tgoop.com/hararimassmediaagency/11300
Last Update:
ታንዛኒያ ባለፈው የምርት ዘመን በበቆሎ አምራች ከሆኑ አፍሪካ ሀገራት ተርታ ሁለተኛ ደረጃ ያዘች ።
*****
ከዚህ በፊት ናይጄሪያ በሁለተኝነት ትቀመጥ የነበረች ሀገር ብትሆንም አሁን ግን ስፍራዋ በታዛኒያ ተነጥቃለች።
ዘ ሲትዝን እንደ ዘገበው ከሆነ ከደበቡ አፍሪካ በመቀጠል በሁለተኝነት የተቀመጠችው ታንዛኒያ እ.ኤ.አ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ማለትም 2023 /24 የምርት ዘመን 11.7 ሚሊዮን ቶን የበቆሎ ምርት ማምረት መቻሏን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ።
ካለፈው የምርት ዓመት በፊት ቀድሞ ከነበረው ምርት ጋር ሲነፃፃር 6.4 ቶን ብልጫ አለው ተብሏል ።
ሀገሪቱ ለበቆሎ ምርት መሻሻል ባደረገችው የማደበሪያ ድጎማ ፣ የማሽነሪ እንዲሁም ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ማሻሻል በመቻሏ የመጣ ለውጥ ነው ተብሏል።
የበቆሎን ምርትማት ከሚቀንሱት መካከል አንዱ በቆሎን የሚመገቡ ፀረ ሰብል የሆኑ የተለያዩ ነብሳቶች ናቸው የሚለው የዓለም አቀፍ ግብርና ትስስር ድርጅት ፤ ታንዛኒያ ከጅምሩ ይህንን ለመከላከል በሰራቸው ስራ ጥሩ ውጤት አስመዝግባለች ብሏል።
በሩሲያና በዩኩሬን ጦርነት ምክንያት የማዳበሪያ ዋጋ መናር ለአፍሪካ ገበሬዎች የምርት ዓመቱን ያከበደ ቢሆንም እንደ ታንዛኒያ ያሉ ሀገራት ድጎማ በማድረግ ብቻ ችግሩን መቋቋም ችለዋል ብሏል ድርጅቱ።
በአፍሪካ ቀዳሚ የበቆሎ አምራች ሀገር በመሆን በዓመት ከ17 ሚሊዮን ቶን በላይ በማምረት ደበብ አፍሪካ ስትመራ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ተለዋዋጭ ምርትን በየዓመቱ በማስመዝገብ የሁለተኛኝት ደረጃው ላይ ተፈራርቀው ይቀመጣሉ ።
የተለያዩ ማመለከቻዎች እንደሚጠቀሙት ደግሞ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይይዛሉ ።
በዓለማችን ከፍተኛ የበቆሎ አምራች ሀገር አሜሪካ ናት ። የዓለምን 32 እጅ ምርት ወደ ጎተራዎ ተስገባለች ። ቻይና እና ብራዚል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይይዛሉ ። በምስጋናው ሀይሉ
28 05 17
BY Harari Mass Media Agency
Share with your friend now:
tgoop.com/hararimassmediaagency/11300