tgoop.com/iwnetlehullu1/518
Last Update:
▣የነቢዩ ﷺ ስብዕና▣
ብዙ ግዜ ካፊሮች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዶዒፍ ሀዲሶችን ከጉግል እየለቃቀሙ እና አንዳንድ ሶሒሕ ሀዲሶችን በትክክል ባለመረዳት የነቢዩ ﷺ ስምን ሲያጎድፉ ይታያሉ።
"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!" ነውና
በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ ራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም።
የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል። ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው።
በአላህ ፈቃድ ስለ ውዱ ነቢያችን ስብዕና የተወሰኑ ሀዲሶችን እናያለን
➠ ውዱ ነቢያችን ከሁሉም የትልቅ ስነምግባር እና ጠባይ ባለቤት ነበሩ
-አላህ እንዲህ ይላል👇
وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
(ሱረቱ አል-ቀለም - 4)
አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡
وعن أنس رضي الله عنه قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم أحسن الناس خلقاً ((متفق عليه)).
አነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል
“ነብዩ ﷺ ከሁሉም የላቀ ስነ-ምግባር የነበራቸው ነበሩ።”
📘Bukhari 3549 muslim 2310a
ውዷ ሚስታቸው ዓኢሻህም ስለ ነብዩ ﷺ ሥነ-ምግባር ስትነግረን፡-
كان خلقه القرآن (رواه مسلم)
“የነብዩ ﷺ ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር” ትለናለች
📘Sahih Muslim 746a
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ: إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩት መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*።
📘 Adab al-mufrad 273
قال أَنَس رضي الله عنهَ :
« لَقَدْ خَدَمْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ عَشْرَ سِنِينَ ، فَوَاللَّهِ مَا قَالَ لِي : أُفٍّ قَطُّ ، وَلَمْ يَقُلْ لِشَيْءٍ فَعَلْتُهُ : لِمَ فَعَلْتَ كَذَا ، وَلا لِشَيْءٍ لَمْ أَفْعَلْهُ أَلا فَعَلْتَ كَذَا »
አነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል
"የአሏህ መልእክተኛን ﷺ አስር አመት አገልግያለሁ። ወላሂ! ፈፅሞ 'ኤጭ!' ብለውኝ አያውቁም። አንድንም ጉዳይ 'ለምን ይህን ሰራህ?'፣ 'እንዲህ ብትሰራ ኖሮ' ብለውኝ አያውቁም»
📘sahih muslim 2309
➠ውዱ ነቢያችን በጣም ለጋስ ነበሩ።
جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ مَا سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم شَيْئًا قَطُّ فَقَالَ لاَ .
ጃቢር(ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ብሏል
" የአላህ መልእክተኛ ﷺ አንድን ነገር እንዲሰጧቸው ተጠይቀው እምቢ አልሰጥም ብለው አያቁም።
📘Sahih Muslim 2311a
➠ ውዱ ነቢያችን ጠላቶቻቸው በነበሩ የመካ አጋሪዎች ሳይቀር ታማኙ ሙሐመድ ተብለው ይጠሩ ነበር።
በመካከላቸው ልዩነት በተፈጠረ ግዜ ታማኙ ሙሐመድ ያፋርደናል ብለው እንዳፋረዷቸው
📘musnad ahmad 15504 ተጠቅሷል።
إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ
[ ሱረቱ አል-ሒጅር - 95 ]
ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡
🌴አላሁመ ሶሊ ዐላ ነቢይና ሙሐመድ 🌴
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1
BY የኢስላም እውነት ለሁሉ Truth for all
Share with your friend now:
tgoop.com/iwnetlehullu1/518