tgoop.com/iwnetlehullu1/534
Last Update:
አሥሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ
➥ ሰለምቴዎችን አደራ➥
➘ ሰለምቴዎችን ስናገኝ ፍቅር እንስጣቸው እንንከባከባቸው እነሱ ለአላህ ብለው የተመቻቸ ኑሮን ትተው ብዙ ችግሮች ሲደርስባቸው እኛ ለነሱ ጀርባ ልንሰጣቸው ይቅርና በጣም ልንኸድማቸው ልንንከባከባቸው ይገባል።
በቻልነው ልክ እነሱን መርዳት አለብን።
ውዱ ነቢያችን ﷺ ለሰለሙ ሰዎች እስከ 100 ግመል ይሰጡ ነበር። አስቡት ለአንድ ሰው 100 ግመል።
100 ግመል ስጡ አልላችሁም ቢያንስ የምትችሉትን ያክል አግዟቸው እርዷቸው ብቸኛ አታድርጓቸው።
➥ አንዳንድ ወንድም እህቶቻችን ለሚጠይቋቸው አንዳንድ ጥያቄዎች አላስፈላጊ መልስ አንስጣቸው። የተጠየቀውን ከመመለስ ይልቅ
አንተ ሙስሊም አይደለህምንዴ? ይሄ እንዴት ይጠፋሀል? ሙስሊም አትመስለኝም. ወዘተ እያሉ ሰዎችን ጥያቄ በመጠየቃቸው ብቻ የሚያከፍሩ አላዋቂዎች አሉ። አድቡ ስርዓት ያዙ መመለስ ባትችሉንኳ ዝም በሉ።
"በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል ብለዋል ውዱ ነቢያችንﷺ
📘Muslim book 1 hadith 80
*ጠያቂዎቹ ገና አዲስ ሰለምቴ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ከእስልምና ራቅ ብለው የነበሩና የቶበቱ ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ አደብ ሊኖረን ይገባል።
ካፊሮችንም እንደዛው አላህ በቁርአኑ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ 📗16:125
ብሎ እንዳዘዘን የአላህ ትዕዛዝ መፈፀም አለብን።
ነቢያችን ﷺ ሊገድሏቸው ሊሰድቧቸው የመጡ ስንትና ስንት ሰዎችን ነው በመልካም ስነምግባራቸው አስልመው ያስቀሩት።
ሰለምቴዎችን ከራሳችሁ ጋር አስፈጥረ
➥ የሰለሙ ሰዎች የሰለሙበትን ቪድዮ አትለቀቁ፣ የሰለሙበትን ሀገር ስም አትጥቀሱ ይሀ ለነሱ ፊትና ነው የሚሆነው
➥ ዘካ የምታወጡ ሰዎች ደግሞ ዘካህ ከሚሰጣቸው ሰዎች መካከል ሰለምቴዎች ናቸውና ዘካህ ለሰለምቴዎች አውጡ
➥ሰለምቴዎችን አደራ አደራ➥
BY የኢስላም እውነት ለሁሉ Truth for all
Share with your friend now:
tgoop.com/iwnetlehullu1/534