tgoop.com/kidstarsema6/4222
Last Update:
እግዚአብሔር የለም
..አንድ አባት ፀጉራቸውን ሊስተካከሉ በቅርባቸው ወዳለው አንድ ፀጉር ቤት ያዘግማሉ ከፀጉር ቤቱም ከደረሱ በኋላ ከመስተካከያው ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ፀጉር አስተካካዮ ፀጉራቸውን መከርከም ይጀምራል
ድንገት ይህ ፀጉር አስተካካይ "እግዚአብሔርማ የለም" በማለት ወሬውን ይጀምራል ሸማግሌው በጣም ደነገጡ ድንጋጤቸው እዳይታወቅባቸው ያልደነገጡ መስለው በመረጋጋት የልጁን ንግግር ማብሰልሰል ጀመሩ ...ንግግሩ ግራ ስለገባቸው ምነው ልጄ እዴት እደዚህ ልትል ቻልክ አሉት?
አስተካካዮም ቀበል አለና አይ አባቴ እሄ ንግግር አሁን ምን ማብራሪያ ያስፈልገዋል አያዩም እዴ? ሰው እርስ በእርሱ ተጨካክኖ ሲባላ ሲገዳደል ደሀ ሲበደል ፍርድ ሲጓደል ጦርነቱ ረሀቡ ግፉ በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰው ሰብዓዊ የመብት ጥሰት የተፈጥሮ አደጋው እረ ምኑን ነግሬዎት ምኑን ልተው እሄንን ሁሉ እያዪ እግዚአብሔር አለ ማለት እዴት ይቻላል ?እረ የለም አለ እራሱ ለራሱ መልሶ።
በልጁ ንግግር የተበሳጩት አዛውንት ንግግሩ እጅግ ቢያበግናቸውም ቀስ ብለው በመረጋጋት ልጁን ካጠኑት በኋላ በዝምታ ትንሽ ዘግየት አሉና እሳቸውም ተራቸውን
" ፀጉር አስተካካይማ የለም አሉ".
አስተካካዩ ተራውን ደነገጠ እዴ ምንም ማለቶት ነው ?
እዴት የለም ይላሉ ከተማውን ሁሉ የሞላውስ ፀጉር ቤት አይደል እርሶንስ እያስተካከልኩ ያለውት እኔ ፀጉር አስተካካይ አይደለሁ እዴ? አላቸው
እሳቸውም ኮራ ብለው ፀጉር አስተካካይ ቢኖርማ ወንዱ ሁሉ ፀጉሩ ተንጨባሮ ግማሹ ጉንጉን ሰርቶት ግማሹ ጠቅልሎት የቅጫም መነሀሪያ አርጉት አይሄድም ነበር ተመልከት በመንገድ ላይ ወጪ ወራጁን ሁሉ ፀጉሩ ያልተስተካከለ ነው እና ለምን ይመስልሀል? አሉትና ፀጉር ቆራጭ ስለሌለ ነው ብለው የራሳቸውን ጥያቄ ራሳቸው መለሱለት
አስተካካዩም በንዴት እያረረ እዴ እነሱ እኮ ወደ ፀጉር ቤት ስላልመጡና ከፀጉር አስተካካዩቹ ጋር ስላልተገናኙ ነው የእነርሱ ፀጉር መንጨባረር የፀጉር አስተካካዪችን አለመኖር አይገልጥም የሚገልጠው የእነርሱ ወደ ፀጉር አስተካካዩቹ ጋር አለመሄዳቸውን ነው ብሎ መለሰላቸው
እርሳቸውም ትክክል መልሰሀል አየህ አንተም እግዚአብሔር የለም ከማለትህ በፊት እነዛ ቅድም የነገርከኝ ፋርድ የተጓደለባቸው ደሀ የተበደለባቸው ግፍ የደረሰባቸው በምድር ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ ነገር በሙ እየደረሰ ያለው እግዚአብሔር ስለሌለ ሳይሆን ሰዎቹ ወደ እግዚአብሔር ስላልሄዱ ነው ቅድም አተ እዳልከው የፀጉር መንጨባረር የፀጉር አስተካካዪችን አለመኖር አይገልጥም
የሚገልጠው የእነርሱ ወደ ፀጉር አስተካካዩቹ ጋር አለመሄዳቸውን ነው ብለህ ነበር አየህ
እዚህ ምድር ላይ የሚደርሰው ግፋና መከራ የእግዚአብሔርን አለመኖር አይገልጥም ።
ይልቅ ሰው ወደ እግዚአብሔር አለሜሄዱን ነው የሚገልጠው ሰው ከእግዚአብሔር በራቀ ቁጥር ለሀጥያት ለዲያብሎስ እና ለስጋ ምኞቱ ተገዢ ይሆናል የስጋ ምኞት ወደሞት እደሚመራን አሳምረህ ታውቃለህ አይደል አሉት? አስተካካዪም አዎ አለ
ከሚመጣው መከራ ለማምለጥ ወደ እግዚአብሔር መሮጥ እሱን መለመን ይጠበቅብና
በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 7÷7
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
ተብሎ የተመዘገበውንስ ታስታውሰዋለህ አይደል አሉት አስተካካዮም አዎ አለ
እሳቸውም ቀጠል አደረጉና አየህ ልጄ ለማግኘት መለመን አለብህ ለመግባትም ማንኳኳት ይጠበቅብሐል ።
በዝናብ አብቅሎ በፀሀይ አብስሎ የሚመግብህን አምላክ የለም በማለት የሰራህው ስህተት ከባድ ስህተት ነው ሐጥያትም ጭምር ነውና ሄደህ ለመምህረ ንሐህ ንገር አሉት አስተካካዪም ከስህተቱ ተሞሮ ወደ ንሰሀ አባቱ ለመሄድ ቃል ገባ..........
https://youtu.be/-3Hz2gharD8
https://youtu.be/-3Hz2gharD8
https://youtu.be/-3Hz2gharD8
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
BY 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
Share with your friend now:
tgoop.com/kidstarsema6/4222