tgoop.com/meazasenay/5289
Last Update:
😥ገዳም እንሂድ...ይለኛል ወንድሜ።ዘማነቴን አያውቀውም። ሴሰኝነቴ አይገባውም።እኔ በምናብ ከፈጠርኳት ሴት ጋ ቀን ከሌት በራሴ አለም ስዳራ የኖርኩ መሆኔን ቢያቅብኝ እንኳን ገዳም አብሮኝም ቆሞ ለመታየት ያፍርብኝ ነበር አንተ ያሬድ ተነስ ሰአቱ እረፈደ ነው። ውጣ እንጂ...አለ።(ዛሬ የቁርጥ ቀን ነው።ገዳም ከመሄዱ በላይ የሚፈታተነኝን ግለ ወሲብ የት ጥዬው እንደምሔድ ጨንቆኝ ስገላበጥ ነው ያደርኩት እ....እሺ ይኸው ወጣሁ(ቦርሳዬን ሸክፌ ተከተልኩት።ለአመታት ልወጣበት ካልቻልኩት ድብቁ ሱስ የሚገላግለኝ ሀይል እንደሌለ አምኛለሁ። ተውኩት ስል እየመጣ፤ የሀጥያት ሀፍረት ሲያከናንበኝ ለአመታት ቆይቶብኛል።አንዳንዴ ግልግል ማለትም ያምረኛል.... ሰውዬ ውረድ እንጂ ምነው ዛሬ ፈዘካል....ከረጅም የፒስታ መንገድ በኋላ በጫካ የተከበበች መሀሪት ማርያም ቤተክርስትያን ደረስን።ጫማ ማድረግ የለም።ምግብ የለም። ስልክ አይገባም።ንሰሐ ሳይገቡ መውጣት...(ገና ከበሩ የግቢው ዘብ ህጉን ሲዘረዝረው ልቤ እንደ ሰም ቀለጠች።ስልኬ ላይ በድፍረት የተሸከምኳቸው የነውር ምስሎሽ በአይኔ እየዞሩ ስልኬን አስረክቤ ወንድሜን ተከትዬ ገባሁ...... "አረ አለም በምን ጣዕሟ" እያልኩ እያማረርኩ ነበር የመሸልኝ።ከተማ ጥዬው የመጣሁት ዝሙት ገዳም ስገባ ጭራሽ ያቅበዘብዘኝ ይዟል።ከፀሎቱ ይልቅ ዝሙት አእምሮዬን ወጥሮት የአንድ ሰአቱን ፀሎት እንደጨረስን ስሮጥ ወደ ጫካው ወረድኩ።ሱሴን ላስታግስ...በዝሙት ልወድቅ....እንደገና ደጁ ልበድል...... ሱሪህን ፍታው....!! አረ ተው ፈጣሪን ፍራ!! እዚህ ጨለማ ማን እንዳያይህ ነው!? ከውስጤ ጋ ትግል እየገጠምኩ ከተራራው ቅጠል እያንኮሻኮሸ የሚወርድ የአውሬ ድምፅ ስሰማ ሱሪዬን እየጎተትኩ ወደ ማደሪያው አመለጥኩ...... ጎረምሳው ና እስቲ እቺን ውሀ አድርስልኝ...(ከኪዳን ስንመለስ ጎልመስ ያሉ መለኩሴ ከሰው መሀል ጠሩኝ እሺ አባቴ ችግር የለም..... ባዶ እግሬን ሸንከል እያልኩ ለመለኩሴው ውሀውን በሩ ላይ አድርሼላቸው እንደዞርኩ ሳትገባማ አትሄድም።ና ግድ የለም ጦም ቢሆንም ትንሽ እረፍት አድርግ..... ኦና የሆነ።ጨለማ የወረሰው ቤት ተከትያቸው ገባሁ።እጣን እጣን ይሸታል።በቆርቆሮው ቀዳዳ የሚገባው ጨረር ቀይ ረጅም መጋረጃቸው ላይ ስላረፈ የሚታየው እሱ ብቻ ነው።የተደገፍኩበት ግድግዳ በምርጊት የቀረ የጭቃ ቤት መሆኑ ያስታውቃል።መሬቱም አባጣ ጎርባጣ አቧራማ መሆኑ እግሬ በዳበሳ ሰልሎታል.... ልጅ ያሬድ ተጫወት (አሉ ከጨለማ ውስጥ ለስለስ ያለ ድምፅ አውጥተው በስመአብ ወወልድ።አማተብኩ።ፈራሁ።