tgoop.com/hamreel/4233
Last Update:
ነዉ ግን ሌሎችን ሁሉ ገዝቶ ነዉ የሚንረዉ እንስሳቱን ሁሉ አራዊቱን ሁሉ አባረን እኛ ቤት ሰርተን ነዉ የምንኖረዉ ግን በጥፍር በጉልበት በኃይል አራዊት ይበልጣሉ። "ቅዱስ ጎርጎሪዎስ"ምን ይላል ለሠዉ ልጅ ጥፍር ቢሰጠዉ ኖሮ ሰዉነቱ ፀጉር ቢኖረዉ ኑሮ ልብስ ባይለብስ ኖሮ በጣም ጉልበኛ ቢሆን ኖሮ አንደኛ በዚህ ጠባያችን ጥፍር ቢኖረን እርስ በእርስ ተጨራርሰን ነበር እኮ እንኳንም አልሰጠን እግዚአብሔር። ጀካማ በመሆናችን ምክንያት እራሳችንን ፕሮፌክት ለማድረግ ብዙነገር ፈጠርን እራቁታችንን ስለሆንን ስለበረደን ሲበርደን ልብስ የማባል ነገር መጣ ጭንቅላታችንን እንድንጠቀም ነዉ እንጂ እማይሞቀን የማይበርደንሰ ፀጉር ያለን ብንሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ አይነት ልብስ ይመጣ ነበር አይመጣም። እና የሰዉ አይምሮ ዉብ አድርጎ ስለሰራዉ ያንን አይምሮ እንዲጠቀም ከሌሎች ደካማ ፍጥረት አድርጎ ፈጠረዉ አራዊትን አሸንፎ ገዝቶ በፊት ተስማምቶ ነበር የሚኖረዉ ከዉድቀት ቡኃላ ግን ይፈራቸዋል ስለዚህ እነሱ ጉልበታቸዉን ሲጠቀሙ እርሱ ጭንቅላቱን ተጠቅሞ አራዊትን አባሮ የተወሰኑትን አስቀርቶ ደግሞ ለብቻ የሆነ ቤት ዉስጥ አስቀምጦ ቅዳሜና እሁድ ልጆቹን ይዞ እየሄደ ይጎበኛል አይደል 🤔 እስኪ ገልብጣችሁ አስቡት እንስሳት አራዊት ቢሆኑ እኛን የሚጎበኙን ሰወችን አስቀምጠዉ እየመጡ ፈቶ ሲነሱ ስንገለብጠዉ ነዉጂ የሚያስቀዉ እኛነን እንደዚህ እያደረግን ያለነዉ ይሄንን ነገር ማድረግ የቻልነዉ ግን አይምሮ ስለሰጠን ነዉ እና በዙሪያዉ ያሉትን ስም ያወጣ ነበር ይላል።
🔹አራተኛዉ አዳምም በገነት መካከል ተኝቶ ነበረ አዳም በገነት እያለ ብቻዉን ነበር ግን የብቸኝነት ስሜት አልተሰማዉም ተሰማዉ የሚልም ነገር የለም ምንድነዉ እግዚአብሔር የፈጠረዉ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ ሰዉ ግን ብቻዉን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የምትመቸዉ እረዳት እንፍጠርለት አለ "ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር ሰዉ ብቻዉን ሲሆን ደስ አላለዉም።" ስለዚህ በአዳም ላይ በገነት ሳለ እንቅልፍ ጣለበት በሰመመን ላይ አደረገዉ ከጎኑ አጥንትን ወስዶ ሔዋንን ሠራ አመጣለት ሔዋን ተሰጠችዉ ማለትነዉ።
