tgoop.com/manbabemuluyadergal/1963
Last Update:
ስንቶቻችን ይህን ግጥም እናስታውሳለን? ድራማው ቀድሞ በግጥም በመነገሩ ካመነው ይልቅ ያላመነው ነበር የበዛው።
አብይና ጸዲ
አንድ ዓይነት ባይሆንም - ለእኛ የሚያወሩት፣
ሲደዋወሉ ነው - ግልጹን ሚናገሩት።
እኛጋ ባይደርስም - በድንገት ተጠልፎ፣
አገኘን ወሬውን - በግጥም ተጽፎ።
ጸዲ ተማጸነ - አብይን ፈልጎ፣
ከኢትዮጵያ ጣቢያ - ደብቆ ሸሽጎ።
የላከው ደብዳቤ - ተሽሎ ካለፈው፣
ለስለስ አድርጎ ነው - መልዕክቱን የጻፈው።
እስቲ ላካፍላችሁ - የተባባሉትን፣
ድንገት ተልኮልኝ - እኔ ያነበብኩትን።
ጸዲ፡ አይበቃም ወይ ዱላው - እየተዋወቅን?
ለሁለት ተያይዘን - በትግል አለቅን።
አብይ፡ ቆየ ከነገርኩህ - እጅህን ስጥና፣
መቃወምን አቁም - የእኔን ብልጽግና።
ጸዲ፡ የአንተ ብልጽግና - ሥልጣኔን ወስዶታል፣
ህገ መንግስቱን ግን - አለቅም ብሎታል።
አብይ፡ ሥልጣን በቃኝ ብላ - ወደ እኔ መጥታለች፣
አታያትም በቃ - ከእጅህ አምልጣለች።
የያዝኩት አጥብቄ - ከወያኔ ወስጄ፤
ህገ መንግስቱን ነው - ማየው እንደ ልጄ።
በእሱ የተነሳ ነው - እዚህ የደረስኩት፣
እኔም ተራዬ ነው - መፍታት እንደቻልኩት።
ጸዲ፡ እኛው አሳድገን - በገዛ ቤታችን፣
ተወረሰ በአንተ - ሁሉ ንብረታችን።
አንተን ለማስወጣት - ከቤታችን ቶሎ፣
አይቀር እንመጣለን - እዛው አራት ኪሎ።
አብይ፡ ሞክራችሁ ነበር - ደርሳችሁ ደርሳችሁ፣
ቡና ሳትጠጡ - ምንድን መለሳችሁ?
እንደው በድጋሚ - ከምትለፉ ብዬ፣
መጣሁ ወደ እናንተ - ጦሬን አስከትዬ።
በሰላም አስገቡኝ - ብዬ ስነግራችሁ፣
አራት ዓመት ሞላኝ - እምቢ እንዳላችሁ።
በቀረበ እርቀት - መቀሌ ይታየኛል፣
እዛ መደበቂያ - ዋሻ የት ያገኛል?
ጸዲ፡ "አወይ አንተ ግደፍ" - ልቤን አታስቆጣ፣
ከተደበቅኹበት - ወጥቼ እንዳልመጣ።
አብይ፡ ከተደበቀበት - ጸዲን ወጥቶ ካየሁ፣
እኔ በበኩሌ - እጅግ በጣም ቆየሁ።
ይልቅ እጅህን ስጥ - አቁም ጦርነቱን፣
በቃን ማለት እወቅ - ተቀበል ሽንፈቱን።
ጸዲ፡ ቦታ ካላገኘን - ካልተጋራን ሥልጣን፣
እንታገላለን - ናና አንተ አስወጣን።
አብይ፡ አይቀርም ይሆናል - ወንበሬን የሚሻ፣
እኔ አሳጣዋለሁ - መግቢያና መድረሻ።
በአንተ ካላሳየሁ - ሌላው አንተን አይቶ፣
ይኮርጅ ይሆናል - ትዕቢትህን ቆይቶ።
ጸዲ፡ ዝም ያልካቸው ሰዎች - የተማሩት ከእኔ፣
ይባሉ አይደለም ወይ - ዛሬ ኦነግ ሸኔ።
አብይ፡ ከሃዲዎች ናቸው - አይቀርም ለእነሱ፣
ምቀጣበት በትር - በፍጥነት መድረሱ።
ጸዲ፡ እሱን እንኳን ተወው - በእነሱ ጭፍጨፋ፣
የስንቱ አማራ - ምስኪን ሕይወት ጠፋ።
አብይ፡ አስመሳይ ነህ አንተ - አማራን ገለኸው፣
ሌላ ታወራለህ - የአንተን ሸፍነኸው።
ጸዲ፡ ሁለታችንም ነን - አማራን ምንጠላው፣
ሥልጣን እንዳይቀማን - ቀድመን የምንበላው።
አንተም ልክ እንደ እኛ - አማራን ጥለሃል፣
ባስተማርንህ መንገድ - ማስወገድ ይዘሃል።
እየተባባሉ - ክርክር ቢያበዙም፣
መፍትሄ የሚሆን - ምንም ፈርጥ አልያዙም።
በአማራ የተነሳ - ምስጢር ሳያወጡ፣
ከመገናኛቸው - ከመስመሩ ወጡ።
መክብብ
September 27, 2022
BY የመፅሐፍ አለም 🇪🇹🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/manbabemuluyadergal/1963