ስሜን ማን ነገራቸው...??? አይዞህ እንግዲህ የመለኩሴ ቤት።እስቲ እቺን ገመድ ያዛት ልጄ አሉ ጨረሩ እጃቸው ላይ ሲያርፍ አረንጓዴ ገመድ አይቼ ተቀበልኳቸው ምን ላድርገው አባ??? አንገትህ ውስጥ አጥልቀው አልገባኝም።ለምን??ልላቸው ብዬ ገዳም መሆኑ ትዝ ብሎኝ እጄ እየተንቀጠቀጠ አንገቴ ውስጥ ከተትኩት።የሆነ ነገር ነብሴን እየጨነቃት ገመዱ እየተሳበ እየጠበቀ ሲመጣ ይታወቀኛል..... አ....አባ ም...ምንድነው??አልኳቸው የሞት ሞቴን ትንፋሽ እያጠረኝ ።እሳቸው ጋ ግን ከማጥበቅ ውጪ መልስ የለም አባ እያነቁኝ ነው።ገመዱን አስለቅቁኝ አባቴ.....(መልስ የለም አባ ልሞት ነው...(ትንፋሼ እየተቆራረጠ በግድ አወራሁ።ገመዱ እየገዘገዘኝ ደምስሬ እየተወጠረ የጣሬን ገመዱን ይዤ በመጨረሻ አቅሜ... አ....አባ (ስል ገመዱ ድንገት ሲረግብ እኩል ሆነና ትንፋሼን እየለቀቅኩ ተነስቼ ለማምለጥ ቃጣኝ ቁጭበል!! እንዴ ምንድነው ከኔ ሚፈልጉት?? ምን አድርግ ነው ሚሉኝ ቆይ.... ምንም አላልኩህም።ሞት እንዴት እንደሆን በትንሹ ላሳይህ ብዬ ነው።ልጅ ያሬድ ከመጣህ ቀን ጀምሮ አውቅሀለሁ ወንድምህ አንተን እዚህ ሲያመጣህ ተማክረን ነው።አየህ በመጀመርያ ቀን ንሰሐ ግባ ሲልህ አሻፈረኝ ብለካል ነገሩ በግድ ስለማይሆን ተውንክ።አንተ ግን ሌላ በደል.... ሌላ በደል!??? አዎ እንግዲህ እዚ ድረስ መጥተህ ከምትጠፋ ብነግርህ ይቀላል።ያንተን ችግር እኔም ወንድምክም እናቀዋለን።ባለፈው በለሊት ጫካ ውስጥ ከራስህ ስትታገል እንደ አውሬ ጩኼ ያባረርኩህ እኔ ነኝ።አስተውል ያሬድ ቅድም ገመዱን ስሰጥህ ቀለል አርጌ ነበር ሸምቀቆው እየጠበበ ሲመጣ ግን መተንፈስ አቃተህ።ግለ ወሲብም እንዲህ ነው።በተዘዋዋሪ በቀላሉ ትገባበትና እየጠበቀ ሲመጣ ግለ ሞት እራስን በፈቃደኝነት በነብስም በስጋም ማጥፋት ይሆናል።እራስህን ብቸኛው ሀጥያተኛ አድርገህ አታስብ ከመድሀኒቱ ቀድመህ ስለበሽታው ካላወቅክ አትድንም።መተፋፈሩ ይበቃል ከዚህ በላይ ሰይጣን እንዲያዋርድህ አትፍቀድ።ለመንፃት ሳትሰለች ተጠመቅ ንሰሐ ግባ ሰይጣን የደበቅክለትን ነውሩን በእግዜር ፊት ስትገልጥበት እግዚአብሔር ደሞ ከሰይጣን የዘማዊነት አሰራር ይከልልካል።አሁንስ ልጅ ያሬድ ምን ትለኛለህ አባ ለንሰሐ መች ልምጣ...እንዲ መሞት አልፈልግም።(ሲሰንፍ የነበረው ልቤ ያዋረደኝን ሰይጣን ለመጣል ሲነሳሳ ለእግዜር ደሞ ሲብረከረክ ተሰማኝ የመዳን ቀን ዛሬ ነው ልጄ ከመጣህ አሁኑኑ ሀጥያትህን ተናዘህ ሂድ...
ለብዙ ሰው ይጠቅማል #ሼር
https://www.tgoop.com/meazasenay
BY መዓዛ ሠናይ
Share with your friend now:
tgoop.com/meazasenay/5289