tgoop.com/meseretmedia/827
Create:
Last Update:
Last Update:
በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት በጅምላ የታሰሩ ወጣቶች እስከ 20 ሺህ ብር ከፍለው እየተለቀቁ መሆኑ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- እሁድ እለት የተጠናቀቀው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ባሉት ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ የታሰሩ ወጣቶች ገንዘብ ከፍለው እየተለቀቁ መሆኑ ታውቋል።
እነዚህ ልደታ አካባቢ በአፈሳ መልክ የታሰሩ ወጣቶች ጦር ሀይሎች አካባቢ ታስረው የቆዩ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 20 ሺህ ብር እየከፈሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለህዳሴ ግድብ የ2 ሺህ ብር ቦንድ እንዲገዙ እየተደረጉ መለቀቃቸውን መሠረት ሚድያ ከታሳሪዎቹ እና ቤተሰቦቻቸው ሰምቷል።
"በስብሰባው ምክንያት ተሰብስባቹ ተቀመጣችሁ ተብለው ቁጭ ብለው ከሚበሉበት በረንዳ የታፈሱት ባለፈው እሮብ ነበር" የሚለው አንድ የመረጃ ምንጫችን ከትናንት ጀምሮ የተወሰኑት እየተፈቱ መሆኑን ተናግሯል።
"ቦንድ ያልገዙት ተቀምጠው እኛ ወጣን" ያለን ደግሞ ለቦንድ 2 ሺህ ከፍሎ ነፃ የወጣ ግለሰብ ነው።
ከሰሞኑ እንደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ያሉ ተቋማት ከእስር ተፈቺዎችን እና ተገልጋዮችን ለማገልገል ወይም ከእስር ለመልቀቅ የ 500 ብር የህዳሴ ግድብ ቦንድ በግዴታ እያስገዙ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia
BY Meseret Media

Share with your friend now:
tgoop.com/meseretmedia/827