tgoop.com/kidstarsema6/4212
Last Update:
🍓🍓🍓#ቤተማርያም🍓🍓🍓
ሐምሌ 7
#ሥሉስ_ቅዱስ
#በአንድነቱ_ምንታዌ_ሁለትነት #በሶስትነቱ_ርባዌ_አራትነት_የሌለበት የዘላለም #አምላክ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ #እግዚአብሔር_ወልድ_እግዚአብሔር #መንፈስ ቅዱስ ሐምሌ 7 አመታዊ ክብረ በዓላቸው ነው።።
መፃህፍታት እንዲህ ይላሉ 👉ከፍጥረት ወገን #ከእመቤታችን ቀጥሎ #የአብርሃምን_ያክል_በእግዚአብሔር ዘንድ የሚወደድ ፍጡር የለም።።አባታችን አብርሃም #የደግነት ሁሉ አባት ነውና #በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ስር #ስላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል።።
አባታችን አብርሃም በ 99 አመቱ እናታችን ሳራ በ 89 አመታቸው የሁሉ ፈጣሪ የሆኑትን #ሥላሴን አስተናገዱ።።
አብርሃም እግራቸውን አጠበ
ምሳቸውን አቀረበላቸው
በዚች ዕለትም መካን የነበረችው ሳራን በሚቀጥለው አመት ስንመጣ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ተብላ ተበሰሩ ሳራ ግን ሳቀች #ሥላሴ_ምንት_አስሐቃ_ለሣራ_ለባሕቲታ ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት #ይሳቅ ተባለ።።
ወዳጆቸ ስላሴን ያስተናገደች ድንኳን ( ሐይመት) #እመቤታችን_ማርያም ምሳሌ ናት።። በድንግል ላይ አብ ለአፀንኦ መንፈስ ቅዱስ ለአንፅኦ ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በርሷ ላይ አርፈዋል።
❤️❤️መልካም ቀን ተመኝን❤️❤️
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
BY 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
Share with your friend now:
tgoop.com/kidstarsema6/4212