tgoop.com/meseretmedia/830
Last Update:
ኮምቦልቻ አቅራቢያ በእስር ላይ የነበሩ ከ890 በላይ እስረኞች በዛሬው እለት ተለቀቁ
(መሠረት ሚድያ)- በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ አቅራቢያ 'ጮሬሳ' ተብሎ በሚጠራው ካምፕ ውስጥ ከ890 በላይ የፖለቲካ እስረኞች በምግብ እና በውሃ ብክለት ምክንያት ታመው እንደነበር መሠረት ሚድያ የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ መዘገቡ ይታወሳል።
ሚድያችን ከእስረኞች ቤተሰቦች በወቅቱ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ እስረኞች ህይወታቸው አልፏል።
አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት በዚህ ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ ሁሉም እስረኞች በዛሬው እለት ተለቀዋል፣ የተለቀቁበት ምክንያትም ግን እንዳልተነገራቸው ታውቋል።
በሽታው በካምፑ ውስጥ የተቀሰቀሰው የካቲት 6/2017 ዓ/ም መሆኑን የተናገሩት የታሳሪ ቤተሰቦች ለእስረኞቹ የሚቀርበው ውሃ ከወንዝ እየተቀዳ በመሆኑ ለበሽታው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ብለው ነበር።
አሁን ነፃ የሆኑት ግለሰቦቹ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖን ኃይል ትደግፋላችሁ በሚል ከመስከረም ወር ጀምሮ ከተለያዩ የአማራ ክልል ወረዳዎች በማሰባሰብ ከኮምቦልቻ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኛው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታስረው እንደነበር ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
ከእስረኞቹ ውስጥ 220ዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና የተፈቀደላቸው ቢሆንም ታሳሪዎቹን የተረከበው የፌደራል ፖሊስ እስረኞቹን መልቀቅ የሚችለው መከላከያ እንጂ ፍርድ ቤት አይደለም በሚል ሊለቃቸው ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል እንደነበር ታውቋል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia
BY Meseret Media

Share with your friend now:
tgoop.com/meseretmedia/830