tgoop.com/hiwete/573
Last Update:
ክፍል ሁለት 2️⃣
የወጣትነት ዘመን ጠባያት
በወጣትነት እድሜ ለክርስትና ሕይወት አስተዋፆ የሚያደርጉ በጎ እድሎችን፤ክርስቲያናዊነትን የሚፈታተኑ ተግዳሮቶችን፤በሕይወታችን መልካም ጓደኛን የመምረጥ ጠቀሜታንና ከክፉ ጓደኛ መራቅ እንዴት እንደሚቻል እና ክርስትና ሕይወታችንን በተሳካ መንገድ ለመምራት የምንችልበት መንገድ እንዲሁም ወጣቶች በዘመናቸው የሚገጥሙ ፈተናዎችን ካሸነፉ ክርስትያን ወጣቶች ለመማር እነርሱም ማሸነፍ የሚችሉበትን ክህሎት በማዳበር "በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ" በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት መጓዝ እንድንችል ይህ አጭር መማሪያ ተዘጋጅቷል።
የሰው ተፈጥሮ
#ሰው እግዚአብሔር በአምሳሉና በምሳሌው የፈጠረው ልዩ ክቡር ፍጥረት ነው። "እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንድምሳሌያችን እንፍጠር "ዘፍ ፩፥፳፮
የሰው ለፈጣሪ ምሳሌነቱ በነፍሱ ሲሆን ሦስት ባህርያት አሉት። እነርሱም ልባዊነት(ማሰብ)፤ ቃላዊነት(መናገር)፤ ዘላለማዊነት(እስትንፋስ) ናቸው።
በመልካችን ብሎ ራሱን አስመስሎ ፈጥሮታል።መልኩም ከአራቱ ባህርያተ ስጋ ተፈጥሯል።
#ባህርያት ማለት የነገር ሁሉ ስር፣መገኛመሰረት ማለት ነው። መሬት፣ውኃ ፣እሳት እና ንፋስ የፍጥረታት መገኛዎች በመሆናቸው አራቱ ባህርያት ተብለው ይጠራሉ። እያንዳዳቸው ሦስት ሦስት ጠባያት አሏቸው። ይኸውም የምስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው።
#መሬት ፡ አፈር ትቢያ ማለት ነው።መሬት ገና ከውኃ ሳትለይ #ጸብር ትባል ነበር።#ጭቃ ማለት ነው። ለፍጥረታት ሁሉ ማደሪያ ትሆን ዘንድ በመሰጠቷ ደግሞ #ምድር ትባላለች። መሬት ሦስት ጠባያት አሏት። እነሱም
#፩. ይቡስነት(ደረቅ መሆን)
#፪. ጽሉምነት(ጨለማነት)
#፫. ቆሪርነት(ቀዝቃዛነት) ናቸው።
#ለውኃ ፡ ሦስት ጠባያት አሏት። እነርሱም
#፩. ብሩህነት(ብርሃን)
#፪. እርጡብነት(መርጠብ)
#፫. ቆሪርነት(ቀዝቃዛነት)
በቀጣይ ክፍል ሁለቱን ባህርያተ ስጋን እና የሁሉንም ባህርያት ዘመን እናያለን።
እባካችሁ share በማድረግ ተባበሩኝ።🙏🙏👋
#share & #join
@hiwete @hiwete @hiwete💚
@hiwete @hiwete @hiwete💛
@hiwete @hiwete @hiwete❤️
BY የወጣቶች ሕይወት✨
Share with your friend now:
tgoop.com/hiwete/573