tgoop.com/hamreel/4236
Last Update:
አንዲት ሴት አይቶ ሌላቀን ነድርጎት የማያቀዉን ዲንጋይ ከማንሳት የሚተካከል ብዙ የሆነ ነገር ሊያደርግ ይችላል ያዕቆብ ግን እንደዛ አድርጎ ከመወሱ ያየዉን ፍዳ 14 አመት ተገዛ ጣኦት አመለከችበት የአባቷን ጣኦት ይዛ መጣች ሰዉ ሳያት የሆነ ነገር ተሰማኝ ብሎ የሆነ ነገር ሊክድ ይችላል። ያዕቆብ ራሔልን ማፍቀሩ ያጠፋዉ ጥፋት አንድ ነዉ ጥፋቱ ራሔልን ካየበት ከወደደበት ስአት አንስቶ እስካገባት ድረስ ያለዉ እግዚአብሔር ሰሚለዉ ስም የለም ። እሷን ሲያይ እግዚአብሔር እረሳዉ እግዚአብሔርን ካስረሳ ስጋዊ ፍቅር አደጋ አለዉ ማለትነዉ። ስለዛህ እግዚአብሔር እጁ ምኑ ላይ ነዉ ካላችሁ ፈጥሮናል ለአንተ የምትሆነ አዘጋጅቷል ወይ አወ አዘጋጅቷል እገሊት ብሎ አላዘጋጀም መፍጠሩ እራሱ ማዘጋጀት ነዉ ሁተኛ ሊያገናኝህ ይችላል አንድ ሰፈር ሆነዉ ሳይገናኙ የሚሞቱ ሰወች አሉ። አንድ ትምህርት ቤት ተምረዉ የማይገናኙ ሰወች አሉ እና እንድናገኛቸዉ ያደርጋል ሔዋንን ያመጣት ለእኛ የሚሆኑ ሰወችነ የሚያጣ እግዛአብሔር ነዉ። ግን ይህን አድርግ አይልም ይች አጥንት ከአጥንቴናት ያለዉ አዳም ነዉ በል ይች አጥንትህ ናት አላለዉም። ስለዚህ እኛነን መስፈርት አዉጥተን ስቃያችንን የምናየዉ።
☘️👉ሌላዉ የምናገባዉን ሰዉ መስፈርት ማዉጣት ይገባል ወይ አወ ይገባል አንዳንድ ጊዜ መስፈርቶቻችን በጣም ከፍ ይሉና እንዲህ የሆነ እንዲህ የሆነች አንድ አባት ምሳሌ ሲሰጡ ምን አሉ መሠላችሁ የሞላኒዛ ዉበና የማዘር ትሬዛን ስብእና አንድላይ ብለዉ የሚያስቡ አሉ። አንዳንድ ጊዜ ዉበት የሚያስደንቀዉ ዉበትን እዉቀት የሚያስደንቀዉ እዉቀትን ብለን መስፈርት ብለነ እንዲህ አይነት ሴት እንዲህ አይነት ወንድ ስንል ትንሽ አልበዛም ወይ? በኃይማኖት እንደት ይታያል ሲባል መስፈርት ማብዛት አልተከለከለም። የእኛ መፅሐፍ ሰባት ገበያ ተመላለስ ከመወሰንህ በፊት ይላል ። የዛኔ ሰዉ የሚገናኘዉ በገበያ ስለነበረ በገበያ ነዉ መግለፅ የሚችሉት ስለዚህ ከመወሰንህ በፊት የብቸኝነት ጊዜህን አንዱ ትልቁ ነገር የመምረጥ መብት አለህ ይሄን ማለት ግን ጓደኝነት እየጀመሩ አብረዉ እየተኙ አይደለም ሰዉ ጫማ ለይደለም እየተለካ 🤔 ክቡር ነዉ ሰዉ ሌላ ነገር ዉስጥ ሳንገባ መምረጥ አለብን መስፈርት ማብዛት ጥፋት አይደለም አንደኛ እምነት ነዉ እግዚአብሔር ይሄን አያሳጣኝም ብሎ ማመን ነዉ
ሁለተኛ በራስ መተማመን አለብን ለምሳሌ አንድ የንጉስ ልጅ የሆነች ሴተ የሚያገቡት የንጉስ ልጅነዉ ለምን እነሱ የንጉስ ልጅ ስለሆኑ መርጠዉ ነዉ የሚያገቡት
እኛ የንጉስ ልጆች ነን የእግዚአብሔር ልጆች ነን ስለዚህ ክብርን ማወቅ ያስፈልጋል።
የሠማነዉን በልቦናችን ያሳድርብን አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቁ ክቡር አሜን ይቆየን
BY የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/hamreel/4236