INFOBYJOSS Telegram 1659
የሰንበት ወግ

⎡በደስአለኝ ከፍአለ— ከመካነ ሰላም⎤

«ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ እንዳናፈራ!»

የመማሪያ ክፍል ውስጥ ነኝ። ዘግይተን የጀመርነውን ኮርስ ለማካካስ ጧት፣ ከሰዓት እና ቅዳሜን ጨምሮ በመማር ላይ ነን።

መካነ አዕምሮአችን የገጠመው የመምህራን እጥረት ለኮርሱ መዘግየት ምክንያት ነበር።

ዶ/ር ሰውአገኝ ይባላሉ። የመቅደላ አምባ መካነ አዕምሮ  የአማርኛ ቋንቋ እና ሥነ ፅሑፍ መምህር ናቸው።የዘገየውን ኮርስ የሚያስተምሩን መምህራችንም ናቸው።

ይሀንን ኮርስ በማስተማር ላይ እያሉ ነበር ከላይ ለወጓ አርዕስት ያደረኳትን ምክር አዘል ንግግር ጣል ያደረጓት።

ከኮርሱ አንደኛው ርዕስ መንደርደሪያ ሆናቸውና እንዲህ አሉ «አሁን አሁን የተረት መፅሐፍትን በማንበብ ህፃናት ልጆችን ማስተኛት ልምድ ከሆነ ቆይቷል» ሲሉ ሌላ ነገር ሊያወሩ እንደሆነ ገባኝና በደንብ ልከታተላቸው ተዘጋጀሁ።

ማብራሪያቸውን ቀጠሉ«ህፃናት ልጆችን ለማስተኛት የተረት መፀሐፍ ይዘን ከአልጋ ላይ ተቀምጠን ማንበብ የብዙዎቻችን ልምድ እየሆነ መጥቷል»።

«ታዲያ ይህ ተግባር ሌላ ትልቅ ችግር እንደሚያስከትል የተገነዘብነው አይመስለኝም »።

«ልጆችን መፅሐፍ እያነበብን እንዲተኙ የምናደርጋቸው ከሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ወደ ት/ት ተቋም ተቀላቅለው በትምህርታቸው ለመብረታት ሲያነቡ  እንዲተኙ ይገደዳሉ ማለት አይደል? »ሲሉ ይጠይቃሉ።

«በርግጥ ተረት ህፃን ልጆችን ለማስተማር፣ በጥሩ ሥነ ምግባር ለማሳደግ፣ የወጡበትን ማህበረሰብ ወግ፣ባህል፣ ልማድ እና ሌሎችንም ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዲያውቁ ለማድረግ የማይተካ ሚና አለው »ይላሉ።

ዳሩ ግን መቼ፣ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ እንጠቀማው የሚለውን እንዲህ ይናገራሉ:-

« ተረትን መፅሐፉን ይዘን እያነበብን እንዲተኙ ከምናደርጋቸው ይልቅ፣ እኛ በሚገባ ካነበብነው በኋላ በቃል እየተረክን፣የአካል እንቅስቃሴ(ከዋኔ) በማድረግ ትኩረታቸውን ወደ እኛ በመሣብ በደንብ አዳምጠውን እንዲማሩበት ማድረግ አለብን »ይላሉ።

«ካልሆነ ግን መዋል ላለበት ዓላማ ቀርቶ፣ መዋል ለሌበት ዓላማ በማዋል ትልቅ ነገር በሚሰሩና ትልቅ ነገር በሚጠብቃቸው የዛሬዎቹ ህፃናት ፣የነገዎቹ ወጣቶች እና ጎልማሶች ላይ ችግር መፍጠር ይሆንብናል»የሚል ፅኑ አቋም አላቸው።

«ከሥነ ቃል አይነቶች አንዱ የሆነውን ተረት ለአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ትውልድን በመቅረጽ ረገድ የሚያበረክተውን የማይተካ አስተዋጽኦ ማደብዘዝ እና ማጥፋት እንዳይሆን »ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ።

«ይህም ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ አፍርተን ለአገር ዕድገት የጀርባ አጥንት የሆነውን የትምህርት ስርዓት ልጆች በንቃት እንዳይሳተፋበትና ውጤታማ እንዳይሆኑበት ያደርጋቸዋል » በማለት ትዝብታቸውን ተናገሩ።

ነገሩን ያጤንኩት በእኛ መካነ አዕምሮ ውስጥ እንደቀልድ የምናደርገው መሆኑ ትዝ ሲለኝ ነበር።

አንድ የዶርም ተማሪ «እንቅልፍ እምቢ አለኝ? » ካለ ጋደም በልና መፅሐፍ ገለጥበት ወዲያው ይወስድሃል። እንበባላለን።

መምህሬ እውነታቸውን ነው። ይኸው እንዳሉት ማንበብን ለዕውቀት ሳይሆን ለእንቅልፍ እየተጠቀምንበት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስጋት ቢያደርባቸው በእሳቸው አልፈርድም።ትውልድ እየተዘናጋ ነውና።

ምክንያቱም ለአገራችን ኢትዮጵያ ቀርቶ ለአፍሪካ እና ለመላው ዓለም አንባቢ ትውልድ ያስፈልገዋል።

በተለይ ለአሁኗ ኢትዮጵያ ያነበበ፣ ወደፊትም የሚያነብ፣ታሪክን ያወቀ፣ወደፊትም የሚያውቅ እና የሚረዳ ችግር ፍቺ ትውልድ ያስፈልጋታል።

በመጨረሻም « እናተም በኋላ ልጆቻችሁን የተረት መፅሐፍት በማንበብ እንዲተኙ እንዳታደርጉ፣ ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ እንዳናፈራ!» በማለት አደራ ጥለውብን ተለያየን።

እናተስ ምን ትላላችሁ?
 
ትዝብታችሁን አጋሩን🙏

   መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ🙏

tgoop.com/infobyjoss/1659
Create:
Last Update:

BY JBC voice🔊📢

Share with your friend now:
tgoop.com/infobyjoss/1659

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Healing through screaming therapy Telegram iOS app: In the “Chats” tab, click the new message icon in the right upper corner. Select “New Channel.” Write your hashtags in the language of your target audience. It’s yet another bloodbath on Satoshi Street. As of press time, Bitcoin (BTC) and the broader cryptocurrency market have corrected another 10 percent amid a massive sell-off. Ethereum (EHT) is down a staggering 15 percent moving close to $1,000, down more than 42 percent on the weekly chart. How to create a business channel on Telegram? (Tutorial)
from us

Telegram JBC voice🔊📢
FROM American