tgoop.com/ras_film/897
Last Update:
ሳናውቅ አንፍረድ...
በአንድ መንደር ውሰጥ ይኖር የነበረ አንድ ትልቅ አርቲስት ነበር ፤ ይኼም አርቲስት ስራዎቹን በመሸጥ የተሻለ ክፍያ ያገኛል። ታዲያ በአንድ ወቅት በአካባቢው የሚኖሩ ድሃዎች ተሰባስበው ወደ አንጋፋው አርቲስት ጋር በመሄድ እንዲህ አሉት፦
"አንተ ለምንድነው የአካባቢውን ሰዎች የማትረዳው? አንተ ከሁሉም የተሻለ ገቢ አለህ። ካንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ዳቦ ጋጋሪውና ባለ ልኳንዳው ስጋ ሻጩ ለአካባቢያችን ድሆች በነጻ ይሰጣሉ በማለት ጠየቁት?
አርቲስቱም ፈገግ አለ በሁኔታው ሰዎቹ ግራ ተጋብተውና ተናደው ጥለውት ወጡ። ነግርግን ሌላ ቀን ወደ ውጭ ሲወጣ ጠብቀው ደበደቡት ፤ እድሜው የገፋ ነበረና በዚያው ታሞ አንድ ጠያቂ እንኳ ቤቱ ሳይመጣ በዚያው ሞተ።
ሆኖም ከዚያም ቀን በኋላ ዳቦ ሻጩም ስጋ ሻጩም በነጻ መስጠት አቆሙ። የአካባቢው ሰዎች ግራ ቢገባቸው ምከንያቱን መጠየቅ ጀመሩ። ያገኙትም ምላሽ ያ አንጋፋው አርቲስት በየወሩ በነጻ እንድንሰጥ ብዙ ብሮችን ይሰጠን ነበር ፤ አሁን ግን ስለሞተ አገልግሎቱ መስጠት እንደማይችሉና እንደተቋረጠ ተነገራቸው።
ብዙዎቻችን በሰዎች ላይ በቂ መረ8ዳት ሳይኖረን የተሳሳተ ግንዛቤ ሊኖረን ይችላል።
አንዳንዴ ነገሮች እንደምናየቸው አይደሉም በሰዎች ላይ ለመፍረድ አንቸኩል።
BY Ras film production funs
Share with your friend now:
tgoop.com/ras_film/897