኝ ከልክ በላይ አናደድኳት ልክ እንደኔው
ህሊናዬን ጎድቻለው በንዴት ቃል እኔው ለኔው።

የድባቴ መንፈስ ሲከናነብ አካላቴን
እንባ ሚሉት ውሃ ተናንቆት ህይወቴን
ገደል ገደል ሚያስመኝ የክፉ መንፈስ ቃል
     #ተፈጥሮዬም_ታሞ_ያውቃል!



#mikiyas_feyisa

ዮኒ
     ኣታን @yonatozz

@getem
@getem
@getem
#ደህና_ሁኝ_እንግዲ

አልፈለኩም መሰናበት ቻው መባባል ተተቃቅፎ
ከባድ ስሜት አለው
ወዳጅን መሸኘት በእንባ ፅሁፍ ፅፎ

ዮኒ
     ኣታን  @yonatozz

@getem
@getem
@getem
አምላኬ


አይኖችሽ ይሉኛል እንደምትወጂኝ
አፍሽ ይነግረኛለ   እንደማትወጂኝ

ታድያ የቱን ልመን
አፍሽ አዬገፋኝ አይንሽ ሲጎትተኝ
ልብሽ ምን እንደሚል  ማወቅ ሲያዳግተኝ

ልቤን ልመን ይሆን ?
ልቤ የሚለኝን  ወደ አምላክ ቅረብ
አንድት እፁብ ለምን  ድልድይህን ጥረብ

ስትራምድ እንዳይጎዳህ  ስትሻገር ወደ እሷ
መለያዬት እንዲያከትም    ተጓዝ ወደ ነፍሷ

ከአንድ ልብ አንድ ነፍስ  እንዲያጣምርህ
ተጠጋ ወደ አላህ    ቅረብ ወደ እግዜርህ
ይለኛል

አምላኬ
ታነብልኚ  ይሆን  የአይኖቿን ሚስጥር
ሰብረህ ትገባለህ  ወደ ልቧ ቅጥር?
አምላኬ


By kerim

@getem
@getem
@getem
¹
“ግፋ” ብለኸው — እግርህን
እያፈስስከው — ላብህን
ስታሯሩጣት — ወደ ፊት...
(ስትከተላት ህልምህን ...)
አሁን ግን በቃህ — ደክሞሃል
አየሁህ መንገድ — ወድቀሃል ።

“በርታ - ተነስ” — አልልህም
“” ደግመህ ሩጥ” — አልልህም
(“ውደቅ እረፍ” — ግዴለህም ።)

♟️

ያቺን ብሩህ ጊዜ...
(ያቺን ፍፁም ደስታ....)
ሮጠህ ብታጣት፤
ወድቀህ ፋታ ስጣት ።
(ወይም ደግሞ ቆመህ
በሩቅ ተመልከታት....)
ወዴትም አትሄድም....
ክብ ነው መሮጫው.....
(ምድርስ ክብ አይደለች?!)
ት ደ ር ስ ል ሃ ለ ች — ባትደርስባትም ፤
ወደ ፊት መሄድ ነው — እርምጃ መግታትም።
---
(አትልፋ ደጋግመህ ....)
እጅ ስጥ ግዴለም — “በቃኝ” በል አንዳንዴ ፤
ተስፋ ካልቆረጡት — ይቀጠላል እንዴ ?!

♟️

[ተራራ ሲገፉ....
ወደ ላይ ሲከንፉ...
ሰማይ የፈለጉት...
መሬት ወድቆ እንደሆን
መች ያስተውሉታል !?
(ዕድሜ ይስጠው ድካም)
ሲሮጡ ያጡትን — ሲያርፉ ያገኙታል ። ]
——
²
አንተም ወዳጄ ምስኪኑ እረኛ ፤
(ፍሬ ለማውረድ....)
መዝለልህ ይብቃ....
ዛፉ ስር ተኛ ።

(መተው መልካም ነው....)
“አልቻልኩም” ማለት ያስችልልሃል ፤
(ሽቅብ ወደ ላይ ስትንጠራራ...)
ያልደረስክበት ጣፋጩ ፍሬ....
ሲበስል መሬት — ይወድቅልሃል ።

“ተነስ” — አልልህም...
“ሩጥ” — አልልህም....
“እረፍ” — ግዴለህም ።
_
@Bekalushumye
ታህሳስ ፪ — ፳፲፮ ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
( ሂጂ ... )
===================

ተራማጅ በዝቶበት ተጎድቷል ገላዬ
ሰርክ ማመላለስ መንገድ ሆኖ ማድረስ
ሰልችቷል ኑሮዬ ....

