tgoop.com/medrekenean/399
Last Update:
በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ✅
በእደ ገብሩ ቆሞስ፣ በእደ ገብሩ መምህር፣ በእደ ብፁዕ ሊቀጳጳስነ፣ በእደ ክቡር መምህር❎
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በልክ እና በመልክ የተሠራ ሥርዓተ አምልኮ አላት፤ ሦስት መዓርጋተ ክህነትም አላት
እነርሱም
1 ድቁና
2 ቅስና
3 ጵጵስና
ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው በፍጹም ትሕትና ሁነው የሚያገለግሉባቸው መደቦች አሏቸው። ወደሰፊው ዝርዝር ሳልገባ ወተነሣሁበት ርእስ ለመመለስ ላሳጥረው።
የዲያቆናት አገልግሎት ተልዕኮ እና ማስተማር
የቀሳውስት ማስተማር ማጥመቅ ማቁረብ መናዘዝ መባረክ
የጳጳሳት ማስተማር ማጥበቅ ማቁረቡ መናዘዝ መባረክ ሌሎችን መሾም ነው።
ምእመናን ደግሞ ተሠጥዎ አላቸው መቀበል ማለት ነው።
ቄሱ ወይም ጳጳሱ ሊለው ከሚገባው ቦታ ላይ መጽሐፉ ይበል ካህን/ይካ ይላል
ዲያቆኑ ሊለው የሚገባው ቦታ ላይ ይበል ዲያቆን/ይዲ ይላል።
ምእመናን በሚቀበሉበት ቦታ ላይ ይበሉ ሕዝብ/ይሕ ይላል።
አገልግሎቱ የሚመራው በዚህ ነው። አሁን አሁን ግን በከተሞች አካባቢ የምንሰማው ነገር መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑ ቀርቶ መሞጋገሻ አስመስሎታል።
አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ፤
ትርጉም፦ በአገልጋዩ በካህኑ እጅ ይባርከን ዘንድ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
በሚለው ቦታላይ
አንዳንዱ ያልተጻፈውን በእደ ብፁዕ ሊቀጳጳስ ከመ ይባርከነ ይላል
ለጳጳሳቱኮ ገብረ እግዚአብሔር መባል ታላቅ ክብር ነው እነ ቅዱስ ጴጥሮስን እነ ቅዱስ ጳውሎስን ገብሩ ወሐዋርያሁ የምንል ሰዎች ገና በምድር ያሉ ጳጳሳትን ገብሩ ብንላቸው ያከብራቸዋል እንጂ አያዋርዳቸውም። እመቤታችንም ነየ አመተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር አገልጋዩ እነሆኝ ነው ያለችው።
መጽሐፉም ይካ ይላል እንጂ ይጳ፣ ይቆ፣ ይመ አይልም።
ጳጳስም ቆሞስም ቄስም ካህናት ናቸው በእደ ገብሩ ካህን የሚለው ያጠቃልላቸዋል ስማቸው ነው።
ከጠለና ደግሞ በእደ ክቡር ቆሞስ ማለት ተጀመረ ይህንን ሳናስተካክል ዝም ስል ጊዜ ቀሳውስቱ አለቆች የኛስ ለምን ይቅርብን ብለው በእደ ክቡር መምህር ማስባል ጀምረዋል።
በመሠረቱ መምህር የሙያ ስም እንጂ የክህነት ስም አይደለም።
ስለዚህ እባካችሁ ዲያቆናቱም በእደ ገብሩ ካህን በሉ
አባቶችም በእደ ገብሩ ካህን መባል ታላቅ ክብር ስለሆነ ሌላ ነገር የሚጨማምሩ ልጇቻችሁን ገሥጿቸው።
መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ።
👉 @tonetore
⏳👇 Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
👉 https://www.youtube.com/channel/UCElyVBweer5T07XVECr_Nkg
BY ከነዓን ሚዲያ - Kenean Media
Share with your friend now:
tgoop.com/medrekenean/399