tgoop.com/nshachannel/1243
Last Update:
♥ ስለ ትዳር ክፍል 1 ♥
እሷን ለማግባት መሠረታዊ ምክንያቱ "መልክ" ከሆነ በእሳት አደጋ ወይም በመኪና አደጋ ወይ በሌላ ምክንያት ፊቷ ቢበላሽ ወይም አካሏ ቢጎድል ይፈታታል።ወይም እርሷን ለማግባት መሠረታዊ ምክንያቱ "ገንዘብ/ሀብት" ከሆነ በተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ አደጋ ንብረቷ ቢጠፋ ይፋታታል።ወይም ደግሞ እውቀቷን አይቶ ቢያገባት ይህም ቢሆን እውቀት ጸጋ ስለሆነ በእርጅና በሕመም ሊጠፋ ይችላል። ስለዝህ እውቀቷ ሲጠፋ ይፋታታል።
።
♥ታድያ ምንን አይተን እንጋባ?♥
በእርግጥ መጀመሪያውንም ትዳርን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲሰጥ ዋና እና መሠረታዊ ምክንያቱ 3 ነው። ይኽውም ዘር ለመተካት፥ ለመረዳዳት፥ እና አንድ ለአንድ ተወስኖ የፈቲው ጾርን ለማሸነፍ ነው።የሰው ልጅ ሲፈጠር ብዙ ዓይነት ፍላጎቶች እንዲስማሙት ተደርጎ ነው የተፈጠረው።ለምሳሌ የመብላት ፍላጎት አለው።ለዚህ ፍላጎቱ ምግብ ተሰርቶለታል።ሴት ከወንድ ወንድ ከሴት በመኝታ አንድ የመሆን ፍላጎት አለው።ለዚህ ፍላጎቱ ደግሞ ትዳር ተሠርቶለታል።ለሁሉም ፍላጎቶቻችን ደግሞ ድንበር ሥርዓት ተሠርቶልናል። ይኸውም ለትዳር አንድ ሴት ለአንድ ወንድ ነው።ሌላው ለመረዳዳት ነው። የሰው ልጅ በብዙ ረገድ ፍጹም ስላልሆነ ረዳት ያስፈልገዋል።ከአንድ ሁለት ይሻላል። አንድ ሊቅ፦
።
ሐንካስ በእግረ እውር ሖረ።
እውርኒ በዓይነ ሐንካስ ነጸረ።
ወበክልኤሆሙ ወይንየ ተመዝበረ።
።
ብለዋል ምስጢሩ መተባበርን ለመግለጽ ነው።አንካሳ በእውር እግር ሄደ።እውር ደግሞ በአንካሳ ዓይን አይቶ በጋራ ሆነው ሥራ መስራት እንደቻሉ ያሳያል። ስለዚህ ለመጋባት ተፈጥሯዊ የሴት እና የወንድ መሳሳብ፥ እንዲሁም በሃይማኖት አንድ መሆን፥ በእድሜ ተቀራራቢ መሆን፥ በቂ ነው። ሌላው እና ዋናው ግን እስከ ሞት የሚዘልቅ ፍቅር ሊኖረው ይገባል።
።
ብትነጫነጭበት፥ ብትቀማጠልበት፥ ብትሸራከት፥ ብትሰድበው፥ ወዘተ ከሌላ ወንድ ጋር እስካልተኛች ድረስ ይህንን ገራገር ሆኖ በትእግስት እየወደዳት እንክብካቤ እያደረገላት እስከ መጨረሻው ሊቀጥሉ ይገባል።ሚስትም ለባሏ ይህንኑ ማድረግ አለባት። ንብረታቸው ቢጠፋና ጎዳና ቢያድሩ፥ በተለያየ ምክንያት በጦርነት በሕመም በቦታ ቢለያዩ እስካሉ ድረስ ሊለያዩ አይገባም። ሌላው ግን አንዱ ሠራተኛ አንዱ ተቀማጭ መሆን የለባቸውም። በተቻለ መጠን ራሳቸውን ለማኖር ጠንክረው መስራት እና ልጆቻቸውን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ አለባቸው።
።
ጌታ ምእመናንን እንዴት እንደሚወዳቸው ምእመናንን ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንደሚወዳት ለመግለጽ በሙሽራ እና በሙሽራይቱ መስሎ ተናግሮታል።ይህም የሚያሳየን ትዳር ሁለት ሰዎች አንድ የሚሆኑበት ነው።
።
ክፍል 2 ይቀጥላል።
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1243