tgoop.com/islam_in_school/6328
Create:
Last Update:
Last Update:
ኒቃቢስቲቱ ባለ ሜዳሊያ ከወሎ ዩኒቨርስቲ‼
================================
✍ «ዚኪራ ሰዒድ በሴቶች ቀን የተመረቀች ጠንካራዋ ሴት
****
ዚኪራ ሰዒድ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ነች::
የትምህርትን ውጣ ውረድ አሸንፋ ዛሬ የተመረቀችው ዚኪራ ራሷንም፣ ቤተሰቦቿንም፣ አስተማሪዎቿንም፣ ዩኒቨርሲቲዋንም፣ አልፎም ሀገርንም በሚያኮራ ውጤት ነው ትምህርቷን ያጠናቀቀችው፡፡
ከትምህርት ክፍሏ 3.99 አጠቃላይ ውጤት በማስመዝገብ፣ በወሎ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የዓመቱ ተመራቂዎች ብልጫ ባለው ውጤት በዛሬው ዕለት ተመርቃለች፡፡
በዚህ ውጤቷም የምስክር ወረቀት፣ የሜዳሊያ እና የሁለት ዋንጫዎች እንዲሁም ልዩ ተሸላሚ ሆናለች ታታሪዋ ዚኪራ፡፡»
ምንጭ፦ EBC
በርግጥ የልጅቷ ዜና የደረሰኝ ትናንት ነው። ታዲያ ኒቃብ ለዚህ ማዕረግ የበቁ ሴቶችን እያፈራ ስለሆነ ብላችሁ ነው እንደ በየቦታው ኒቃቢስቶችን የምታሰቃዩት?
እስኪ አስተውሉ። ኒቃብ ስትከለክሉ ብዙ አቅም ትቀብራላችሁ፣ ሃገርን ወደ ኋላ ትጎትታላችሁ።
ኒቃብ አካልን እንጂ አዕምሮን አይሸፍንም የምንለው በምክንያት ነው።
@islam_in_school
BY ISLAMIC SCHOOL️

Share with your friend now:
tgoop.com/islam_in_school/6328