#ነሐሴ ፳፬ - ክብረ በዓል
" የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯
እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)፣ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)፣ ለቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ እንዲኹም ለአበው አብርሐም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ ።
@kinexebebe
" የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯
እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)፣ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)፣ ለቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ እንዲኹም ለአበው አብርሐም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ ።
@kinexebebe
ታምሩ ብዙ ነው
መምህር ትህትና አባ ተክለሃይማኖት
ታምርህ በዛብኝ በዕለት በዕለት
አሐዱ አብ ቅዱስ ወላዲ አሰራጺ
አሐዱ ወልድ ቅዱስ ብለህ ተወላዲ
አሐዱ መንፈሰ ቅዱስ ነው ብለህ ሰራጲ
አስተማርክ ሰበክ በወንጌል አዋጅ
ሥላሴ ዕሩየ ሰባኪ ነህና
ላመሰግንህ እኔ በፍጹም ትህትና
የአንተ ውለታ በዝቶብኛል ና
አባ ባርከኒ በቅዱስ መሰቀልህ
ሁልጊዜ ልናገር ከጣፋጩ ገድልህ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈሰቅዱሰ
ልደትህ የሆነ በወርኃ ታኃሳስ
ማጥንትህ የሆነ በወርኃ ህዳር
ፍልሰትህ የሆነ በወርኃ ግንቦት 12
እንደዚህም ሆነ አንደበትህ ይላል ሥላሴ ሥላሴ
አባቴ ይደንቀኛል ገድልህ ለሁል ጊዜ
ለኔም አንተ ነህና ክብርና ሞገሴ
መድኃኒተ ኩና ለሕምምት ነፍሴ
ዳቤህን በልቼ ጸበልክን ጠጥቼ
እኖራለሁ ከአንተ ሁሌ ተጠግቼ
ኢቲሳ ትናገር አስተዳደግህን
ዳሞትም ትመስክር ጣዕም ስብከትህን
ታውራ አማራ ሳይንት ሕሙማን መፈወስህን
በፀሎተ ሚካኤል ደጅ ትህትና መዝራትህን
ደሞ መንበረ ሥላሴ የአጠንክባት ቦታ
በዛች ሐይቅ ደሴት ያረከው ታምራት
ምድሪቷን አረካት የጸባኦት ቦታ
ደብረ ዳሞ ወተህ ስትል ሃሌ ሉያ
አምላክህ ሸለመህ የመላዕክትን ክንፍ ደርቦ ደራርቦ
ጎብኝተህ ስትጨርሰ ገዳማትን ትግሬ
ለብሰህ ተጎናጽፈህ መልበሰ ዝማሬ
ሄድክ ቀራንዮ ሀገሩ ለህሬ
ሁሉንም ጨርሰህ መጣህ ደብር አስቦ
እኔስ ይገርመኛል የአንተ ተውሀቦ
በሁለት እግርህ ቆመህ የፀለይክባት ቦታ
ደሞም በአንድ እግርህ የቆምክባት ቦታ
በረከት ይገኛል ከማያልቀው ጸጋህ
ለዚህ ድንቅ ውለታህ አባቴ እንዴት ላመስግንህ
የኢትዮጵያም ምድር ውለታህ በዝቶባት እንዴት ታመስግንህ
ውለታህ በዛብኝ እንዴት ላመስግንህ
ታምረህ በዛብኝ እንዴት ላመስግንህ
ትርምትህ በዛብኝ እንዴት ላመሰግንህ:
@kinexebebe
መምህር ትህትና አባ ተክለሃይማኖት
ታምርህ በዛብኝ በዕለት በዕለት
አሐዱ አብ ቅዱስ ወላዲ አሰራጺ
