tgoop.com/rezakuhakimu/1609
Create:
Last Update:
Last Update:
የቱ ነው አደምሽ?
አይን ሲበዛብሽ የኔ ባይ ሲበዛ
ራስሽን ብታይ አለምን እንደገዛ
ለምርጫ ቢከብድሽ የቱን እንደምትይ
ሌላው ትርፍ ነው ልብሽን ተከተይ
እንደ ጽጌሬዳ ሁሉም ቀጣፊሽ ነው
አበባ እንዳየ ንብ ከባቢሽ ብዙ ነው
ግን አስተውይና ንብሽን ምርጪ
ለየትኛው ንብ ነው ራስሽን ምትሰጪ?
ለውበትሽ ወድቆ ለመልክሽ ሰጋጁ
እሱ ቅርብ ሂያጅ ነው ፍቅር የለም በእጁ
አንቺነትሽን ብሎ ለድንሸ የመጣው
እሱ ነው ቀሳሚሽ በቶሎ ምረጪው።
🐝🐝🐝
▬▬▬▬๑۩🌹۩๑▬▬▬▬▬
ለአስተያየት @Arehimu
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
BY Islamic knowledge for all
Share with your friend now:
tgoop.com/rezakuhakimu/1609