tgoop.com/rezakuhakimu/1618
Last Update:
ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው
አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያችን - ﷺ - የቲም ነበሩ። እናታቸውን በ6አመታቸው አጥተዋል ፤ ርቧቸው ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረዋል ፤ ሌላም ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። ታዲያ አሏህ ጠልቷቸው ነው ብለህ ታስባለህን? በጭራሽ.
°
እንደውም በተቃራኒው እንደሚወድህ አመላካች ነው። ነብያችን - ﷺ - ይህን ስላሉ ፦ [ አሏህ ህዝቦችን ከወደደ ይፈትናቸዋል። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 23623). በሌላም ሐዲስ ላይ [ ከሰዎች ሁሉ በላእ የሚበረታባቸው ነብያቶች ናቸው ከዛም ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው። ] (ሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 144).
°
አማኝ በሆነ ሰው ላይ ፈተና መብዛቱ አሏህ ለሱ መልካምን ነገር እንዳሰበለትም አመላካች ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ አንድን ሙስሊም ከድካምም ይሁን ከበሽታ ከጭንቅም ይሁን ከሐዘን ከችግርም ይሁን ከጭንቀት ሙሲባ አይደርስበትም ከምትወጋው የሆነች እሾህም ብትሆን አሏህ በሷ አማካኝነት ከወንጀሉ ቢያፀዳው እንጂ። ] (ሶሒሁል ቡኻሪ ፥ 5641). አሏህ ፈተናን ታግሰው እሱ ከሚወዳቸው ባሪያዎቹ ያድርገን።
┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄ 🍃
https://www.tgoop.com/rezakuhakimu
BY Islamic knowledge for all
Share with your friend now:
tgoop.com/rezakuhakimu/1618