አሐዱ ወልድ ቅዱስ ብለህ ተወላዲ
አሐዱ መንፈሰ ቅዱስ ነው ብለህ ሰራጲ
አስተማርክ ሰበክ በወንጌል አዋጅ
ሥላሴ ዕሩየ ሰባኪ ነህና
ላመሰግንህ እኔ በፍጹም ትህትና
የአንተ ውለታ በዝቶብኛል ና
አባ ባርከኒ በቅዱስ መሰቀልህ
ሁልጊዜ ልናገር ከጣፋጩ ገድልህ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈሰቅዱሰ
ልደትህ የሆነ በወርኃ ታኃሳስ
ማጥንትህ የሆነ በወርኃ ህዳር
ፍልሰትህ የሆነ በወርኃ ግንቦት 12
እንደዚህም ሆነ አንደበትህ ይላል ሥላሴ ሥላሴ
አባቴ ይደንቀኛል ገድልህ ለሁል ጊዜ
ለኔም አንተ ነህና ክብርና ሞገሴ
መድኃኒተ ኩና ለሕምምት ነፍሴ
ዳቤህን በልቼ ጸበልክን ጠጥቼ
እኖራለሁ ከአንተ ሁሌ ተጠግቼ
ኢቲሳ ትናገር አስተዳደግህን
ዳሞትም ትመስክር ጣዕም ስብከትህን
ታውራ አማራ ሳይንት ሕሙማን መፈወስህን
በፀሎተ ሚካኤል ደጅ ትህትና መዝራትህን
ደሞ መንበረ ሥላሴ የአጠንክባት ቦታ
በዛች ሐይቅ ደሴት ያረከው ታምራት
ምድሪቷን አረካት የጸባኦት ቦታ
ደብረ ዳሞ ወተህ ስትል ሃሌ ሉያ
አምላክህ ሸለመህ የመላዕክትን ክንፍ ደርቦ ደራርቦ
ጎብኝተህ ስትጨርሰ ገዳማትን ትግሬ
ለብሰህ ተጎናጽፈህ መልበሰ ዝማሬ
ሄድክ ቀራንዮ ሀገሩ ለህሬ
ሁሉንም ጨርሰህ መጣህ ደብር አስቦ
እኔስ ይገርመኛል የአንተ ተውሀቦ
በሁለት እግርህ ቆመህ የፀለይክባት ቦታ
ደሞም በአንድ እግርህ የቆምክባት ቦታ
በረከት ይገኛል ከማያልቀው ጸጋህ
ለዚህ ድንቅ ውለታህ አባቴ እንዴት ላመስግንህ
የኢትዮጵያም ምድር ውለታህ በዝቶባት እንዴት ታመስግንህ
ውለታህ በዛብኝ እንዴት ላመስግንህ
ታምረህ በዛብኝ እንዴት ላመስግንህ
ትርምትህ በዛብኝ እንዴት ላመሰግንህ:
@kinexebebe
https://www.tgoop.com/ShareGifts_bot/ShareGifts?startapp=r_394755665
💥I have already won $27.2!🎁 Get $120.00 Every Day💵 Earn $5 For Every Referral💰 Click the link Play for free and start earning!
💥I have already won $27.2!🎁 Get $120.00 Every Day💵 Earn $5 For Every Referral💰 Click the link Play for free and start earning!
ዘመን እንደዋዛ
🌼🌼🌼🌼
ሰከንድ ደቂቃውን ደቂቃ ሰዓቱን
እያደገ ሲሄድ ሰይገታ ጉዞውን
በዚህ ሳያበቃ ሰዓት ቀንን ወልዶ
ቀኑም ሳምንት ሲሆን ተሻግሮ ተራምዶ
ሳምንትም በተራው ወራትን ሲተካ
የተቦካው ሲያልቅ ተፈጭቶ ሲቦካ
ወራት ወደ አመታት በአንዴ ሲቀየሩ
እረፋት የለሽ ሰዓት ሲዞር መዝወሩን
እድሜዬ አብሮ ሮጠ አለፈ ዘመኔ
ጆሮዬ እየሰማ እያየኹት በዓይኔ።
ብልጭ ድርግም ስትል ያቺ ፈጣን ሰኮንድ
በእጄ ላይ አስርያት ተቀምጣ በእኔ ክንድ
እኔ ስስቅባት ፍጥነቷን እያየሁ
ምንድን አስቸኮለሽ አጣደፈሽ እያልሁ
ለካስ ምስጢር አላት ዘመን ትቆጥራለች
በእድሜ መቀለዴን ነጋሪ ኖራለች።
እኔ መች ተረዳሁ ምስጢሩ መች ገባኝ
እብድነች እላለሁ ለካስ እብዱ እኔ ነኝ።
ዛሬ ባስታውሰው ያለፈ ዘመኔን
የሰኮንድ ደቂቃ የሰዓት ምስጢሩን