☘️👉አንድ ክርስቲያን የብቸኝነት ሕይወት እንዴት መኖር አለበት እሚለዉ ከመጀመሪያዉ ሰዉ ከአዳም አራት ነገሮችን እንማራለን ማለትነዉ። አዳም የመጀመሪያ ሩ ምንድነዉ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ አንድ ወጣት የብቼኝነት ጊዜዉን ማሳለፍ ያለበት ከእግዚአብሔር ጋር ነዉ ከሔዋን ጋር ከመሆኑ በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሳይሆኑ ከሔዋን ጋር ይሆናሉ ቀድሞ ከሔዋን ጋር የተጀመረ ነገር ብዙ ችግሮች ይፈጠራሉ ። መጀመሪያ ቅድሚያ ልንፈጠዉ የሚገባን ግንኙነት መስጠት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ነዉ ይሄን ማለት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ማለትነዉ ሰወ በሕይወቱ ሌላ አጋር ከመጨመሩ በፊት መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ ግንኙነት ምንድነዉ ስለ ኃይማኖቴ ምን አዉቄአለሁ ምን ይላል እንዲያም ቀገ"ቅዱስ ጳዉሎስ" ብቻዉን ቢሆን የተሻለ ነዉ ለማገል ገል ከሚያገባ ይልቅ መጀመሪያ ከእግዚአብ ጋር ቢሆን ይሻላል እንደ ጳዉሎስ ሀሳብማ ሰዉሁሉ ጭራሽ ባያገባ ሁልጊዜም ብቻዉን ቢሆን ደስ ይለኛል ምክንያቱም ከሚስቱ ጋር ከሆነ ሚስቱን እንደት ደስ እንደሚያሰኛት ያስባል ብቻዉን ከሆነ ግን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንደት ደስ እንደሚያሰኛት ያስባል ይላል። ያን ማድረግ ባንችል እንኳን የብቸኝነት ጊዜአችንነ ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ አለብን ። ስለዚህ ወደ እጮኝነት ሕይወት ያልገባ ሰዉ ወደ እጮነት ሕይወት ከመግባቱ በፊት የሚጠይቀዉ እራሱን መጀመሪያ መንፈሳዊ ሕይወቴ ምኑ ጋር ነዉ ያለዉ የንስኃ ሕይወቴ ምኑ ጋር ነዉ ያለዉ ሊል ያስፈልጋል። አንደኛዉ ይሄነዉ
☘️👉ሁለተኛዉ ደግሞ አዳም ስራ ይሰራ ነበር ወደ እጮነት ከመግባት በፊት ስራ መስራት ይቀድማል። እራስን መቻል ይቀድማል። የፈለገ የሀብታም ልጅ ብትሆን የፈለገ የድሎት ኑሮ ዉስጥ ብትኖር ገነት ዉስጥ አይደለም የምትኖረዉ !! አዳም ስራ ይሰራ የነበረዉ ገነት ዉስጥ ሁኖ ነዉ ገነት አሁን ምኗ ይቆፈራል ተቆፍራ ያለቀች ያማረች ነች ግን ስራ የተፈጠረዉ ጥረህ ግረህ ብላ ቡሀላ ነዉ እንጂ ስራ ግን የበፈጠረዉ ከዉድቀት በፊት ነዉ ገነትንም ይሰራ ነበር ይላል። እንኳን እዚህ የተበላሸ አለም ላይ ሁነን ገነት ላይም ስራ ይሰራል። እግዚአብሔር መጀመሪያ የፈጠረዉ እንዲያዉም ስራን ነዉ ይባላል እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ይሄ እራሱ ስራ ነዉ ስራዉን ሰርቶ ሲጨርስ ሰዉን ፈጠረ እና ሁለተኛዉ እራስን መቻል ያስፈልጋል ነዉ በአጭሩ።
