tgoop.com/nshachannel/1244
Last Update:
♥ ትዳር ክፍል ♥
በቁርባን ያልተደረገ ጋብቻ ቁጥሩ ከዝሙት ነው እንጂ እንደ ትዳር አይቆጠርም።እጮኝነት የዝግጅት ጊዜ ነው።በእጮኝነት ጊዜ ምንም ዓይነት የመኝታ ግንኙነት ሊኖር አይገባም። እጮኝነት የልቤ ንግሥት፥ የኔ ማር የሚባባሉበት ሳይሆን ስለወደፊት ሕይወት በጥልቀት የሚወያዩበት ጊዜ ነው። ከትዳር በፊት የሚደረግ ግንኙነት ቁጥሩ ከዝሙት ነው። ድንግልናቸውን ጠብቀው ለሚያገቡ ሰዎች ሥርዐተ ተክሊል ተደርጎላቸው ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ይጋባሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ ብዙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎች ስላሉበት ከትዳር በፊት ግንኙነት ያደረጉ ሰዎች ካሉ ደግሞ ንሥሓ ገብተው ጸሎተ መዓስባን ተደግሞላቸው ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ይጋባሉ። ከተጋቢዎች አንዱ ድንግል አንዱ ደግሞ ድንግል ካልሆነ ደግሞ ድንግል ለሆነው ተክሊል ተደርጎለት ድንግል ላልሆነው ሳይደረግለት ሥርዐቱ ይከናወናል። ከሠርግ በፊት ባልና ሚስት ትዳራቸው ይባረክላቸው ዘንድ 40 ቀን መጾም አለባቸው።
።
ያለ ቁርባን መጋባት የመጣው ከግራኝ መሐመድ መነሳት ወዲህ እንደሆነ ይነገራል።ነገር ግን ያለ ቁርባን የሚደረግ ሠርግ እና ጋብቻ ቁጥሩ ከዝሙት ስለሆነ ይህንን ነገር ካህናት ተገንዝበው በገጠርም በከተማም ማንኛውም ክርስቲያን የሆነ ሰው በቁርባን እንዲያገባ ሊያደርጉ ይገባል። ይህንን ባያደርጉ ግን በፈጣሪ ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ።ሌላው በትዳር ጊዜ እድሜ ለሴት ቢያንስ 15 ዓመት ሊሆናት ይገባል።ለወንዱም ቢያንስ 22 ዓመት ሊሆነው ይገባል። በፍትሐ ነገሥቱ መሰረት ይህ ምናልባት ተመችቷቸው ያደጉ ሴቶች ካሉ ቢያንስ 12 ዓመት ወንዱ ደግሞ 18 ዓመት ሊሆን እንደሚገባ ፍትሐነገሥት አንቀጽ 24 በሰፊው ይገልጻል።
።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
።
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1244