ሂጂ ሌላ ሞልቷል
ዛሬም መሻገርያ ዛሬም መንገድ ካሻሽ
እኔን ተይኝ እቱ ካልሆንኩኝ ከነአን
ፍጻሜ መድረሻሽ !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
ስንክሳር


ስቃይ በመርዛማ እሾሆቹ አንዳይወጋን
ዶልዱመው ይጠፉ ዘንድ እዬተጋን
ችግርን በፀጋ መቀበል አንፍራ
ከሽሽት ትግል ይወለዳል እና መከራ
የህይወት ድርሻችንን በመቀበል እንጋፈጠው
በትግል እና በእቢተኝነት መንፈስ ላናመልጠው
ውጣ ውረድ የበዛባትን የስንክሳር አለም
ደንብሮ ከመፈርጠጥ ቆመን እንፋለም ።


ንሸጣ ፦ ኤፒክታተስ
ገጣሚ።፦ ከሪም

@getem
@getem
@getem
¹
ፍቅርንስ ያፍቅሯት ጌቶች ....
(መውደድ በእነሱ ያምራል )
በልዑላኑ — በሀያላኑ —
በንጉሦቹ ፤
(በፈላጭ በቆራጮቹ )
ጊዜም ስልጣንም ባላቸው ፤
ሁሉን በሚቻላቸው ።

(እንደ እኔ አይደሉም እነሱ....)

የልብን መሻት ይሞላሉ ....
እንባን ማበስ ይችላሉ ....
(ለሚጠሉት ባይሆን እንኳን )
ለሚወዱት ይደርሳሉ ።

(ለምን ወደድኩሽ እኔ ግን?)

“መውደድ” (የንጉሥ ዘመድ)
በባሪያ ልብ ምን ይሰራል?
ላፈቀሩት ካልደረሱ ....
ማፍቀር ብቻ ምኑ ያምራል?

ባይሽም በእሳት መካከል
ባለጊዜ ሲያንገላታሽ
ቢሰማኝ ጩኸት እሪታሽ
አድንሽ ዘንድ ....
(አተርፍሽ ዘንድ )
አቅመቢስ ነኝ ድኩም ባሪያ
ስስ ጉልበቴ አንሶብኛል ፤
ታዲያ ....
(“ደረስኩልሽ” ማለት አቅቶኝ)
“ወደድኩሽ” ብል ያምርብኛል?

ለወደዱት አካል ለወደዱት ገላ ....
ለመድረስ የሚችል ከሌለበት አቅም
ያሳምማል እንጂ መውደድ ምን ሊጠቅም?
ካላበስኩልሽ እንባሽን
ካላከምኩት ህመምሽን
ካላተርፍኩት....
ቆሜ ካየሁት ልብሽ ሲሰበር ፤
ባልወድሽ ይሻለኝ ነበር ።

²
ፍቅርንስ ያፍቅሯት ጌቶች....
(መውደድ ያምራል በእነሱ ፤)
ቀላል ነው እንባ ማበሱ ፤
(ላፈቀሩት ሰው መድረሱ ። )

ጌታም ራሱ ሁሉን የሚችል....
(የማርያም ልጇ) የዓለም ንጉሥ ነው
ስለመውደዱ ተሰቅሎ ያልፋል ፤
ደሙን አፍስሶ ፍቅሩን ያተርፋል ፤
ሞቱ እንኳን ሚዛን ይደፋል ።