የሳምንት የወራት የዓመታት ድምሩን
ለካ ሄዶብኛል
ዘመን አልቆብኛል
በራሴ ላይ ሆኖ ሞት ይስቅብኛል።
ልጠይቅ እራሴን ምን ሰራሁ በእድሜዬ❔
በኖርኩበት ዘመን በዚህ ቆይታዬ
አንድ ነገር ቀረቶኛል
ጭንቀት ይሰማኛል
ኑሮ እንዴት እንደሆነ ማሰብ ተስኖኛል
የእኔነቴ መሰረት አምላክ ከእኔ ርቋል።
አዎ❕አሁን ገባኝ ሁሉ የእድሜ አቆጣጠሩ
የሳምንት የወራት የዓመታት ምስጢሩ
ያለ ቅጽበት ዕረፍት በፍጥነት መብረሩ
ሰዓት በእርሷ ስስቅ ለካ ትስቃለች
እግሬን ወደ ጉድጓድ ይዛ ትሮጣለች።
እኔማ መች ገባኝ ቁም ነገር መሥራቷ
በሕይወቴ ዙርያ በእድሜ መጫወቷ።
ከአምላክ መለየቴ መች ተገለጸልኝ
እርቃኔን መቆሜን ማን አይቶ አለበሰኝ።
ውሃና ሳሙና ተቀምጦ በፊቴ
አድፌን ሳላስወግድ ድረስ ሰዓቴ
አይ ዘመን❕
አምላክ ለእኔ አስቦ ተጨንቆ ተጠበበ
ለንስሐ ብሎ ጊዜዬን ቆጥቦ
ምህረት ቢለግስኝ ወደ እረሱ እንድመለስ
እኔ ግን ዘነጋሁት መስቀሉን ማስታወስ።
እስኪ አንተም ንገረኝ
በይ አንቺም ንገረኝ
ዘመንህ እንዴት ነው❔
ዘመንሽ እንዴት ነው❔
የአጠቃቀም ስልቱ ዘዴው እንደምን ነው❔
በሃሜት በወሬ ወይስ በለቅሶ ነው❔
በወሬም ይቆጥራል
በሃሜት ይበራል
በፀሎትም ያልቃል
ከእንባ ጋር ይወርዳል
ጊዜማ መብረሩን መች አቁም ያውቃል።
ግን ቁጥሩ አንድ ቢሆንም ጥቅሙ ይለያያል።
እናም የእናቴ ልጅ ዘመንህን ተመልከት
ሃሜቱን ተውና ንስሐ ግባበት
ሃሜቱን ተይና ንስሐ ግቢበት
ኮንትራትህ ሲያልቅ ቁም ነገር ሥራበት
በላይ በሰማያት ስንቅን አስቀምጭበት።
በሉ አሁን ተነሱ ያለፈው ይብቃና
እኔም አንተም አንቺም ንስሐ እንግባና
ከአምላክ እንታረቅ
መንገዱን እንወቅ
ቀሪ ዘመናችን ከእርሱ ጋር ትዝለቅ።
፧፧፧ስብሐት ለእግዚአብሔር፧፧፧
✍ገጣሚ መምህር አለምቀረ ሙሉ
🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼@kinexebebe 🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
🌼🌼🌼🌼
ሰከንድ ደቂቃውን ደቂቃ ሰዓቱን
እያደገ ሲሄድ ሰይገታ ጉዞውን
በዚህ ሳያበቃ ሰዓት ቀንን ወልዶ
ቀኑም ሳምንት ሲሆን ተሻግሮ ተራምዶ
ሳምንትም በተራው ወራትን ሲተካ
የተቦካው ሲያልቅ ተፈጭቶ ሲቦካ
ወራት ወደ አመታት በአንዴ ሲቀየሩ
እረፋት የለሽ ሰዓት ሲዞር መዝወሩን
እድሜዬ አብሮ ሮጠ አለፈ ዘመኔ
ጆሮዬ እየሰማ እያየኹት በዓይኔ።
ብልጭ ድርግም ስትል ያቺ ፈጣን ሰኮንድ
በእጄ ላይ አስርያት ተቀምጣ በእኔ ክንድ
እኔ ስስቅባት ፍጥነቷን እያየሁ
ምንድን አስቸኮለሽ አጣደፈሽ እያልሁ
ለካስ ምስጢር አላት ዘመን ትቆጥራለች
በእድሜ መቀለዴን ነጋሪ ኖራለች።
እኔ መች ተረዳሁ ምስጢሩ መች ገባኝ
እብድነች እላለሁ ለካስ እብዱ እኔ ነኝ።
ዛሬ ባስታውሰው ያለፈ ዘመኔን
የሰኮንድ ደቂቃ የሰዓት ምስጢሩን
የሳምንት የወራት የዓመታት ድምሩን
ለካ ሄዶብኛል
ዘመን አልቆብኛል
በራሴ ላይ ሆኖ ሞት ይስቅብኛል።
ልጠይቅ እራሴን ምን ሰራሁ በእድሜዬ❔
በኖርኩበት ዘመን በዚህ ቆይታዬ
አንድ ነገር ቀረቶኛል
ጭንቀት ይሰማኛል
ኑሮ እንዴት እንደሆነ ማሰብ ተስኖኛል
የእኔነቴ መሰረት አምላክ ከእኔ ርቋል።
አዎ❕አሁን ገባኝ ሁሉ የእድሜ አቆጣጠሩ
የሳምንት የወራት የዓመታት ምስጢሩ
ያለ ቅጽበት ዕረፍት በፍጥነት መብረሩ
ሰዓት በእርሷ ስስቅ ለካ ትስቃለች
እግሬን ወደ ጉድጓድ ይዛ ትሮጣለች።
እኔማ መች ገባኝ ቁም ነገር መሥራቷ
በሕይወቴ ዙርያ በእድሜ መጫወቷ።
ከአምላክ መለየቴ መች ተገለጸልኝ
እርቃኔን መቆሜን ማን አይቶ አለበሰኝ።
ውሃና ሳሙና ተቀምጦ በፊቴ
አድፌን ሳላስወግድ ድረስ ሰዓቴ
አይ ዘመን❕
አምላክ ለእኔ አስቦ ተጨንቆ ተጠበበ
ለንስሐ ብሎ ጊዜዬን ቆጥቦ
ምህረት ቢለግስኝ ወደ እረሱ እንድመለስ
እኔ ግን ዘነጋሁት መስቀሉን ማስታወስ።
እስኪ አንተም ንገረኝ
በይ አንቺም ንገረኝ
ዘመንህ እንዴት ነው❔
ዘመንሽ እንዴት ነው❔
የአጠቃቀም ስልቱ ዘዴው እንደምን ነው❔
በሃሜት በወሬ ወይስ በለቅሶ ነው❔
በወሬም ይቆጥራል
በሃሜት ይበራል
በፀሎትም ያልቃል
ከእንባ ጋር ይወርዳል
ጊዜማ መብረሩን መች አቁም ያውቃል።
ግን ቁጥሩ አንድ ቢሆንም ጥቅሙ ይለያያል።
እናም የእናቴ ልጅ ዘመንህን ተመልከት
ሃሜቱን ተውና ንስሐ ግባበት
ሃሜቱን ተይና ንስሐ ግቢበት
ኮንትራትህ ሲያልቅ ቁም ነገር ሥራበት
በላይ በሰማያት ስንቅን አስቀምጭበት።
በሉ አሁን ተነሱ ያለፈው ይብቃና
እኔም አንተም አንቺም ንስሐ እንግባና
ከአምላክ እንታረቅ
መንገዱን እንወቅ
ቀሪ ዘመናችን ከእርሱ ጋር ትዝለቅ።
፧፧፧ስብሐት ለእግዚአብሔር፧፧፧
✍ገጣሚ መምህር አለምቀረ ሙሉ
🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼@kinexebebe 🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼
"ዘመኔን ባርኪልኝ!!"
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
እልዕፍ አመት ባወራ..... ቅኔ ብዘርፍልሽ
ምንም ቃል አጣሁኝ!..... በምን ልቀኝልሽ?
የሚስጥሬ ሙዳይ..... የሃሳቤ ብራና!
የደስታዬ ባህር.... የኑሮዬ ቃና!
ማርያም እመቤቴ.... የጌታዬ እናት
የአዲስ ተስፋ ብርሃን.... የሰማይ ጉልላት!
የአምላኬ ስጦታ.... ረቂቋ ማህደር
ፍቅርሽ ከልቤ ላይ....እንደዋለ ይደር!
ቢከፋኝ መፅናኛ..... ብጨነቅ ምሽጌ
በፍስሐው ዘመን..... መዋቢያ ማዕረጌ!
ፈጣሪ አክብሮሻል....መች አፍርብሻለው!
የክብሬ ሰንደቅ ነሽ!......"እኮራብሻለው!!"
እንዳለፈው ታሪክ......መንገዴን አፍኪልኝ!
ዛሬም በእቅፍሽ ነኝ!....."ዘመኔን ባርኪልኝ!"
🌻ከእህተ ማርያም
➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴
@kinexebebe
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
እልዕፍ አመት ባወራ..... ቅኔ ብዘርፍልሽ
ምንም ቃል አጣሁኝ!..... በምን ልቀኝልሽ?
የሚስጥሬ ሙዳይ..... የሃሳቤ ብራና!
የደስታዬ ባህር.... የኑሮዬ ቃና!
ማርያም እመቤቴ.... የጌታዬ እናት
የአዲስ ተስፋ ብርሃን.... የሰማይ ጉልላት!
የአምላኬ ስጦታ.... ረቂቋ ማህደር
ፍቅርሽ ከልቤ ላይ....እንደዋለ ይደር!
ቢከፋኝ መፅናኛ..... ብጨነቅ ምሽጌ
በፍስሐው ዘመን..... መዋቢያ ማዕረጌ!
ፈጣሪ አክብሮሻል....መች አፍርብሻለው!
የክብሬ ሰንደቅ ነሽ!......"እኮራብሻለው!!"
እንዳለፈው ታሪክ......መንገዴን አፍኪልኝ!
ዛሬም በእቅፍሽ ነኝ!....."ዘመኔን ባርኪልኝ!"
🌻ከእህተ ማርያም
➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴🌼➴
@kinexebebe
++ የአዲስ ዓመት ሥነጹሑፍ !!
( ይችን ዓመት ተወኝ ! )
ከዓመት እስከ አመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ፤
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ፤
አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እያጎሳቆልኩኝ፤
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬየን ለመልቀም እንዳመላለስኩህ፤
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅየ ደርቄ ጠበኩህ ፤
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም፤
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አልለየኝም ከአለም።
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ፤
የኔን ክፋት ተወዉ መልአክህን ሰምተህ ይችን ዓመት ተወኝ።
አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር፤
ብዙ ግዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር።
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይኸ ጊዜ ሰምተኸኝ ነበረ፤
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮየ አልፎ ባዲስ ተቀየረ ።
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ፤
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ።
የቃልህን ውሐ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳትታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ፤
ወደልቤ ሳይሰርግ ህይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈስሶ ቀረ።
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ፤
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ።
ብዙ ጥቅስ አገኝሁ ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ፤
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁንኝ በበደል ተኝቼ ።
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርጸኝ ተማሪ ብሆንም፤
ይችን ዓመት ተወኝ ተደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም።
እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ፤
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መአዛ እንዲደርሰኝ።
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሸከመኝ አትሰልቸኝ አደራ፤
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት እየሰሩ ስሰራ።
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ፤
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ።
ቦታ የሚይዙት ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸው፤
ልክ እንደዘንባባ የተንዠረገገ ተጋድሎ ጽድቃቸው ።
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው፤
እኔ አይደለሁም ቦታስ የምትይዘው የአንተው እናት ናት፤
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት፤
ይችን አመት ተወኝ ከስሯ እሆናለሁ ባፈራ ምናልባት፤
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት፤
ሺህ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ላንተ ዓመት ኢምንትህ ናት።
ይኸ ዓመት አልፎ ደግሞ ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ፤
እባክህ ጌታየ ይችን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ።
ጸሐፊ - (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

