tgoop.com/kidstarsema6/4255
Last Update:
🌻🌻🌻🌻#ቤተማርያም🌻🌻🌻🌻
#ጳጉሜን_3
እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
🌿🌿 ርኅወተ ሰማይ
🌿🌿 ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን::" ትባላለች::
አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም:: የሰው ልጆችን #ልመና_ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም #ቅዱስ_ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ::
#እመቤታችን_ድንግል_ማርያም #ለአጼ_ናዖድ እንደ ነገረቻቸው
👉👉በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: #የእግዚአብሔር_የምሕረት መዝገቡ #ስለሚከፈት_ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል:: በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት #ለዓመት_የሚበቃ_ምሕረት ይገኛል::
#ስለዚህም_አባቶቻችን_በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ:: በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል::
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን::አሜን
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
🌿🌿🌿🌿ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::
በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ (መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል:: በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::
አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት (ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::
ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው:: በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::
በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::
ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ #ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል::
#ቅዱስ_ሩፋኤል
መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
መዝገበ ጸሎት (#የጸሎት_መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
#ፈታሔ_ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል::
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
BY 🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
Share with your friend now:
tgoop.com/kidstarsema6/4255