tgoop.com/iwnetlehullu1/527
Last Update:
▣ ቁርአን ፍጡር አይደለም ▣
بسم الله الرحمن الرحيم
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
➠ ባሳለፍነው ርዕሳችን ላይ ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑን ከቁርአን ከሐድስና ከሰለፎች ንግግር በማስረጃ አይተናል። ዛሬ ደግሞ በአላህ ፈቃድ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ እናያለን ኢንሻአላህ።
ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ማስረጃዎቻችን👇
➥ ባለፈው ርዕስ ላይ ቁርአን የአላህ ቃል እንደሆነ አይተን ነበር።ቁርአን የአላህ ቃል ከሆነ ቁርአን ፍጡር ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የአላህ ቃል የአላህ ባህሪይና መገለጫ እንጂ ፍጡር አይደለም። የአላህ ንግግር ከአላህ ተነጥሎ የሚቆም ነገር ስላልሆነ የአላህ ባህሪይና መገለጫ እንጂ ፍጡር አይደለም።
➥ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ካወቅንባቸው ማስረጃዎች ሁለተኛው
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዐላ በቁርአኑ ወስጥ ትዕዛዙን ከፍጥረት ለይቶ ስላመጣው ፍጥረት እና ትዕዛዝ ለየ ቅል የሆኑ የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ألا لهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡
[📗አዕራፍ 54]
☝️አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ እዚህ አንቀጽ ላይ ፍጥረት እና ትዕዛዝ ለይቶ ጠቅሷል።
ሁለቱም የተለያዩ ነገሮች ስለሆኑ የአላህ ትዕዛዝ ፍጡር አይደለም።
ቁርአን ደግሞ የአላህ ትዕዛዝ ስለሆነ ፍጡር ሊሆን አይችልም።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡
[📗 ሹራ 42:52]
➥ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ካወቅንባቸው ማስረጃዎች ሌላኛው አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ በቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል👇
إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ
እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡
[📗 አል'ቀመር 54:49]
አላህ የፈጠራቸው ነገሮች ገደብ እና ውስኑነት ማለቂያ አላቸው። ፍጡር የሆነ ነገር ሁሉ ያልቃል።
የአላህ ቃል ደግሞ ፍጡር ስላልሆነ ማለቂያ የለውም።
አላህ እንዲህ ይላል👇
قُل لَّوْ كَانَ الْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَاتِ رَبِّي لَنَفِدَ الْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَاتُ رَبِّي وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِ مَدَدًا
«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡
(📗ሱረቱል ከህፍ 18:109)
-ፍጡር ማለቂያ ካለውና የሚያልቅ ከሆነ
-የአላህ ቃል ደግሞ ማለቂያ ከሌለው
የአላህ ቃል ፍጡር ሊሆን አይችልም።
➥ በተጨማሪም ሀዲስ ላይ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች ሲጠበቁ እና እንድንጠበቅ እየመከሩን እናያለን።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِذا نَزَلَ أَحَدُكُمْ مَنْزِلًا، فَلْيَقُلْ: أَعُوذُ بكَلِماتِ اللهِ التّامّاتِ مِن شَرِّ ما خَلَقَ، فإنَّه لا يَضُرُّهُ شيءٌ حتّى يَرْتَحِلَ منه.﴾
“አንዳችሁ የሆነ ቦታ ካረፈ ‘ሙሉ በሆኑት የአላህ ንግግሮች እሱ ከፈጠራቸው ተንኮሎች እጠበቃለሁ’ ካለ ከቦታው እስኪሄድ ድረስ ምንም ነገር አይጎዳውም።”
(📘ሙስሊም ዘግበውታል: 2708 )
➠እንደሚታወቀው ፍጡር በሆኑት ነገሮች መጠበቅ አይፈቀድም ክልክል ነው። ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች መጠበቃቸው የአላህ ንግግሮች ፍጡር አለመሆናቸው ያመላክታል። የአላህ ንግግሮች ፍጡር ቢሆኑ ኖሮማ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች ባልተጠበቁ ነበር። ቁርአን ደግሞ የአላህ ንግግር ስለሆነ ፍጡር አይደለም።
➠ ቀደምት ሰለፎቻችንም ቁርአን የአላህ ቃል እና ባህሪይ እንደሆነ ፍጡር እንዳልሆነ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።
قال أحمدُ بنُ محمَّدِ بنِ حَنبَلٍ رحمه اللهُ: لقيتُ الرِّجالَ، والعُلَماءَ، والفُقَهاءَ، بمكَّةَ والمدينةِ والكوفةِ والبَصرةِ والشَّامِ والثُّغورِ وخُراسان، فرأيتُهم على السُّنَّةِ والجماعةِ، وسألتُ عنها الفُقَهاءَ؟ فكُلٌّ يقولُ: القُرآنُ كلامُ اللهِ، غيرُ مخلوقٍ، منه بدأ، وإليه يعودُ
ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል{164-241ሂ) እንዲህ ብሏል" በመካ፣በመዲናህ፣በኩፋህ፣በበስራህ፣በሻም፣በሰغوር እና በኸራሳን ብዙ ኡለሞች(ሊቃውንት) በአህለ-ሱናህ ላይ ሆነው አይቻቸዋለሁ።ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣ፍጡር አይደለም ከአላህ ዘንድ መውረድ ጀመረ ወደሱም ይመለሳል ብለው ያምኑ ነበር።
📘ኢኽቲሷስ አል-ቁርአን ገፅ 21
➠ ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል
" ቁርአን የአላህ ባህሪይ በመሆኑ ላይ የሱናህ ባለቤቶች ተስማምተዋል።"
📘መጅሙዕ አል-ፈታዋ ቅጽ 17 ገፅ 78
ኢማም አቡ ሐቲም አል-ራዚ{195-277ሂ} እና አቡ ዙርዓህ አል-ራዚ{207-264ሂ) በሁሉም የዐለማችን ክፍሎች የነበሩ ኡለሞች የነበሩበትን እምነት ሲጠቅሱ " ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፤ ፍጡር አይደለም ብለው ያምኑ ነበር" ብለዋል።
📘ሸርሕ ኡሱል ኢዕቲቃዱ አህሊ-ሱና ወል-ጀማዓህ ገፅ 279
ስለዚህ ቁርአን የአላሁ ሱብሐነሀ ወተዓላ ንግግር እና ባህሪይ እንጂ ፍጡር አይደለም።
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1
BY የኢስላም እውነት ለሁሉ Truth for all
Share with your friend now:
tgoop.com/iwnetlehullu1/527