tgoop.com/infobyjoss/1645
Last Update:
የማምሻ ወግ...!
✅ፊታውራሪው ያወጓችሗል
፩(₁).«ኢትዮጵያ ማርቆስ አባቴ እስክንድሪያ እናቴ ብላ አምና የሃይማኖት ክርክር በተነሳ ቁጥር ስትሠለፍ የኖረችው ከእስክንድሪያው ፓትሪያርክ ጎን መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል።
፪(₂).«ሀገራችንን ግራኝ በወረረ ጊዜ ካቶሊካዊ የሆኑት የፖርቹጋል ሰዎች ለእርዳታ መጥተው ታላቅ መሥዋዕት በመክፈል ሲረዱን የግብጽ እስላማዊ መንግስት ከቱርክ ጋር ሆኖ ግራኝን ሲረዳ እንደነበረ ታሪኩ ይመሰክራል።»
፫(₃).«አፄ ምኒልክ ሀገራቸውን በስልጣኔ ለመምራት አስበው አዲስ አበባ የዳግማዊ ምኒልክን ትምህርት ቤት ሲከፍቱ ግብፆች በሃይማኖት አስታከው እኛ እናስተምራለን ብለው የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ሥራ ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ በፈረንሳዊ ና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጠው ትምሕርት በመጠኑ ከማንበብና ከመፃፍ ደረጃ እንዳያልፍ ወስነው ተማሪ ቤቱ ሲሠራ በአንድ ዓይነት ፕላንና መሠረት አብሮ ተሠርቶ ጣራው ተከድኖ፣የጣራው ፕላፎንና የመሬቱ ወለል በሳንቃ ማልበስና ማንጠፍ መዝጊያ እና መስኮት መግጠም ሲቀረው ሥራው ቆሞ የእርግቦች መኖሪያ ሆነው የኖሩትን ሁለት ክፍሎች ማስጨረስና በሥራ ላይ ማዋል ይመስል በቸልተኝነት ማኖራቸው የትምሕርቱንም አሰጣጥ በዘመናዊ እቅድ ባለመምራታቸው በአባይ ጅረት ምክንያት ኢትዮጵያ ሠልጥና ኃይል እንዳታገኝ የሚመኘውን የሀገራቸው እስላማዊ መንግሥት ሲአደርገው የኖረውን የቁጥጥር ፖሊሲ ሲጠብቁ እንደነበረ ያሳያል።»
በአባይ ጅረት ምክንያት ኢትዮጵያ ሠልጥና ኃይል እንዳታገኝ የሚመኘው የግብጽ መንግሥት፣ፊታውራሪ አርአያ ሥላሴ ዘለቀ፣ከገጽ 14—15 የተቆነጠረ!
ወጉን ያጋራችሁ ሰውየ @gazetaw1 ውስጥ አለ!
BY JBC voice🔊📢
Share with your friend now:
tgoop.com/infobyjoss/1645