tgoop.com/kidase/667
Last Update:
📌 #የእለቱ_ንባብ =ሮሜ 5:18-19
¹⁸ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
¹⁹ በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
📌 #የእለቱ_ጥያቄ =የዓብይ ፆም ጉዞ ጥያቄ ክፍል አራት (ከጥያቄ 10-12)
🔴 10. እስራኤል በሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ዘመን ለሁለት ተከፍለው ነበር ሰሜኑ እስራኤል የሚል ስም ወሰደ የደቡቡ ስም ማን ይባል ነበር?
ሀ/ ሰማርያ
ለ/ የሞዓብ ምድር
ሐ/ ከነዓን
መ/ ይሁዳ
🔴 11/ በአባቱ በንጉሥ ዳዊት ላይ ያመፀዉ ልጅ ማነው?
ሀ/ መቃቢስ
ለ/ ሰሎሞን
ሐ/ ይሁዳ
መ/ አቤሴሎም
🔴 12. ንጉሥ አክዓብ "እስራኤልን የምትገላብጥ አንተ ነህን" ብሎ የተናገረው ማን ነው?
ሀ/ አብድዩ
ለ/ አሰሳዕ
ሐ/ ኤልያስ
መ/ በኣል
📡 Tewahedo youth channel (Tyc) 📡
ተዋሕዶ የወጣቶች ቻናል
የቅዳሴ እና መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል
🎙 Telegram = @kidase @kidase @kidase
📺 Youtube= https://youtube.com/channel/UCSBVFP-t15hhw4HB8u94hoA
BY Tewahedo youth channel (Tyc) ተዋሕዶ የወጣቶች ቻናል የቅዳሴ እና መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል
Share with your friend now:
tgoop.com/kidase/667