tgoop.com/keldenakumnger/281
Last Update:
#በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደረሰ፤ የሟቾች ቁጥርም 20 ሆኗል
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5500 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 1934 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 75 ወንድ እና 54 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 124 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት የደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ የአሜሪካ፣ የኤርትራ እና ሱዳን ዜጎች ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 101 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 5 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል ናቸው።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ80 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ህይወት አልፏል።
ሟቿ ወደ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና በመጡ በአንድ ሰዓት ወስጥ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። በአስክሬን ምርመራም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሃያ (20) ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች (2 ከትግራይ ክልል፣ 6 ከአፋር ክልል፣ 1 ከሶማሌ ክልል እና 10 ከአዲስ አበባ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 281 ደርሷል።
Via@AccessAddis
BY 👍
Share with your friend now:
tgoop.com/keldenakumnger/281