☘️👉ሶስተኛዉ በዙሪያዉ ላሉ እንስሳት ስም ያወጣ ነበረ ስለዚህ እኛም በዙሪያችን ላሉ ለድመት ለዉሻ ምናምን ስም ማዉጣት ማለት አይደለም ያጊዜ አልፏል ስም ወጥቶላቸዉ አልፏል ግን ሪዕዮተ አለም የምንለዉ ዙሪያችንን አይተን መጨረስ ስለ አለም ያለን አመለካከት ምንድነዉ? በዙሪያችን ያሉ ሰወችን በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን አመለካከታችንንና አስተሳሰባችንን ዲፋይን አድርገን መጨረስ አለብን እሩቅ ሳንሄድ ለምሳሌ ጓደኞች ይኖራሉ ማነዉ ጓደኛችን ከማን ጋር ነዉ የምንዉለዉ ምንድነዉ የምንወደዉ ምንድነዉ የምንጠላዉ ይሄንን ሰዉ መጨረስ አለበት ሌላሰዉ ጨምሮ ከማሰቃየቱ በፊት ብቻዉን በነበረ ስአት መጨረስ አለበት አዳም በዙሪያዉ ያሉት እንስሳት ናቸዉ ለእንስሳት ስም አወጣ እኛ ደግሞ ስም የምናወጣላቸዉ ብዙ የሕይወት ፕሪን ስፒሎች አሉ ጓደኞችሰ ሊኖሩን ይችላሉ ሴቶች የወንድ ጓደኛ የሴት ጓደኛ ወንዶችም የወንድም የሴትም ጓደኛ ይኖሩናል እና ማነዉ ጓደኛየ ብሎ መምረጥ አለበት የእጮኝነቱን ሳይሆን ዝምብሎ ጓደኝነቱን ማለትነዉ። ወዳጆቻችን ምን አይነት ናቸዉ አንዳዴ ሴቶች ከወንድ ጋር ወንዶች ከሴት ጋር ጓደኛ ሊሆኑ ይችላሉ ምንድናችሁ ሲባሉ አይ እንዲሁ ጓደኛ የሚሉ ከልክ በላይ የሆኑ አሉ አሁን እንደዉ እጮኛ ብትሆኑ ከዚህ በላይ ምን ታደርጋላችሁ የሚያስብሉ ማለትነዉ። ከመጠን በላይ የሆነ መቀራረብ አካላዊ ቅርርብ ይሄ ልክ አይደለም አይ ወንድሜ ነዉ =ልክነዉ ወንድም ነዉ ግን "ወንድ ነዉ" =እህት ናት ግን "ሴት ናት" ስለዚህ አይ እኔ ዉስጤ ንፁሕነዉ ምንም አላሰብኩም ልንል እንችላለን ግን ሌላኛዉ ሰዉ ምን እንደሚያስ አናዉቅም ። ብዙ ሰወች ሳያስቡት እንደዚህ አይነት ጓደኝነት ዉስጥ ገብተዉ ወደ ማይሆን መስመር ሂደዉ ለቁም ነገር መብቃት አንድ ነገር ነዉ ብቻ ሳይፈልጉት የሚገቡበት ጓደኝነት አለ። እና እራሳችንን ልናምነዉ እንችላለን ልናዘዉ እንችላለን ግን ስጋችንን ማዘዝ አንችልም። ፈተና ዉስጥ እራስን አለመክተት ነዉ እና ለዙሪያዉ ስም አዉጥቶ መጨረስ አለብን በብዙ ጉዳዮች ላይ ያለንን አቋም የምንጨርስበት የምናሳልፍበት ጊዜነዉ። የብቸኝነተ ጊዜ።
☘️👉የመጨረሻዉ አዳም ተኝቶ ነበር ይላል አዳም የብቸኝነት ስሜት አልተሰማዉም አዳም ተኝቶ ፈጣሪየ ሆይ እንደዉ በቃ ብቻየን ታስቀረኝ እያለ አይደለም ሔዋንን ያገኘዉ አዳም በገነት መሬት ላይ ተኝቶ ነበር ። እግዚአብሔር ያዘጋጅለት ነበር ተኝቶ ነበር ማለት እኛ ጨርሰን እንተኛ ማለት አይደለም መተኛት ማለት ሀሳቡን መተዉ መጣል ማለትነዉ። ስለዚህ አሳባችንን ለእግዚአብሔር መተዉ ነዉ አዳም ከመጠን በላይ ማነን ነዉ የማገባዉ እያለ ስለተጨነቀ አይደለም ልባችሁ ስለትዳር በማሰብ እንዳይከብድl
BY የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/hamreel/4233