(ታውቂያለሽ ይሄንን)
የንጉሥ ነው እንጂ
የጌታ ነው እንጂ
ምንም ለውጥ የለውም
(ተዓምር አይፈጥርም ) የአንድ ባሪያ መጉደል
እኔ ብሞትልሽ አትተርፊም አይደል !?
_
By
@Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
Finally 🙏
ፈጣሪ ታላቅ ነው።
አዕጋረ ፀሓይ ዛሬ ሕትመቷን ጨርሳ ለስርጭት ጃዕፋር መፅሀፍት ተልካለች። በቅርቡም በመላው አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ትዘልቃለች።
በሂደቱ ሁሉ ከጎናችን ለነበራችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።
መልካም ንባብ

ደራሲ ሚካኤል አስጨናቂ
አሚን አሚን አሚን

እስኪ ልነሳና እንዝርቴን ላስላዉ
ምን ያቦዝነዋል ፈትሎ አዳሪ ሰዉ
እንደ ጊዜው ክፋት
እንደሰዉ ክዳት
እንደኔ አንድ መሆን
ምን ይበጀኝ ነበር አንተ ከኔ ባትሆን።
የዘመናችን ሰው ምንኛ ተጎዳ
በአፉ እየወደደ በሆዱ እየከዳ፤
እኔማ ረግሜ ምንኛ ልጎዳው
እሱም ይውደድና ያመነው ሰው ይክዳው።
አሚን አሚን እማዋየው አሚን
ጌትዬ እጄን አውዛው
እጁ የወዛ ነው ሚዜው የሚበዛው።
የወሎ ደመና አይጥልም ከየጁ
ገልግለኝ ህመሜን ከነእግዴ ልጁ።
ብሶቴ ችግሬ ገለል በል ከፊቴ
እግሬን ልዘርጋበት
አሞኛል ጉልበቴን የኮረተምኩበት።
አቤት አቤት አቤት

እማማ ዚነት🖤

@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
Digital art exhibition

“Longing for the Unknown”! 🌌
Artist Fanuel Leul


Fendika Cultural Center
Opening on July 1st at 6 PM and running until July 15th.

@seiloch
ተጋፈጥኩ መከራዬን
ተፋላምኩ ፈተናዬን
ኃይሌን ጨረስኩ እንጂ መች አገኙሁ ውጤት
እኔ አለቅኩ እንጂ መች በቃሁ ለስኬት
ሩጫዬን ገታሁ አቆምኩ ትግሌን ላፍታ
ቃኘሁ ድክመቴን የሽንፈቴን ቃታ
ለካ
ብቻዬን ነው ምጓዝ እርቃኔን ወጥቼ
መከታ ጋሻዬን ረዳቴን ትቼ
ለካ
ውልክፍክፍ ስንኩልኩል ነበር አሯሯጤ
እውር ድንብር ነበር ሚወነጨፍ ውስጤ
ለካ
በዜሮ ተባዝቷል ሙከራ ጥረቴ
አንቺን ሳልይዝ ሂጄ ድንግል እመቤቴ

አፈገፈግኩ ወደ ኋላ
ተመለስኩ ወደ ቀልቤ
ሰአሊ ለነ እያልኩ ታጠቅኩሽ በልቤ

ይኸው ነጻ ጥርጊያው
ይኸው ቀና መንገዱ
ገና ሳልጠጋው
ሲያዘቀዝቅ አየሁ  የመከራ ቀንዱ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
ሌላኛው ሊስት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ምርጥ 5 ውስጥ ያለ የክሪፕቶ ቢዝነስ ነው።

እድሎን ይሞክሩ!
https://www.tgoop.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_454803628 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
ገጣሚ ታሮስ ዓለሙ

@getem
@getem
ይድረስልኝ ላንቺ ✍️በዔደን_ታደሰ
<unknown>
ይድረስልኝ ላንቺ.........
ገጣሚ እና አንባቢ ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
ቆንጆ የዕጅ ፅሁፍና የሀረግ አሰራር ለመማር ይሄን ገፅ ይመልከቱት!

https://youtube.com/@thelotrscribe?si=lzP8Ex6WV4W9OdHv
2024/07/01 01:52:37
Back to Top
HTML Embed Code: