tgoop.com/kunuzil8jenah/3905
Last Update:
1,እንኳን ተኝተህ ነቅተህም ትሔዳለህ
«أَلَيْسَ الصُّبْحُ بِقَرِيبٍ»
«ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» [ሁድ:81]
አንዲት በዕድሜዋ ጫፍ የደረሰች እንስት በሕይወቷ ያለፈችበትን በጸጸት ስሜት በማስተወሻ ደብተሯ ላይ እንዲህ ስልት አስፍራለች፦
«ልጅ እያለሁ 'እንደ ጓደኞቼ ትልቅ ሆኜ መች ይሆን የምገባው!' እያልኩ እጓጓ ነበር። እንደተመኘሁትም ጊዜው ደርሶ ትምህርት ቤት ገብቼ የልጅነት ጊዜዬን አሳለፍኩ። ከዚያ ብዙ መቆየቴ ስላሰለቸኝ፣ 'መቼ ይሆን ዩኒቨርስቲ መግባት የምችለው!' ብዬ አስብ ነበር። እንደተመኘሁትም በተግባር ገባሁ። ነገር ግን ከሱም ቢሆን በመሰላቸቴ ተመርቄ የምወጣበትን ዕለት በናፍቆት እጠብቅ ጀመርኩ። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተመርቄ ወጣሁ። ወደ ቤት ስገባ ነጠላነቴ ተሰማኝ። ስለዚህም ማግባት እንዳለብኝ ወሰንኩ። ብዙም ሳልቆይ አገባሁ። ነገር ግን ቤቱ በጭርታ የተሞላ ሆነብኝ። አላህ ልጆች በሰጠኝ ብዬ ተመኘሁ። ብዙም ሳልቆይ የልጆች እናት ለመሆን በቃሁ። ነገር ግን በቤት ውስጥ መዋል በጣም አስጠላኝ። እናም በተማርኩት ዘርፍ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ። ከዚያም የራሴ ቤት እንዲኖረኝ ተመኘሁ። ምኞቴም ተሳካ። ነገር ግን ልጆቼ ያደጉ በመሆኑ ሁሉም እያገቡ አንድ ባንድ እያገቡ ወጡ። ከጊዜ ቡሀላ በተቀጠርኩበት ስራ ተሰላቸሁና ጡረታ ወጣሁ። ከዚያም በቤት ውስጥ መዋል ስጀምር ከተመረኩ በኋላ እንደነበረው ህይወቴ ብቸኝነት ዳግም ያሳድደኝ ጀመር። ነገር ግን ያን ጊዜ ፊቴን ለሕይወት ያዞርኩ ወጣት ነበርኩ። አሁን ግን ዕድሜዬ ወደ አመሻሹ ላይ በመሆኑ ለሕይወት ጀርባ ሰጥቻለሁ። ያለፈው ሕይወቴን እንዴት በፍጥነት እንዳለፈ ከአንዱ የሕይወት እርከን ወደ ሌላው እየተሸጋገርኩበት ከመሆኑ በስተቀር ትርጉም ያለው ነገር አይሰማኝም። ይሁንና አሁንም ቢሆን ሙጣጭ ጊዜና ተስፋ አለኝ። እናም ቁርአንን በቃል ለማጥናት ተመኘሁ፤ ነገር ግን በዕድሜዬ ሳቢያ የማስታወስ ችሎታዬ ከድቶኝ አገኘሁት። ለአላህ መጾም ፈለግኩኝ፤ ሆኖም ግን ጤንነቴ እንደማይፈቅድልኝ ተረዳሁ። የሌሊት ሰላት መስገድ ፈለግኩ፤ ይሁንና እግሮቼ ሊሸከሙኝ አልቻሉም። ጊዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባኝ በጣም ዘግይቴ ነበር!....» (ቂሰቱን ወሒካያ/141/)
ታሪኩ የሚነግረን በጊዜ ውስጥ የምናልፈው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑንና ዳግም እድል የማይሰጠን መሆኑን ነው።
.
.
.
ይቀጥላል
=======
ምንጭ፦ የማር ጠብታ ከሚለው መፅሀፍ
========
join our telegram channel for more topic
https://www.tgoop.com/Humanity02H
BY كنز من كنوز الجنة
Share with your friend now:
tgoop.com/kunuzil8jenah/3905