tgoop.com/nshachannel/1247
Last Update:
♥ ስለ ትዳር ክፍል 4 ♥
እሷ ወይም እሱ ሩካቤ ማድረግ የማይችል/የማትችል ከሆነ ቢፋቱ ይቻላል ነውርነት የለውም። ሚስቱ ጽንሷ ከታወቀ በኋላ ሩካቤ የሚያደርግ ወንድ የተጸነሰው ወንድ ቢሆን ግብረ ሰዶም ሴት ብትሆን ደግሞ ከልጁ እንደ ደረሰ ይቆጠራል።በወር አበባ ጊዜ፣ በጽንስ ጊዜ፥ በአጽዋማት ጊዜ፥ በዐበይት በዓላት ጊዜ፥ ሥጋውን ደሙን ከመቀበላቸው በፊት እና በኋላ ባሉት 3/3 ቀናት፥ በአራስነቷ ጊዜ፥ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም። ካህናት ሁለተኛ ካገቡ ብዙ ቀኖና ተሰጥቷቸው ከክህነታቸው ይሻራሉ። ሦስተኛ ካገቡ ግን ከክርስቲያንነታቸው ተወግዘው ይለያሉ። ክህነት የሌለው ምእመን አንድ ካገባ በኋላ በሞት ወይም በዝሙት ምክንያት ሌላ ሚስት ያገባል።ይህች ሁለተኛ ሚስቱም በዝሙት ወይም በሞት ብትለየው ታላቅ ቀኖና ተሰጥቶት ሦስተኛ እንዲያገባ ይፈቀዳል።ከሦስትኛ ሚስቱ በላይ አራትኛ ጊዜ ካገባ ግን ይወገዛል።
።
ከተጫጩ በኋላ ምናልባት ሴቲቱ ወይም ወንዱ የማግባት ሐሳቡን ቢቀይር እስካልተጋቡ ድረስ ነውር የለበትም። ሌላ ማጨትም ይችላል።ልመንኩስ ካለም መመንኮስ ይችላል። ነገር ግን ከተጋቡ በኋላ በዝሙት ካልሆነ በስተቀር ሊፋቱ አይገባም።ምናልባት አንዱ ልመንኩስ የሚል ሀሳብ ቢያቀርብ ባለቤቷ/ባለቤቱ ካልፈቀደችለት አይችልም። ባልና ሚስት ተመካክረው እንመንኩስ ቢሉ ወይም አንዱ ለአንዱ ከፈቀደለት ግን ይችላል።
።
♥ የተፈቀደ ፍቺ ♥
ባሏን ወይም ሚስቱን ሌላ ሰው ሊገድለው/ላት እንዳቀደ ሰምቶ ወይም ሰምታ ካልነገረችው ወይም ካልነገራት ይፋቱ ይላል ፍትሐነገሥት።በተጨማሪም ከላይ እንደገለጽኩት ሴቲቱ ወይም ወንዱ ሩካቤ ማድረግ የማይቻለው ወይም የማይቻላት ከሆነ ትዳር ይፈርሳል።መፋታት ይችላሉ።
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1247