የፀሎቴ አላማ🙏
አንተ የሰማዩ የምድሩ ጌታ
ካንተ ሌላ የለኝ አንተ ነህ አለኝታ
ከሁሉ ብቸኛ የምትሆን መከታ
እጆቼን ዘርግቼ በጠዋት በማታ
አንተኑ ልለምን ለብቸኛው ጌታ
በጣም ተፀፅቼ በሰራሁት ወንጀል
በፊትህ ቆሚያለው ምህረት በመከጀል
ይቅር ባይ ነህና(2) አጥያቴን ማርልኝ
የሁለቱም ሀገር ኑሮ እንዲያምርልኝ
በምድር ስኖር ሲገጥመኝ ፈተና
ታጋሽም እንድሆን በርትቼ እንድፀና
ፍቅር እንድትሰጠኝ በሰዎች መካከል
በሀጥያት ወድቄ እንዳልሰናከል
በትዕዛዝህ ልቁም በመልካም ጎዳና
በፀጋህ እንድጓዝ በመልካም ደመና
እባክህ ጌታዬ ልቤን ላንተ አስገዛት
ነብሴንም ውሰዳት ላንተ ብቻ አድርጋት
አንተ ታላቅ እሳት
እኛን ለማዳን በለበስካት
በእናትህ በድንግል ማርያም
በክብር ያለህ በአርያም
ፀሎቴም ይቺሁ ናት አባቴ አደራ
በላይ በሰማያት በበደል መዝገብ ስሜ እንዳይጠራ
አስተዋይ ልብ ስጠኝ አንተን እንድፈራ
✍️ገጣሚ ዘላለም ታደሰ
@kinexebebe
አንተ የሰማዩ የምድሩ ጌታ
ካንተ ሌላ የለኝ አንተ ነህ አለኝታ
ከሁሉ ብቸኛ የምትሆን መከታ
እጆቼን ዘርግቼ በጠዋት በማታ
አንተኑ ልለምን ለብቸኛው ጌታ
በጣም ተፀፅቼ በሰራሁት ወንጀል
በፊትህ ቆሚያለው ምህረት በመከጀል
ይቅር ባይ ነህና(2) አጥያቴን ማርልኝ
የሁለቱም ሀገር ኑሮ እንዲያምርልኝ
በምድር ስኖር ሲገጥመኝ ፈተና
ታጋሽም እንድሆን በርትቼ እንድፀና
ፍቅር እንድትሰጠኝ በሰዎች መካከል
በሀጥያት ወድቄ እንዳልሰናከል
በትዕዛዝህ ልቁም በመልካም ጎዳና
በፀጋህ እንድጓዝ በመልካም ደመና
እባክህ ጌታዬ ልቤን ላንተ አስገዛት
ነብሴንም ውሰዳት ላንተ ብቻ አድርጋት
አንተ ታላቅ እሳት
እኛን ለማዳን በለበስካት
በእናትህ በድንግል ማርያም
በክብር ያለህ በአርያም
ፀሎቴም ይቺሁ ናት አባቴ አደራ
በላይ በሰማያት በበደል መዝገብ ስሜ እንዳይጠራ
አስተዋይ ልብ ስጠኝ አንተን እንድፈራ
✍️ገጣሚ ዘላለም ታደሰ
@kinexebebe
አፍቃሪዬ🥰
የምር የወደደኝ በልቡ የሾመኝ
ለአይኖቼ ብሌን ብርሐን የሆነኝ
እውነተኛ ፍቅሩን በደሙ ያሳየኝ
አፈቀርኩህ ብሎ መልሶ ያልተወኝ
ከ መ
ድ
ሐ
ኒ
አ
ለ
ም
ሌላ አፍቃሪ የት አለኝ
ፍቅሬ እጅግ ጨመረ ናፍቆቴም በረታ
ናልኝ መንፈስ ቅዱስ ናልኝ የኔ ጌታ
✍️ገጣሚ ዘላለም ታደሰ
@kinexebebe
የምር የወደደኝ በልቡ የሾመኝ
ለአይኖቼ ብሌን ብርሐን የሆነኝ
እውነተኛ ፍቅሩን በደሙ ያሳየኝ
አፈቀርኩህ ብሎ መልሶ ያልተወኝ
ከ መ
ድ
ሐ
ኒ
አ
ለ
ም
ሌላ አፍቃሪ የት አለኝ
ፍቅሬ እጅግ ጨመረ ናፍቆቴም በረታ
ናልኝ መንፈስ ቅዱስ ናልኝ የኔ ጌታ
✍️ገጣሚ ዘላለም ታደሰ
@kinexebebe
ወዲያው ወዲያው የሚከፍል ነው ሞክሩት
https://www.tgoop.com/ShareGifts_bot/ShareGifts?startapp=r_394755665
💥I have already won $33.3!🎁 Get $120.00 Every Day💵 Earn $5 For Every Referral💰 Click the link Play for free and start earning!
https://www.tgoop.com/ShareGifts_bot/ShareGifts?startapp=r_394755665
💥I have already won $33.3!🎁 Get $120.00 Every Day💵 Earn $5 For Every Referral💰 Click the link Play for free and start earning!
""ጳጉሜ/ ጾመ ዮዲት እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!""
ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል ትታወቃች ፡፡
ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡
እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ (ዮዲ.፪፥፯)፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ.፰፥፪፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡
ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንልን አሜን
T.me/kinexebebe

Telegram
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ
ይህቺን ዓመት ተወኝ
ከዓመት እስከ ዓመት ፍሬን ሳላፈራ ደረቅ እንደሆንኩኝ
በራድ ወይም ትኩስ ሁለቱንም ሳልሆን እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ ፤
አለሁኝ በቤትህ ለሙን መሬትህን እያጎሳቆልኩኝ ፤
አውቃለሁ አምላኬ ፍሬዬን ለመልቀም እንዳመላለስኩህ ፤
ዛሬም ሳላፈራ እሾህን አብቅየ ደርቄ ጠበኩህ ፤
ያልተደረገልኝ ያላፈሰስክብኝ ያልሰጠኸኝ የለም ፤
ነገር ግን ይህ ሁሉ አላርምህ አለኝ አልለየኝም ከዓለም
የማትሰለቸኝ ሆይ ተነስቼ እስክቆም እባክህ ታገሰኝ ፤
የኔን ክፋት ተወው መልአክህን ሰምተህ ይችን ዓመት ተወኝ ።
አውቃለሁ ታውቃለህ ቀጠሮን ሰጥቼ እንደማላከብር፤
ብዙ ግዜ አቅጄ ብዙ ጊዜ ዝቼ በወሬ እንደምቀር ።
ዘንድሮስ እንዳልኩኝ አምና ይኼን ጊዜ ሰምተኸኝ ነበረ፤
ምንም ሳልለወጥ ዘንድሮዬ አልፎ በአዲስ ተቀየረ
ፍሬ የማይወጣኝ እኔን በመኮትኮት እጆችህ ደከሙ ፤
እኔ ግን አለሁኝ ዛሬም አልበቃኝም በኃጢአት መታመሙ ።
የቃልህን ውሃ በድንጋይ ልጅህ ላይ ሳትታክት ስታፈስ ዘመን ተቆጠረ ፤
ወደልቤ ሳይሰርግ ህይወቴን ሳይለውጥ እንዲያው ፈስሶ ቀረ
ቃልህን ጠግቤ እያገሳሁት ነው ሌሎች እስኪሰሙ ፤
በቃልህ መኖር ግን አልያዝህ አለኝ ከበደኝ ቀለሙ ።
ብዙ ጥቅስ አገኝሁ ከቅዱስ መጽሐፍህ ገልጬ አይቼ ፤
ከራሴ ላይ ብቻ አንድ ጥቅስ አጣሁንኝ በበደል ተኝቼ ።
ውጤቴ ደካማ ትምህርት የማይሰርጸኝ ተማሪ ብሆንም ፤
ይችን ዓመት ተወኝ ደግሞ ትንሽ ልማር ታገሰኝ አሁንም ።
እባክህ አልቆረጥ በቅዱስ መሬትህ ልቆይ ፍቀድልኝ ፤
ያፈሩት ቅዱሳን የፍሬያቸው ሽታ መዓዛ እንዲደርሰኝ ።
የተሸከምከኝ ሆይ ዛሬም ተሸከመኝ አትሰልቸኝ አደራ ፤
ማን ይታገሰኛል ጠላት እየሆንኩት እይሰሩ ስሰራ ።
አታውጣኝ ከቤትህ ብዙ ቦታ አልይዝም ፍሬ ስለሌለኝ
ስፍራ የማያሻኝ ቤት የማላጣብብ ፍሬ አልባ በለስ ነኝ ።
ቦታ የሚይዙት ባለምግባሮቹ ቅዱሳንህ ናቸው ፤
ልክ እንደ ዘንባባ የተንዠረገገ ተጋድሎ ጽድቃቸው ።
ከሊባኖስ ዝግባ እጅጉን የበዛ ገድል ትሩፋታቸው ፤
እኔ አይደለሁም ቦታስ የምትይዘው የአንተው እናት ናት ፤
ስሮቿ በምድር ጫፎቿ በሰማይ ሲደርሱ ያየናት ፤
ይህቺን ዓመት ተወኝ ከስሯ እሆናለሁ ባፈራ ምናልባት ፤
ይቺን ዓመት ተወኝ እባክህ አምላኬ አንድ ዓመት ምንህ ናት ፤
ሺህ ዓመት አንድ ቀን አይደለም ወይ ለአንተ ዓመት ኢምንትህ ናት ።
ይኸ ዓመት አልፎ ደግሞ ዓመት ስጠኝ እስከምልህ ድረስ ፤
እባክህ ጌታየ ይችን ዓመት ተወኝ የወጉን እንዳደርስ ።
@kinexebebe
✍️ ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ

የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1636545295560576&inviterId=1045664158336008&language=am&campaignType=collectPetal&time=Sept-04-2024-Sept-12-2024
🌼 "የዕንቁጣጣሽ" ሥያሜ አመጣጥ?
ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡
በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡
ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡
አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።" (ራእይ 21፥5)
#ውድ_የተዋህዶ ልጆች_የቻናሎቼ_ተከታዮች
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወደዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ::
ቀን እና ሌሊትን
ሳምንታትን እና ወራትን
አመታትን እና አዝማናትን እያፈራረቀ በዕድሜያችን ላይ ዕድሜን ጨምሮ ለአዲሱ ዘመን ያደረሰን ከዘመናት በፊት የነበረ ዘመናትንም አሳልፎ የሚኖር ለህላዌው ዘመን የማይቆጠርለት ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለማይነገር ስጦታው እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
አዲሱ አመት ዘመን የምንቀይርበት ብቻ ሳይሆን እኛም ተቀይረን ለክብር የምንበቃበት ይሁንልን።
ብዙዎች ይቺን ቀን ለማየት ናፍቀው ያላዩ በሞት የተጠሩ አሉ።
ብዙዎች በህመም በየ ሆስፒታሉ በየፀበሉ ያሉ አሉ።
በመከራ በስቃይ በችግር ውስጥ ያሉ አሉ እኛን ግን እግዚአብሔር ነብዩ 'በቸርነትህ' አመታትን ታቀዳጃለህ'' (መዝ 65:11) ብሎ አንደተናገረው በስራችን ሳይሆን በቸርነቱ አዲሱን አመት ያሳየን ቸሩ አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።
ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያው መልእክቱ ምዕራፍ 4-3 ላይ
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።”
ብሎ ባለፈው ዘመን ከኖርንበት የኃጢአት መንገድ እንድንመለስ ያስተምረናል::
እኛም ከክፋት፣ከተንኳል፣ከመከፋፈል በጠቃላይ ከክፉ ተግባር ርቀን እግዚአብሔርን የምናስደስትበት ዘመን ያድርግልን።
ዲ/ን ተረፈ ተስፋዬ ነኝ።
@ty1921
@webzema @menefesawinet @kinexebebe @yedawit_begena @amantaakoo @yeberhanljoche @esxifanose

Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?
📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ እዲውም
እና የሌሎችንም ...........
ዘማሪዎች መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
👇👇👇👇
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◥
➣ ➤ JOIN US
█◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
10+10×0+10=???
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!
10+10×0+10=???
#ስዕል
ብዙ ጊዜ ሰዎች እኛ ኦርቶዶክሳውያንን '' እናንተኮ ለስዕል የምትሰግዱ ስዕል አምላኪዎች ናቹሁ '' ይሉናል። ግን እውነት ነው? አይደለም። እኛ ለስዕሉ ማለትም ስለዕሉ ለተሳለበት ቀለም፣ ስዕሉ ላረፈበት አቡጀዴ( ሸራ)ና ለፍሬሙ አንሰግድም። ግን በስዕሉ በኩል ለስዕሉ ባለቤቱ እንሰግዳለን። ይህም ስግደት የአምልኮ ወይም የጸጋ (የክብር) ተብሎ ይከፈላል። የአምልኮው ስግደት ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ የሚቀርብ ነው። የጸጋ ስግደት ደግሞ ለቅዱሳን መላእክትና ሰዎች የሚቀርብ ነው።
ቅዱሳን ስዕላት ከሌሎች ስዕላት የሚለዩት ቅዱስ በሚለው ስማቸው፤ በመንፈሳዊ አገልግሎታቸና ፈውስን በመስጠታቸው ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ በቁስ ላይ አድሮ ተኣምር እንደሚሰራ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ እውነት ነው። ለምሳሌ ጌታችን በልብሱ እንዱሁም ቅዱስ ጳውሎስም በልብሱ በሽተኛዎችን እንደፈወሱ ስንመለከት የእግዚአብሔር መንፈስ በቁስ ላይ እያደረ ተአምራትን እንደሚሰራ እንገነዘባለን። በቁስ ደረጃ ደግሞ ስዕልም ጨርቅም አንድ ናቸው ፤ የተሰሩበት ግብአት ቢለያይም። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንፈስ በስዕል ላይ አድሮ ተአምር አይሰራም ማለት ስህተት ነው።
ለመሆኑ በስዕል የተፈወሰ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት እንችላለን? አዎ እይታችንን ካስተካከልን እንችላለን። ለምሳሌ እንዲህ የሚል ቃል አለ :-: " ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ #ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን #ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር። ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።"
(ሐዋ 5:15-16)
ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው በሽተኛ ይፈውስ ነበረ። ጥላ ምንድነው? ጥላ በመሰናክል አካል ምክንያት ብርሀን የማያገኝ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ብርሀን አስተላላፊ ካልሆነ አካል በስተጀርባ ይገኛል። #ይህ_ጥላ_የሚፈጥረው_ቅርፅ_ብርሀን_እንዳያልፍ_ያደረገውን_አካል_ግልብጥ_ምስል_ነው ። ማለትም ራስኑን ቅርጽ በጥቁር ቀለም መልክ ማለት ነው።
ጥላን ወደ ስነ-ጥበብ ስንመጣው ደግሞ Shadow Art በሚባል የአሳሳል ጥበብ እናኘዋለን። ጥቁር ቀለምን ብቻ በመጠቀም አንድን አካል አስመስሎ የመሳል ጥበብ ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ልክ እንደ Shadow art ነው በተፈጥሮ ብርሃን በምደር ላይ የተሳለ ፥ ይህንን ጥቁር ጥላ ከነቅርጹ በደንብ ሙያ ተጨምሮበት በቀለም አሳምሮ በመሳል የባለቤቱን ገጽታ ማምጣት ይቻላል። በመሬት ላይ ያረፈው ጥላ መፈወሱ ፤ በክብር በሸራና በተለያዩ አካላት ላይ ምሥጢርን፥ ሥርአትን ጠብቀው የተሳሉ ስዕላት እንደሚፈውሱ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ነው።
ይቆየን።